Vehicle and Machinery Sale

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋምቤላ ዲስትሪክት የእርሻ ትራክተር እና ማረሻ ማሽን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በድርድር ጨረታ ለመሸጥ ወይም ለማከራየት ይፈልጋል

Description

የድርድር ጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋምቤላ ዲስትሪክት በሊዝ ፋይናንሲንግ ስርዓት ደንበኛ የሆነው ሀርቨስት ሞደርን እርሻ መካናይዜሽን አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማህበር / ለግብር ሜካናይዜሽን ፕሮጀክት አገልግሎት ከባንኩ በኪራይ የወሰደውን የእርሻ ትራክተር እና ማረሻ የማሽን የኪራይ እና የአገልግሎት ክፍያ በገባው ውል መሰረት ሊፈጽም ባለመቻሉ ምክንያት ባንኩ መልሶ የተረከባቸውንና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በድርድር ጨረታ ለመሸጥ ወይም ለማከራየት ይፈልጋል።

1. የሚሸጡ / የሚከራዩ ንብረቶች ዝርዝር

.

የተከራዩ ስም

ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ

የመያዣ ንብረት ዝርዝር መረጃ

የድርድሩ መነሻ ዋጋ ብር

የድርድሩ ደረጃ

የድርድሩ የሚካሄድበት ቦታ

1

ሀርቨስት ሞደርን እርሻ ሜካናይዜሽን አገልግሎት /የተ/የግ/ማህበር

በጋ////መንግስት አኙዋ  ዞን ጋምቤላ ከተማ የዲስትሪክት የዋስትና ንብረት ማከማቻ መጋዘን ቅጥር ግቢ ዉስጥ

አንድ LANDINI 2022  MODEL 133Hp Tractor እና አንድ AGRI-WAY ባለ28 ምጣድ መከስከሻ

7,265,379.06 ሰባት ሚሊዮን ሁለት መቶ ስድሳ  አምስት ሺህ ሶስት መቶ ሰባ ዘጠኝ ብር ከ06  ሳንቲም

 

 

 

የድርድር ጨረታ

 

ጋምቤላ ዲስትሪክት ጽ/ቤት፣ ነሐሴ 28 ቀን 2018 ዓ/ም ከረፋድ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት 

2. የጨረታው መመሪያ

  1. ከላይ የተመለከቱትን ንብረቶች በጥሬ ገንዘብ መግዛት ወይም መከራየት የሚፈልግ ማንኛውም አካል (ግለሰቦች፣ ተቋማት ወይም አነስተኛና መካከለኛ ማህበራት) ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው የንብረቱን የድርድር መነሻ ዋጋ 10% በጥሬ ገንዘብ ወይም በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ስም በተዘጋጀና በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) በማስያዝ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ በድርድሩ መሳተፍ ይችላሉ።
  2. ንብረቱን ሙሉ በሙሉ በጥሬ ገንዘብ (ካሽ) ለመግዛት ተደራድሮ ያሸነፈ ተጫራች ቀሪውን ገንዘብ በ15 ተከታታይ ቀናት ጊዜ ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል። ካልከፈለ የድርድሩ ውጤት ተሰርዞ የተያዘው ገንዘብ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል። ለሥራው አስፈላጊ የሆኑ ማስረጃዎችን (የንግድ ፈቃድ፣ የታደሰ መታወቂያ ወዘተ) ይዞ መቅረብ ያስፈልጋል። ድርድሩ ባልተሳካላቸው ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወይም ሲፒኦ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
  3. የድርድሩ አሸናፊ ንብረቶቹን በጥሬ ገንዘብ የሚገዛ ከሆነ ተመሳሳይ ከቀረጥ ነፃ የመጠቀም መብት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል። ከቀረጥ  ነፃ የመጠቀም መብት ከሌለው በመንግሥት የሚጠበቁ ማናቸውንም ቀረጥና ሌሎች ክፍያዎች በቅድሚያ የመክፈል ግዴታ አለበት።
  4. የድርድሩ አሸናፊ ባሸነፈበት ዋጋ ላይ 15%VAI (ተጨማሪ እሴት ታክስ) ጨምሮ የመክፈል ግዴታ አለበት።
  5. አሸናፊው ተጫራች ንብረቱን ለመከራየት (በሊዝ) የሚፈልግ ከሆነ ቢያንስ የማሽኑን ጠቅላላ ዋጋ 20% በቅድሚያ በመክፈል በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የባንኩን የማሽነሪ ኪራይ መስፈርት በማሟላት የማሽነሪ ኪራይ ውል መፈረም ይኖርበታል። በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ግዴታውን ካልተወጣ አሸናፊነቱ ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል።
  6. ንብረቶችንከድርድሩ በፊት ማየት ወይም መጎብኘትየሚፈልጉተጫራቾች ከባንኩ ጋር አስቀድመው ፕሮግራም በመያዝ መጎብኘት ይችላሉ። ተጫራቾች በሠንጠረዡ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በጋምቤላ ዲስትሪክት ቅጥር ግቢ በአካል ተገኝተው ድርድሩን ማካሄድ ይኖርባቸዋል።
  7.  ባንኩ የተሻለ አማራጭ መንገድ ካገኘ ድርድሩን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  8. ለማንኛውም ማብራሪያ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋምቤላ ዲስትሪክት በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር +251 47 551 2577/ +251 47 551 2588 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋምቤላ ዲስትሪክት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-03
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid opening: 2026-09-03 12:00
  • Region: Gambela
  • Publishing entity: Development Bank of Ethiopia
  • Buyer address: DBE Head Office, Property and Facility Management Directorate Procurement Team, Tower II,5th floor,
  • Bid bond: 10%
  • Published on: Addis Zemen (Aug 10, 2026)
  • Posted at: 2026-08-11T10:07:30.000Z
← Back to all tenders