Stationery
በምሥ/ሸዋ ዞን የቦሰት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በመደበኛ በጀት የጽ/መሣሪያዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የመኪና ጎማ፣ የደንብ ልብስ፣ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በምሥ/ሸዋ ዞን የቦሰት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በመደበኛ በጀት የጽ/መሣሪያዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የመኪና ጎማ፣ የደንብ ልብስ፣ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም እጩ ተጫራቾች ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
1. ተጫራቾች በዘርፉ ሕጋዊ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር 2018 የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ የ2019 ፍቃዳቸውን ያደሱ መሆን አለባቸው።
2. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሠነድ ከነዋጋ ማቅረቢያ በታሸገ ኤንቨሎፕ ኮፒና ኦሪጅናል በመለየት ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ጨረታውም በ16ኛው ቀን ከቀኑ 5፡30 ታሽጎ በዕለቱ በ 8፡00 ሰዓት ቢሮ ቁጥር 3 ይከፈታል።
3. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000.00 በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፤
4. ማንኛውም እጩ ተጫራች ያሸነፈበትን ዕቃ ለማቅረብ አስቀድሞ ከመ/ቤቱ ጋር ውል ለመፈረም ፈቃደኛ መሆን አለበት።
5. ተጫራቾች በፌዴራል ወይም በኦሮሚያ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ አቅራቢዎች መዝገብ ላይ የተመዘገቡ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
6. የጨረታውን ሠነድ የማይመለስ ብር 200.00 ለእያንዳንዱ ሠነድ በመክፈል ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከቦሰት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 መግዛት ይችላሉ።
7. ከቀረበው አጠቃላይ የግዢ ዋጋ መስሪያ ቤቱ 20% ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።
8. የጠቅላላ የግዥ ዋጋ 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) ከሆነ 3% ተቀናሽ ይሆናል።
9. እጩ ተጫራቾች የተጨማሪ ታክስ ከፋይ ወይም ቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
10. የንግድ መለያ ቁጥር (TIN number) ማቅረብ ይኖርበታል።
11. ማንኛውም ተጫራች ካሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ ላይ 10% የዉል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል።
12. ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ካሸነፈ ከመ/ቤቱ ጋር ዉሉን ከፈረመ በኋላ ዕቃውን ለቦሰት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በራሱ ማጓጓዣ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል።
13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ይሆናል።
ለበለጠ መረጃ ሥ.ቁ 022-113-0062
በምሥ/ሸዋ ዞን የቦሰት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-27
- Bid closing time: 11:30
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 5፡30
- Bid opening: 2026-08-27 14:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00
- Region: Amhara
- Publishing entity: East Shewa Zone Boset Woreda Finance and Economics Development Bureau
- Bid bond: 5000.00 ብር
- Bid document price: ብር 200.00 ለእያንዳንዱ ሠነድ
- Published on: Addis Zemen (Aug 09, 2026)
- Posted at: 2026-08-10T08:00:35.000Z