Vehicle and Machinery Sale

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት የህክምና ኦክሲጅን ማምረቻ ማሽን መሸጥ ይፈልጋል

Description

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት ከዚህ በታች በሰንጠረዥ ውስጥ የተጠቀሰውን የካፒታል ዕቃ ዱቤ ግዥ እና ክራይ ተከራይ በውሉ መሰረት ግዴታውን ባለመወጣቱ ምክንያት ባንኩ በአዋጅ ቁጥር 103/90 እና 807/2005 በተሠጠው ስልጣን መሰረት ከተከራዩ መልሶ የተረከበውን የካፒታል ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በጥሬ ገንዘብ መሸጥ ይፈልጋል።

የካፒታል ዕቃ ተከራይ ስም

 

የሚሸጠው ንብረት

የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር

 

የሚሸጠው ንብረትና የሚገኝበት ቦታ

የሐራጅ ደረጃ

 

ሐራጅ የሚካሄድበት ቦታ ቀን እና ሰዓት

አቶ ሀብታሙ አበጋዝ

 

የህክምና ኦክሲጅን ማምረቻ ማሽን

 

64,991,747.97

 

ቢሾፍቱ ከተማ ዱከም / በተከራዩ የማምረቻ ቅጥር ግቢ ውሰጥ

1

 

በተከራዩ ማምረቻ ቅጥር ግቢ ውስጥ ነሐሴ 19 ቀን 2018 . 400- 600 4:00–6:00

ማሳሰቢያ

1. ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 20% (ሃያ በመቶ) የባንክ ከፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡

2. አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT ጨምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ የሸያጭ ጨረታው ውጤቱ ይሰረዛል።

3. ህጋዊ ሰውነት ያላቸው ድርጀቶች በመወከል በሸያጭ ጨረታ ላይ የሚሳተፍ ግለሰብ የተረጋገጠ ዋና የውክልና ስልጣን ይዞ መቅረብ ይኖርበታል።

4. የጨረታው አሸናፊው ያስያዘውን ገንዘብ ከግዢው ዋጋ ሲታሰብለት ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ተመላሸ ይደረጋል።

5. የጨረታው አሸናፊ የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ነጻ መብት ሊኖረው አሊያም በመንግስት የሚፈለገውን ቀረጥ ለመክፈል ይገደዳል።

6. የጨረታው አሸናፊ 15% የተጨመሪ እሴት ታክስን ጨምሮ ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን እንዲሁም የስም ማዛዋወሪያ ክፍያ ጨምሮ ገዢው ይከፍላል።

7. አሸናፊ ተጫራች ማሸኑን ካለበት ማምረቻ ቦታ መውሰድ አሊያም ከይዞታ ባለቤቱ ጋር መስማማት ይኖርበታል።

8. ዝርዝርና ተጨማሪ መረጃ በተመለከተ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት መስሪያ ቤት በአካል በመቅረብ ማነጋገር ወይም በስልክ ቁጥር፡- 022-211-6687 ላይ መደወል ይቻላል። ንብረቱን መጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከዲስትሪክቱ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በማስያዝ መጎብኘት ይችላሉ።

9. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሃራጁን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-25
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid opening: 2026-08-25 12:00
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Development Bank of Ethiopia
  • Buyer address: DBE Head Office, Property and Facility Management Directorate Procurement Team, Tower II,5th floor,
  • Bid bond: 20%
  • Published on: Addis Zemen (Aug 10, 2026)
  • Posted at: 2026-08-11T07:15:27.000Z
← Back to all tenders