Textile, Garment and Leather
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አየር ጤና አጠቃላይ 2ኛ/ ደ/ት/ቤት በ2019 ዓ.ም የተለያዩ ዕቃዎችን ለመግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2016
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አየር ጤና አጠቃላይ 2ኛ/ ደ/ት/ቤት በ2019 ዓ.ም ፋ/ገን/የሥራ ሂደት በጨረታ ቁጥር 001/2019 ዓ.ም መሰረት ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት የመማር ማስተማር የሚውሉ ዕቃዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1 የደንብ ልብስ 15000.00
- ሎት 2. አላቂ የቢሮ እቃዎች 12000.00
- ሎት 3. ህትመት 10000.00
- ሎት 4 አላቂ የትምህርት እቃዎች 15000.00
- ሎት 5 አላቂ የፅዳት እቃዎች 5000.00
- ሎት 6. የተለያዩ መጻህፍት 1000.00
- ሎት 7 ቋሚ ኤሌክትሮኒክ እቃዎች 10000.00
- ሎት 8 ፈርኒቸር የቤትና የበሮ ቋሚ ዕቃዎች 10,000.00
- ሎት 9. የተለያዩ የጉልበት ስራዎችና የጭነት አገልግሎት 1000.00
- ሎት 10 ጀነሬተር ፕሪንተር እድሳትና ጥገና 9000.00
- ሎት 11. ጥገና 20000.00
በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፤
1. በዘርፋ አግባብነት ያለው ሕጋዊ የታደሰ ፈቃድ ያለው ፡ የዘመኑን ግብር የከፈለ።
2. በመንግሥት ግዥ ኤጀንሲ በዕቃ አቅራቢነት የተመዘገበበትን ኮፒ ማቅረብ የሚችል።
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
4. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ሠራ ቀናት የማይመለስ በእያንዳንዱ ሎት 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረትውን ዝርዝር ሰነድ ከግዥ ክፍል መውሰድ ይቻላል።
5. ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ በመሙላት በታሸገ ፖስታ ኦርጅናል እና ኮፒ ማስገባት አለበት። ሰነዱ ላይ ፊርማና ክብ ማህተም መኖር አለበት።
6. ተጫራቾች ከላይ በየሎቱ የተጠቀሱትን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው።
7. ናሙና ለሚያስፈልጋቸው የዕቃ አይነቶች ናሙና ማቅረብ። በናሙና ለማቅረብ የሚያስቸግሩትን በፎቶ ጨረታው ከመዘጋቱ ቀደም ብለው መቅረብ ይኖርባቸዋል። የዕቃ አይነቶች ወይም የሚቀርበው የዕቃ መግለጫ /specification/ መሰረት መቅረብ ይኖርበታል። ናሙናዎች በጨረታ ለተሸነፉ ተጫራቾች ተመላሽ ይሆናሉ።
8. ጥቃቅን እና አነስተኛ ዕቃ አቅራቢዎች ከሚመለከተው አካል በት/ቤቱ ስም የተጻፈ ደብዳቤ አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
9. አሸናፊው ያሸነፈበትን እቃ ትምህርት ቤቱ የዕቃ መረከቢያ ስቶር ድረስ በራሱ ትራንስፖርት በማቅረብ ማስረከብ ይኖርበታል።
10. ጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን 11፡30 ታሽጎ በ11ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
11. አሸናፊው ውል ገብቶ ዕቃዎችን ከማስገባት በፊት ውል የመሰብሰቢያ 10 በመቶ ማስያዝ አለባቸው።
12. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
13. ት/ቤቱ አሸናፊው ድርጅት ላሸነፈባቸው ዕቃዎች 20/100 ብዛት ከውል በፊት የመቀነስ ወይም የመጨመር መብት አለው።
14. በማስታወቂያው ላይ ያልተገለጹ ነገሮች ቢኖሩም በግዥ መመሪያ መሰረት ተፈፃሚ ይሆናሉ።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0118357496/0118387908
አድራሻ፡- በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ አየር ጤና አጠቃላይ 2ኛ ደ/ት/ቤት ውስጥ አየር ጤና ታክሲ ተርሚናል ፊት ለፊት
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አየር ጤና አጠቃላይ 2ኛ/ደ/ት/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-20
- Bid closing time: 17:30
- Bid closing (note): ጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን 11፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-21 12:00
- Bid opening (note): ጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ayer Tena General Secondary School
- Buyer address: አየር ጤና ታክሲ መናኸሪያ ፊት ለፊት
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Published on: Addis Zemen (Aug 10, 2026)
- Posted at: 2026-08-11T08:12:23.000Z