Stationery and office consumables
የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/መምሪያ የጽህፈት መሳሪያዎች እና የጽዳት ዕቃዎች ግዥ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/መምሪያ ለሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ለ23ቱም ሴክተር መስሪያ ቤቶች በ2019 በጀት ዓመት በታቀደው መሰረት የጽህፈት መሳሪያዎች እና የጽዳት ዕቃዎች ግዥ ለመፈጸም በግልጽ ጨረታ በማወዳደር በዘርፉ ፈቃድ ካላቸው አቅራቢዎች መካከል በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት -
- 1) የጽህፈት መሳሪያዎች ግዥ: ሎት: 01/2019
- 2) የጽዳት ዕቃዎች-ሎት 02/2019
ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች መወዳደር ይችላሉ፡-
- በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ፣
- የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፣
- ከሚመለከተው መ/ቤት የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ አለበት፤
- የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ ቢሮ (አዲሱ ከተማ አስተዳደር ህንፃ) አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 (ሃምሳ አራት) በመቅረብ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 /ለአሥር/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርባችሁ ሰነድ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በየሎቱ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር ) በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲ ፒ ኦ (CPO ) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቬሎፕ አንድ ኦርጂናል እና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10(አሥር) ተከታታይ ቀናት ፋይናንስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 54 (ግዢ ኬዝ ቲም) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን በበዓላት ፤ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሠዓት የሚታሸግና የሚከፈት ይሆናል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር 046-212-13-34
የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋይ/ኢኮ/መምሪያ
Tender details
- Deadline: 2026-08-19
- Bid closing time: 09:30
- Bid closing (note): ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-19 10:00
- Bid opening (note): ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Region: Sidama
- Publishing entity: Hawassa City Administration Finance & Economic Development Command Bureau
- Bid bond: 100,000 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 09, 2026)
- Posted at: 2026-08-10T08:03:10.000Z