Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን የሠኮሩ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት እስቴሽነሪ፣ የቢሮ ፈርኒቸር፣ የመኪና ጎማ፣ ፊልትሮ ዘይት እና ፍሬን ሸራ፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የሠራተኞች የደንብ ልብስ እና ጫማ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን የሠኮሩ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  1. እስቴሸነሪ
  2. የቢሮ ፈርኒቸር
  3. የመኪና ጎማ ፊልትሮ ዘይት እና ፍሬን ሸራ
  4. የፅዳት ዕቃዎች
  5. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
  6. የሠራተኞች የደንብ ልብስ እና ጫማ

በዚሁ መሠረት፡-

1. ተጫራቾች ህጋዊ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም በአቅርቦት እና በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

2. ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) ከሠኮሩ ሀገር ውስጥ ገቢ /ጽ/ቤት በመክፈል ሠኮሩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 በማቅረብ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታው ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት በመገኘት መግዛት ይችላሉ።

3. ተወዳዳሪዎች የሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ እቃ 15,000 (አስራ አምስት ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ ወይም (CPO) ከዋናው ቴክኒካል ሰነዱ ጋር በአንድ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው።

4. ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ 11፡30 ድረስ የእቃውን ዋጋ በመግለፅ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ Original & Copy በወረዳው ገ/ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።

5. ጨረታው መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

6. እቃዎቹ በጥያቄያችን መሠረት ደረጃቸውን እና ጥራታቸውን የጠበቁ መሆን አለባቸው።

7. ጨረታውን ያሸነፈ ድርጅት ዕቃዎቹን በጥራት ካላቀረበ ዕቃውን የማንቀበል መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን።

8. ጨረታውን ያሸነፈ ድርጅት እቃውን እስከ ወረዳው ድረስ ማቅረብ ወይም ማድረስ ይኖርበታል።

9. መስሪያ ቤቱ ከአሸናፊ ተጫራቾች ጋር የዕቃውን ብዛት ከማቅረቡ በፊት በ20% የመጨመር ወይም መቀነስ መብት አለው።

10. በመጨረሻ ወረዳው ወይም ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው።

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 09-30-50-40-12, 09-35-15-20-72 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።

በኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን የሠኮሩ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-08
  • Bid closing time: 17:30
  • Bid opening: 2026-10-09 10:30
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Jimma Zone Sekoru Woreda Finance and Economic Development Bureau
  • Bid bond: 15,000.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 18, 2026)
  • Posted at: 2026-09-18T08:54:52.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders