House Furniture
ቡና ኢንሹራንስ አክሲዮን ማህበር የቢሮ እቃዎች፣ ኮምፒውተር እና ተዛማጅ እቃዎች፣ ተሽከርካሪዎች እና ተዛማጅ ግዥ፣ የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የህትመት ዓይነቶች እና የጽዳት እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ቡና ኢንሹራንስ አክሲዮን ማህበር ከዚህ በታች በሰንጠረዥ በዝርዝር የተገለፁትን የቢሮ እቃዎች፣ኮምፒውተር እና ተዛማጅ እቃዎች፣ ተሸከርካሪዎች እና ተዛማጅ ግዥ፣የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያዎች፣የህትመት ዓይነቶች እና የጽዳት እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የእቃው ዝርዝር |
የሎት ብዛት |
የጨረታ ማስከበሪያ መጠን |
|
1 |
የተለያዩ የቢሮ እቃዎች (Furniture) |
Lot (ጥቅል) 1 |
60,000 |
|
2 |
ኮምፒውተር እና ተዛማጅ እቃዎች-(Computer and related) |
Lot (ጥቅል) 2 |
100,000 |
|
3 |
የተለያዩ ተሽከርካሪዎች እና ሰመር ሰብል ፓንፕ-(Vehicles and related) |
Lot (ጥቅል) 3 |
100,000 |
|
4 |
የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያዎች(Stationeries) |
Lot (ጥቅል) 4 |
50,000 |
|
5 |
የተለያዩ የህትመት ዓይነቶች ግዥ(printings) |
Lot (ጥቅል) 5 |
50,000 |
|
6 |
የተለያዩ የፅዳት እቃዎች (Sanitary) |
Lot (ጥቅል) 6 |
50,000 |
በጨረታው ለመሳተፍ ተጫራቾች፡-
1. ከላይ ከሎት አንድ እስከ ስድስት የተገለፁትን የግዥ ዝርዝሮች ውስጥ በአንድ ወይም በሁሉም Lot (ጥቅል) መወዳደር ይችላሉ።
2. በመስኩ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የታደሰ የታክስ ከፋይነት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
3. ከአንድ ሎት በላይ የሚወዳደሩ ከሆነ ሰነዶቻቸውን በየሎቱ በመነጣጠል ለየብቻ በማድረግ ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን በየሎቱ የተጠየቀውን የጨረታ ማስከበሪያ የገንዘብ መጠን በኩባንያችን ስም በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ብቻ አብረው ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ከተጠቀሰው መጠን በታች ወይም ከተገለፀው አይነት የተለየ ያስያዘ ተጫራች ከጨረታ ውጭ የሚደረግ ይሆናል።
4. ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት ከአፍሪካ ሕብረት ጀርባ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ከፍ ብሎ በሚገኘው የቡና ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ ዋናው መ/ቤት ስለጨረታው የሚገልፀውን ሠነድ ለየሎቱ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) ሁለተኛ ፎቆ ፋይናንስ መምሪያ ክፍያ በመፈፀም የጨረታ ሰነዱን ከግዥና ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል (ምድር ቤት) በመምጣት መውሰድ ይችላሉ።
5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሰነድ በታሸገ ኤንቬሎፕ እስከ ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ.ም 4:00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
6. ጨረታው ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ በ4:30 ሰዓት በኩባንያው ዋና መ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ (ምድር ቤት) ይከፈታል።
7. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 470 5908 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
8. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፦
ቡና ኢንሹራንስ አ.ማ ዋና መ/ቤት
ግዥና ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል
የስልክ ቁጥር፡- 011 470 5908 / 011 126 3103
አዲስ አበባ
Tender details
- Deadline: 2026-08-24
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-08-24 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Bunna Insurance S.C.
- Buyer TIN: 0038530762
- Buyer address: ሳር ቤት ወይም አፍሪካ ህብረት ጀርባ ሕንፃ 3ኛ ፎቅ
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 300.00 ብር ለየሎቱ
- Published on: Reporter (Aug 09, 2026)
- Posted at: 2026-08-10T14:03:15.000Z