Spare Parts and Car Decoration Materials

የደባርቅ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ፅ/ቤት በ 2019 በጀት ዓመት ለጽቤቱ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ በሎት አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል

Description

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የደባርቅ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ፅ/ቤት በ 2019 በጀት ዓመት ለጽቤቱ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ በሎት አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።

ስለዚህ -

  • ሎት 1- የመኪና ና የማሽነሪ መለዋወጫ (ስፔርፓርት) እቃዎች
  • ሎት 2 - የማሽነሪ እና የመኪናዎች ጎማና ባትሪ

ስለዚህ ተጫራቾች ሊያሟሉት የሚገባቸው-

  1. ህጋዊ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው
  2. ቲን ነምበር ያላቸው
  3.  የግዥ መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ(VAT) ቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናቶች በመንግስት የስራ ሰዓት የጨረታ ሰነዱን በብር 100 /አንድ መቶ ብር/ መግዛት ይቻላል፡፡
  5. ተጫራቾች ለጨረታ - ማስከበሪያ ለሚጫረቱበት ጨረታ በየሎቱ በእያንዳንዱ ማለትም ለሎት 1- የማሽነሪና መኪና መለዋወጫዎች ስፔርፓርት ግዥ 30,000 ብር ለሎት 2 ጎማና ባትሪ ግዥ 20,000 ብር ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ፣ በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ በመሂ 1 የተቆረጠ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ ተረጋገጠ ሌተርኦፍ ክሬዲት ሆኖ መረጃውን ፖስታው ውስጥ አስገብተው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
  6. የጨረታ ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 13 በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመ ጊዜ ጀምሮ በ16ኛ ቀን ከቀኑ 4፡00 ስዓት ድረስ ወይም ከዚያ በፊት አንድ ኦርጅናል ና አንድ ፎቶ ኮፒ በታሸገ ፖስታ ከጨረታ ሳጥኑ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. የመጫረቻ ሰነዱ ዋጋ ፀንቶ የሚቆየው ጊዜ ለ40 የስራ ቀናት ይሆናል፡፡
  8.  ጨረታዉ ቢሮ ቁጥር 13 በተገለጸዉ ቦታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመ ጊዜ ጀምሮ በ16ኛ ቀን ከቀኑ 4፡00 ስዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ወይም ባይገኙ ከቀኑ በ4፡30 ስዓት ጨረታው ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
  9. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የዕቃ ዓይነት ዝርዝር ከሚገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዕቃ ዝርዝር መረዳት ይችላሉ::
  10. አሽናፊው ድርጅት ንብረቱን ደባርቅ ከተማ አስተዳደር ከተማ ና መሰረተ ልማት ፅ/ቤት ቢሮ ቁጥር 13 ድረስ በማምጣት ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
  11. ተጫራቾች ሰነዱን በሚሞሉበት ሰዓት ስርዝ ድልዝ መኖር የለለበት ሲሆን የእቃው ናሙና ቢሮ ቁጥር 13 በግንባር በመቅረብ ማየት ይኖርባቸዋል፡፡
  12. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ሙሉ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን በሙሉ በር/ አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
  13. ጨረታው በሎት ጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ሙሉ በሙሉ በሞላ ስለሆነ ከመጫረቻ የዋጋ ም መሙያ ሰነዱ ላይ ክፍት ማድረግ የለባችሁም፡፡ በተጨማሪም የዕቃዎች ብዛት ከበጀት አንፃር ገና ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
  14. መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  15. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ አቅራቢዎች ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልጋቸው በስልክ  ቁጥራችን 058 1170033 ወይም 0581171208 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ፡- ሁሉም ዕቃዎች ጥራቱን የጠበቀና በተጠየቀው ሞዴል መሰረት ኦርጅናል መሆን አለባቸው፡፡

ተጨማሪ ማብራሪያዎች መረጃዎች ካሉ በቢሮአችን በውስጥ ሰሌዳ ማስታወቂያ የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

የደባርቅ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሠረተ ልማት ጽ/ቤት 


Tender details

  • Deadline: 2026-08-25
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመ ጊዜ ጀምሮ በ16ኛ ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-25 10:30
  • Bid opening (note): በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመ ጊዜ ጀምሮ በ16ኛ ቀን ከቀኑ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Debarek City Administration Infrastructure Development Bureau
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 10, 2026)
  • Posted at: 2026-08-11T08:19:45.000Z
← Back to all tenders