Property and building foreclosure

88 ካ/ሜ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

Description

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት ወ/ሮ የሊበንወርቅ ላሚሶ እና የፍ/ባለዕዳ አቶ ስዩም ወ/ሰንበት መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 53248 በ61/11/2013 ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/305507 በግንቦት 23 ቀን 2005 ዓ/ም በ14/2/2017 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 4 ከልል ውሰጥ የሚገኝ የቤት ቁጥር 864 የሆነ ቤት የካ/ቁ/35613 በሆነው መኖርያ ቤት ግቢ ውስጥ የተሰሩ 7 ከፍል ቤቶች የ7 ከፍል ቤቶች ያረፈበት 88 ካ/ሜ ከአጠቃላይ ግቢው የቀለበት መንገድ (የሰፈር መንገድ) 34 ካ/ሜ ይነካዋል። ይዞታው በ1988ዓ.ም በተነሳው አየር ካርታ መሰረት የጋራ ግቢ መሆኑን የሚያሳይ ስለሆነ በጋራ መውጫና መግቢያ ይኖረዋል ተብሎ ታሳቢ የሚደረግ ነገር ግን በአካል ወረዳው ወርዶ ባጣራው መሰረት አሁን ላይ በቤቱ ውስጥ ተከራይ የሚኖሩበትና የሚገቡበትና የሚወጡበት ለብቻ በር ያለው ሆኖ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 12,131,800 (አስራ ሁለት ሚሊዮን ሺህ አንድ መቶ ሰላሳ አንድ ሽህ ስምንት መቶ ብር) ሆኖ የትራክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ መስከረም 7 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 5፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ  እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን። ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-17
  • Bid closing time: 11:00
  • Bid opening: 2026-09-17 11:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
  • Bid bond: 25%
  • Published on: Addis Zemen (Aug 09, 2026)
  • Posted at: 2026-08-10T09:10:29.000Z
← Back to all tenders