Textile, Garment and Leather
አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት የደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ የግዥ ዘዴ በግዥ መለያ ቁጥር አአከአአድ/ብግጨቁ/002/2019 የደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም በመስኩ የተሰማሩና ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው አቅራቢዎች (ድርጅቶች) ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን፡-
1. በዘርፉ የተሰማራ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ኮፒ (Valid Trade licensee)
2. በመንግስት ግዥ ላይ ለመሳተፍ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመግባቱ በድረ-ገፅ የተመዘገበበት ኮፒ፣
3. የታክስ ከፋይ የምዝገባ ሰርተፍኬት
4. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፊኬት ኮፒ (Vat Certificate)
5. በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የታደሰ ፈቃድ (Valid Tax Clearance Certificate)፣
6. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም የባንከ ጋራንቲ ብር 300,000.00 (ሶስት መቶ ሺህ) በማቅረብ በግልፅ ጨረታ ላይ መወዳደር ይችላሉ።
7. በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ አቅራቢዎች (ድርጅቶች) ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ እስከ ምሳ ሰዓት (6፡00 ሰዓት) የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በጥሬ ገንዘብ በመክፈል በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ 22 እየሩስ ህንጻ ከሚገኘው የድርጅቱ ዋናው መ/ቤት (ማዕከል) የግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 7-02 ወይም 7-01 መውሰድ ይችላሉ።
8. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶክመንት በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦሪጅናል እና ኮፒ በመለየት እስከ ነሐሴ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ በግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 702 ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
9. ጨረታው ነሐሴ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ጠዋት 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 702 ይከፈታል።
ማሳሰቢያ፤ ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር፡ 0116 663 206
አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-08-27
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-08-27 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Addis Ababa City Bus Service Organization
- Bid bond: 300,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 11, 2026)
- Posted at: 2026-08-11T10:24:26.000Z