Medical Equipment and Supplies

በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/ መስተዳድር የካፋ ዞን የገ/ፃዲቅ ሻዎ አጠቃላይ ሆስፒታል ለ2019 በጀት ዘመን የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 01/2019

በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/ መስተዳድር የካፋ ዞን የገ/ፃዲቅ ሻዎ አጠቃላይ ሆስፒታል ለ2019 በጀት ዘመን ከዚህ በታች የተጠቀሱትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት

1. ሎት/1/ የመድሃኒትና ህክምና መሣሪያ ግዥ

2. ሎት/2/ የመኪና ጎማ ገዥ

3. ሎት/3/ የጽህፈት መሳሪያዎች ግዥ

4 . ሎት/4/ የፅዳት እቃዎች ግዥ

5. ሎት/5/ የደንብ ልብስ ግዥ

6 . ሎት/6 / የቧንቧ ዕቃዎች እና ህንፃ ተገጣጣሚ እቃ ገዥ

7. ሎት/7/ የህትመት አገልግሎትግዥ

8. ሎት/8/ ለተኝቶ ታካሚዎች የምግብ አገልግሎት ግዥ ብቻ ሲሆን ተወዳዳሪዎች የሚጠበቅባቸው ቅድመ ሁኔታዎች በሎት/ህ/ ቀደም ሲል በመ/ቤቱ የፁሑፍ ማስጠንቀቂያ ያለው ተጫራች መወዳደር አይችልም በመቀጠል የገቢዎች ክሊራንስ ያለው፡፡

1. የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ እና የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ፡፡

2 . የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው እንዲሁም ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ

3 . በመንግስት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

4. የእቃ አቅራቢነት ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ እና ለሎት /8/የገቢዎች ክሊራንስ ማቅረብ ግዴታ ነው።

5 . ተራ ቁጥር ከሎት2 እስከ ሎት6 ድረስ ለወጡ ጨረታዎች ናሙና ማቅረብ ግዴታ ሆኖ ሎት/7/ ከመ/ቤቱ ናሙና በመውሰድ መጫረት የሚችሉ መሆኑን ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ ቦንጋ ገ/ፃ/ሻዎ/ ሆስፒታል 3ኛ ፎቅ ግዥ ንብረት አ/ር ቢሮ ቁ.22 በመቅረብ የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር ለእያንዳንዱ ጨረታ/500/ አምስት መቶ ብር በመክፈል መውሰድ ይችላሉ። ለእያንዳንዱ ጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር ሲፒኦ እና ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ቼክ እና በባንክ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ማቅረብና ማስያዝ አለባቸው። የጨረታ ሰነድ አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ ዋጋ በመሙላት ቦንጋ ገ/ፃ/ሻዎ/አጠቃላይ ሆስፒታል 3ኛ ፎቅ ግዥና ንብረት አ/ር ቢሮ ቀ.22 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ላይ ፖስታዎችን ማስገባት ይችላሉ።

6. ጨረታው በ16ኛው ቀን ላይ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ ቦንጋ ገ/ፃ/ሻ/አ/ሆስፒታል 3ኛ ፎቅ ግዥና ንብረት አ/ር ቢሮ ቁ.22 ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል።

7. ተጫራች ያሸነፈበትን እቃ ሙሉ በሙሉ እስከ ገ/ፃ/ሻ/አ/ሆስፒታል ቅጥር ግቢ በሚገኘው ግምጃ ቤት/ ንብረት ክፍል ለማቅረብ ፈቃደኛ የሆነ እና በበጀት ዘመኑ ተጨማሪ ግዥ ፍላጎት ሲቀርብ ባሸነፈ ዋጋ ማቅረብ የሚችል።

8. ተጫራቾች ተሟልቶ አለመገኘት ሂደቱን እያስተጓጉልም፡፡

9 . አሸናፊ ድርጅት ማሸነፉ ሲረጋገጥ ያሸነፈበትን የጠቅላላ ዋጋ 10% ውል ማስከበሪያ ለማስያዝ በሆ/ሉ ስም በዝግ አካውንት ለማቅረብ ፍቃደኛ የሆነ እና ማሸነፉ ከተረጋገጠበት አምስት ቀናት ቀርቦ የውል ስምምነት ለመፈፀም ፈቃደኛ የሆነ

10. ጨረታው የሚከፈተው ቦንጋ ገ/ጻ/ሻ/አጠ/ሆስፒታል 3ኛ ፎቅ ግዥና ንብረት አ/ር ቢሮ ቁ.22 ሲሆን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ የሚቀጥለው የሥራ ቀን ላይ ይሆናል፡፡

11. ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 047 331 0316 / 047 331 2361 ያገኙናል።

የገ/ፃ/ሻዎ/አጠቃላይ ሆስፒታል / ከፋ ቦንጋ


Tender details

  • Deadline: 2026-08-26
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ላይ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-26 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ላይ 4፡30 ሰዓት
  • Region: South West Ethiopia Region
  • Publishing entity: Kafa Zone G/Tsadik Shawo General Hospital
  • Bid bond: 50,000.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Bid document price: 500.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published on: Addis Zemen (Aug 11, 2026)
  • Posted at: 2026-08-11T10:08:18.000Z
← Back to all tenders