Fuel and Lubricants

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሻሸመኔ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ለ2019 በጀት ዓመት ለዲስትሪክቱ ተሽከርካሪዎችና መሣሪያዎች አገልግሎት የሚውሉ የተለያየ ዓይነት ያላቸው ዘይቶችና ቅባቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ኢመአ/ሻሽ/006/2019

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሻሸመኔ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ለ2019 በጀት ዓመት ለዲስትሪክቱ ተሽከርካሪዎችና መሣሪያዎች አገልግሎት የሚውሉ የተለያየ ዓይነት ያላቸው ዘይቶችና ቅባቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠብቅባቸዋል።

1. ተጫራቾች የ2018 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፍቃድ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርቲፍኬት እና የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።

2. ተጫራቾች ለ2017 በጀት ዓመት ግብር ስለመክፈላቸው የሚገልጽ ክሊራንስ ማቅረብ አለባቸው።

3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ብር 50,000.00 (ሀምሳ ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም።

4. ተጫራቾች ዋጋ የተሞላበትን ፋይናንሻልና ቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ በማድረግ በተለያየ ፖስታ በማሸግ በእለቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

5. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጨረታው በ16ኛው የሥራ ቀን ከሰዓት በኃላ 8፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ የሚከፈት ይሆናል። በእለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር 1000002579859 ገቢ በማድረግ የገቢ ደረሰኝ ይዞ በመቅረብ ከሻሸመኔ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ዕቃ ግዥ አ ን/አስተዳደር ቢሮ የጨረታ ሰነዱ መግዛት ይቻላል።

7. በጨረታው መክፈቻ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም መሥሪያ ቤቱ ጨረታውን የመክፈት መብቱ የተጠበቀ ነው።

8. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0462 114 616 መጠቀም ይችላሉ።

9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር

የሻሸመኔ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-25
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ16ኛው የሥራ ቀን ከሰዓት በኃላ 8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-25 14:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ16ኛው የሥራ ቀን ከሰዓት በኃላ 8፡30 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሻሸመኔ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 10, 2026)
  • Posted at: 2026-08-11T08:14:57.000Z
← Back to all tenders