Plastic Products
በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የውሃና ፍሳሽ መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ዲቪዥን ብዛት ሃምሳ (50) በFiber Reinforced Fiberglass የተሰሩ ተንቀሳቃሽ የህዝብ መፀዳጃ ቤቶችን በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር AAWSA/WSIDD/GOV/NCB/G002/2018
በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የውሃና ፍሳሽ መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ዲቪዥን ብዛት ሃምሳ (50) በFiber Reinforced Fiberglass የተሰሩ ተንቀሳቃሽ የህዝብ መፀዳጃ ቤቶችን በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎችን በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
1. ተጫራቾች ዘወትር በስራ ሰዓት ልደታ በሚገኘው የህዝብ መናፈሻ ጎን ዲቪዥን ጽ/ቤት በመገኘት ከላይ ለተጠቀሰው እቃ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 300.00(ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
2. ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ በዕቃ አቅራቢነት በፋይናስና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር መመዝገቡን የሚያረግጥ የምስክር ወረቀት፣ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር መለያ ቁጥር (TIN) ሰርትፍኬትና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
3. በጨረታው ለመሳተፍ በቅድሚያ በተዘረዘረው መሰረት የጨረታ ማስከበሪያ ቢያንስ ለ90 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ በCPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ማስያዝይ ይኖርበታል። ይህንኑም እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ከዋናው ሰነድ ጋር በማስያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት።
4. አሸናፊው ተጫራች ላሸነፈበት ዕቃ የጠቅላላ ዋጋውን 10% (የውል ማስከበሪያ) ውል በተፈረመ በ15 ቀናት ውስጥ ማስያዝ ይኖርበታል። የሚገዙ እቃዎችና ተያያዥ አገልግሎቶች መጠን 20% ሊጨምር ወይም 20% ሊቀንስ ይችላል::
5. ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ለ60 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን አለበት። ከዚህ ያነሰ የጨረታ ዋጋ ፀንቶ መቆያ ጊዜ ያቀረበ ተጫራች ከጨረታው ይሰረዛል።
6. የጨረታ ሰነዱን በስሙ አስመዝግቦ ያልገዛ ማንኛውም ተወዳዳሪ በጨረታው መሳተፍ አይችልም።
7. ጨረታው ነሐሴ 21 ቀን 2018 ዓ/ም ከቀኑ 8፡00 ስዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕለቱ ከቀኑ በ8፡30 5ኛ ፎቅ በመ/ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል ። ከጨረታው መዝጊያ ሰዓትና ቀን ዘግይቶ የሚመጣ ማንኛውም የመወዳደሪያ ሰነድ ተቀባይንት የለውም፡፡
8. ተጫራቾች ዲቪዥን መ/ቤቱ ባስቀመጠው የዋጋ ማቅረቢያ ፎርማት መሰረት ግልጽ በሆነ መልኩ ሞልቶ ማቅረብ ይኖርበታል። የሚቀርበው ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን ያካተተ መሆን አለመሆኑን በግልጽ ተለይቶ መቀመጥ አለበት። ይህንን ያልገለጸ ተወዳዳሪ ያቀረበው ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስን እንዳካተተ ተደርጎ ይቆጠራል።
9. ዲቪዥኑ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡ ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 የቦታው ልዩ ስም፡- ልደታ ኮንዶሚኒየም ልደታ መናፈሻ አጠገብ
ስልክ ቁጥር +251 11 557 9036 (1ኛ ፎቅ ግዥ ክፍል)
የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ውሃና መሰረት ልማት ማስፋፊያ ዲቪዥን
Tender details
- Deadline: 2026-08-27
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-08-27 14:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Addis Ababa Water and Sewerage Authority
- Buyer address: ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ-08 ፣ የቦታው ልዩ ስም፡- ልደታ ኮንዶሚኒየም ልደታ መናፈሻ አጠገብ
- Bid bond: 100,000.00 ብር
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 10, 2026)
- Posted at: 2026-08-11T08:09:15.000Z