Textile, Garments and Uniforms

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዋ/ስ/አስፈጻሚ የመንግሥት ግዥ አስተዳደር ቡድን የተለያዩ አገልግሎቶች እና እቃዎች መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2019

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዋ/ስ/አስፈጻሚ የመንግሥት ግዥ አስተዳደር ቡድን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አገልግሎቶች እና እቃዎች ማለትም፡-

  • (ሎት1). እስታንደርዳቸውን የጠበቁ ችሎት ላይ የሚለበሱ የኘሮቶኮል ሡፍ ልብሶች እና ቆዳ ጫማዎች ግዥ
  • (ሎት2). የጽሕፈት መሣሪያዎች ግዥ
  • (ሎት3). የህትመት ሥራዎች ግዥ
  • (ሎት4). የእንስሳት መድሃኒት እና የህክምና መገልገያ መሣሪያ ዕቃዎች ግዥ
  • (ሎት5). የመኪና ኪራይ አገልግሎት ግዥ
  • (ሎት6) የድንኳን ኪራይ አገልግሎት ግዥ
  • (ሎት7). የዲኮር አገልግሎት ግዥ
  • (ሎት8). ቢሮዎችን በተለያዩ የእንጨት፣ እንጨት ነክና ተያየዥ ወዘተ...ማቴሪያሎች ለስራ ምቹ ማድረግ እና የፓርቲሽን ሥራ
  • (ሎት9). የተለያዩ የስብሰባ ፕሮግራሞችን የማስተዋወቅ እና መድረክ መምራት አገልግሎት ግዥ
  • (ሎት10). የተለያየ ዝሪያ ያላቸው ዶሮዎች ግዥ
  • (ሎት 11)  የዶሮ መኖ ግዥ
  • (ሎት12). የመኪና አልባሳትና ዕቃዎች ግዥ
  • (ሎት13). የቢሮ መጋረጃና ምንጣፍ ግዥ
  • (ሎት14). የተለያዩ የሽልማት እና ዕውቅና ዕቃዎች ግዥ
  • (ሎት15). የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስና የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ግዥ በጨረታ አወደድሮ መግዛት ይፈልጋል

 ስለሆነም በጨረታው ለመሣተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ሁኔታዎች በቅድሚያ ማሟላት ይኖርባቸዋል።

1. በዘርፉ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ማቅረብ የሚችሉ፣

2. የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉና ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

4. በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ

5. የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ በባንክ በተረጋገጠ CPO ብቻ በየሎቱ ለየብቻ ማቅረብ ይኖርባችዋል እንዲሁም አሸናፊው ድርጅት ላሸነፈባቸው ዕቃዎችና አገልግሎቶች የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርበታል። CPO ሲያሰሩ ለአቃ/ቃ/ክ/ከ/ዋና/ስ/አስፈጻሚፋይናንስቡድንወይምAk K/S/C/C/Executive finance team ብለውያሰሩ

  • (ሎት.1) 80,000.00 (ሰማኒያ ሺህ ብር)
  • (ሎት.2) 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)
  • (ሎት.3)-50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)
  • (ሎት.4)- 10,000.00 (አስር ሺህ ብር)
  • (ሎት.5)- 100,000.00 (መቶ ሺህ ብር)
  • (ሎት.6) 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)
  • (ሎት.7) 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)
  • (ሎት.8) 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)
  • (ሎት.9) 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)
  • (ሎት.10) 100,000.00 (መቶ ሺህ ብር)
  • (ሎት 11)- 80,000.00 (ሰማኒያ ሺህ ብር)
  • (ሎት.12) -40,000.00 (አርባ ሺህ ብር)
  • (ሎት.13)- 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)
  • (ሎት14) 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)
  • (ሎት15) 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)

ተጫራቾች ለተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች የሚገዙትን የእቃዎች እና አገልግሎቶች ዝርዝር የያዘውን ሰነድ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አቃ/ቃ/ክ/ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን 9ኛ ፎቅ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

6. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ መሙላት ያለባቸው ከቫት በፊት ያለውን ዋጋ ሲሆን የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒ በተለያዩ ፖስታ በማድረግ ኦርጅናል ላይ ኦርጅናል ኮፒ ላይ ኮፒ በማለት በታሸገ ኤንቨሎፕ እያንዳንዱን ሎት ለየብቻ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ለዚሁ ጨረታ ለማስገባት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚቻል ሲሆን ከገዙት ሰነድ ውጪ በሌላ ሠነድ የተሞላ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም።

7. ተጫራቾች የተጫረቱበትን ዕቃዎች ናሙና ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ያለባችሁ ሲሆን፣ ናሙና ያላቀረበ ተጫራች ለውድድር አይቀርብም

8. ጨረታው ከአስረኛው ቀን ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ቀን 4፡30 ሰዓት ይከፈታል።

9. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ከቁጥር 09 44 31 17 95 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል። መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት የመንግሥት ግዥ አስተዳደር ቡድን

አድራሻ፡- ቃሊቲ መናኽሪያ ፊት ለፊት የሚገኘው የአስተዳደሩ ህንጻ 9ኛ ፎቅ ላይ ነው።

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዋ/ስ/አስፈጻሚ የመንግሥት ግዥ አስተዳደር ቡድን


Tender details

  • Deadline: 2026-08-21
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከአስረኛው ቀን ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-21 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከአስረኛው ቀን ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Akaki Kaliti Sub-City Chief Executive Office, Government Procurement Office
  • Buyer address: ቃሊቲ መናህሪያ ፊት ስፌት የሚገኘው የአስተዳደሩ ህንጻ 9ኛ ፎቅ ላይ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: ለእያንዳንዱ ሎት 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 10, 2026)
  • Posted at: 2026-08-11T07:33:54.000Z
← Back to all tenders