Stationery and office consumables
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በሸገር ከተማ አስተዳደር የገላን ክ/ከተማ ገ/ጽ/ቤት የጽህፈት መሣሪያ፣ የመኪና ጎማ፣ ፈርኒቸር፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የደንብ ልብስ፣ የቴክኒክ እና ሙያ እቃዎች፣ የፒካፕ መኪና እና ትንንሽ የቤት መኪና ኪራይ መከራየት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በሸገር ከተማ አስተዳደር የገላን ክ/ከተማ ገ/ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት ለመጀመሪያ ዙር ለሴክተር መሥሪያ ቤቶች የሚውሉ
- የጽህፈት መሣሪያ
- የመኪና ጎማ
- ፈርኒቸር
- ኤሌክትሮኒክስ
- የደንብ ልብስ
- የቴክኒክ እና ሙያ እቃዎች ግዢ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ እና
- የፒካፕ መኪና እና ትንንሽ የቤት መኪና ኪራይ መከራየት ስለምንፈልግ ከዚህ በታች የተገለጸውን መመሪያ መረጃዎች በማቅረብ/ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፍ ይጋብዛል።
1. በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ ፍቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፍሉ።
2. አቅራቢዎች ዝርዝር ተርታ የተመዘገቡና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣
3. ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ ተመዝጋቢ የሆነ።
4. የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ከሊራንስ ማቅረብ ይኖርባችኋል።
5. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት (15) ተከታታይ የሥራ ቀናት እና በሥራ ሰዓት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 1500.00 (አንድ ሺህ አምስት መቶ) ብር በሲንቄ ባንክ አካውንት 1064934721214 በማስገባት (በመክፈል) በገላን ክ/ከተማ ገቢዎች ባለሥልጣን ጽ/ቤት ወደ ደረሰኝ በመቀየር ሰነዱን ከገላን ከ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት መውሰድ ይችላሉ።
6. ተጫራቾች የሚያቀርቡበትን የዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር (ሰነድ ዋና እና ኮፒ ለየብቻ በታሽገ ኤንቨሎፕ በፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት (15) ተከታተይ የሥራ ቀናት ድረስ በገላን ክ/ከተማ ገ/ጽ/ቤት ባዘጋጀነው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይቻላል።
7. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የመኪናውን ሙሉ መረጃ (ሊብሬውን) ማቅረብ ይኖርበታል
8. ጨረታው በ16ኛው ቀን 4፡ዐዐ ሰዓት የጨረታ ሳጥን ታሽጎ (ተዘግቶ ልክ በዚሁ ቀን 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በገላን ክ/ከተማ ገ /ጽ/ቤት ውስጥ ይከፈታል። ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል። ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው የማይገኙ ከሆነ ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም።
9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበረያ ዋስትና ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ብቻ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
10. ተጫራቾች ጨረታውን አሸናፊነቱ ከተገለፀላቸው በኋላ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 10% በማስያዝ ውል መዋዋል ይጠበቅባቸዋል።
11. ተጫራቾች የጨረታውን አሸናፊነቱ ከተገለፀላቸው በኋላ ውል ካልፈፀሙና የውል ማስከበሪያ ካላስያዙ የጨረታ ማስከብሪያ ለመንግሥት ገቢ ይሆናል።
12. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሰነድ ውስጥ በተገለፀው መስረት የተጨራቱበትን የእቃ ናሙና /Sample/ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል።
13. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ለይ የተገለጹትን ማንኛውንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለው ማለት አይችልም።
14. የመወዳደሪያ በጨረታ ሰነዱ በተዘረዘረው መሠረት ተሞልቶ መቅረብ ይኖርበታል።
15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
16. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 445 0182 ወይም 09 23 57 49 41 በመደወል እና በአካል ተገኝቶ መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
አድራሻ፡- በሸገር ከተማ አስተዳደር የገላን ከ ከተማ ገ/ጽ/ቤት
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በሸገር ከተማ አስተዳደር የገላን ክ/ከተማ ገ/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-27
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-27 10:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: Dhaabbata Bosonaa fi Bineensa Bosonaa Oromiyaa Damee Harargee
- Bid bond: 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/
- Bid document price: ለእያንዳንዱ ሰነድ ብር 1500.00 (አንድ ሺህ አምስት መቶ) ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 09, 2026)
- Posted at: 2026-08-10T08:57:04.000Z