Property and building foreclosure
አቢሲንያ ባንክ አ.ማ. ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
አቢሲንያ ባንክ አ.ማ ለሰጠው ብድር በዋስትና ያዛቸዉና በሠንጠረዡ የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደ ተሻሻለው) መሠረት ንብረቶቹ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች በጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲፒኦ በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም በማስራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ችላሉ።
- የጨረታው አሸናፌ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል። በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል። በጨረታው ተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ይመስላቸዋል።
- ተበዳሪው /መያዣ ሰጪው/ በሐራጁ ቀንና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ። ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል።
- የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል። ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ለቀሪው የሊዝ ክፍያ ገዢው ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ይዋዋላል።
- ንብረቱን በሥራ ሰዓት ፕርግራም አስይዞ መጎብኘት ወይም ማየት ይቻላል።
- ከታች በሰንጠረዥ ተራ ቁጥር 1 የተጠቀሰዉ ንብረት በሀራጅ ሲሸጥ ለገዥዉ ከፊል ፋይናንስ /ብድር/ ባንካችን የማይሰጥ ስለሆነ በካሽ ክፍያ ብቻ ግብይቱ እንደሚፈፀም እንገልጻለን፡፡
- ከታች በለኝጠረዥ ተራ ቁጥር 2 የተጠቀሰዉ ንብረት በሀራጅ ሲሸጥ በባንኩ የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟላ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢ /አሸናፊ /ባኩ በከፊል ብድር ሲሰጥ ይችላል።
- የጨረታ ቦታ አዲስ አበባ ከተማ፣ ቂርቆስ ክ/ ከተማ፣ ለገሀር በሚገኘው የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት 4ኛ ፎቅ ፎርክሎዠር እና ዴት ሊትጌሽን ለጨረታ ባዘጋጀዉ ቢሮ ላይ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 515 1153 እና 011 515 07 አ.አ በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪው ስም |
የመያዣ ሰጪው ስም |
ንብረቱ አይነት እና አገልግሎት |
የቦታው ስፋት በካ.ሜ |
ባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር |
ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ |
የጨረታው መነሻ ዋጋ በብር |
ጨረታው የሚካሄድበት ቀን |
የምዝገባ ሰዓት
|
የጨረታ ሰዓት
|
ጨረታ የወጣበት ጊዜ |
|
1 |
አቶ አማኑኤልበቀለ ባንቲውረድ (ሄማርስ ብረታ ብረት ንግድ) |
አቶ አዲሱ አባይ አባስበር |
ግንባታው ያልተጠናቀቀ G +3 መኖሪያ ቤት |
72 |
ETH0001000000-00004085450 (የይዞታ ልዩ መለያ ቁጥር AA000090700077) |
አዲስ አበባ ከተማ ኮልፌ
|
8,588.869.21
|
መስከረም 07 ቀን 2019 ዓ.ም.
|
4:30-5:30
|
5:30-6:00
|
ለመጀመሪያ ጊዜ |
|
2 |
አቶ ኢሳያስ ካሳዬ በቀለ |
አቶ ተስፋዬ ቶላ ደሜ |
G +1 መኖሪያ ቤት |
160 |
BI/14922/09
|
ኦሮሚያ ብ /ክ መንግስት ቢሾፍቱ ከተማ ዲባዩ ክ/ ከተማ (ቀበሌ 01) |
10,703,843.59
|
መስከረም 07 ቀን 2019 ዓ.ም. |
8:30-9:30
|
9:30-10:00
|
በድጋሚ |
Tender details
- Deadline: 2026-09-17
- Bid closing time: 16:00
- Bid closing (note): የሐራጁ መዝጊያ ሰዓት የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-09-17 16:00
- Bid opening (note): የሐራጁ መክፈቻ ሰዓት የተለያየ ነው
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Bank of Abyssinia S.C.
- Buyer address: Addis Ababa Ethiopia
- Bid bond: 25%
- Published on: Reporter (Aug 09, 2026)
- Posted at: 2026-08-10T11:40:05.000Z