Cleaning and Janitorial Equipment and Service
የሰሜን ወሎ ዞን ገንዘብ መምሪያ ለራሱና አገልግሎት ለሚሰጣቸው የዞን መምሪያዎችና ተ/ጽ/ቤቶች የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የሰ/ወ/ዞገ/መ/ግ/ጽጨረታ ቁጥር 001
የሰሜን ወሎ ዞን ገንዘብ መምሪያ ለራሱና አገልግሎት ለሚሰጣቸው የዞን መምሪያዎችና ተ/ጽ/ቤቶች፡-
- ሎት 1 የጽ/መሳሪያ
- ሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
- ሎት 3 የመኪና እቃዎች
- ሎት 4 የመኪና ጎማና ባትሪ
- ሎት 5 የጽዳት እቃዎች
- ሎት 6 ፈርኒቸር/የቢሮ መገልገያ እቃዎች/ የውጭ
- ሎት 7 ፈርኒቸር /የቢሮ መገልገያ እቃዎች/የሀገር ውስጥ
- ሎት 8 የተሽከርካሪ የሞተር ዘይትና ቅባት
- ሎት 9 አጠቃላይ ዓመታዊ የህትመት ስራ
- ሎት 10 አጠቃላይ የኤሌክትሮኒክስ ጥገና ስራ
- ሎት 11 የፈርኒቸር (የቋሚ እቃ) ዓመታዊ ጥገና ስራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች ለመሣተፍ የሚከተሉትን መስፈርቶች ሟማላት ይጠበቅባቸዋል
1. የታደሰ ንግድ ፈቃድ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin number/ ያላቸው
3 በአዲሱ የንግድ ፈቃድ አሰራር መሰረት የQR ደረሰኝ ያሳተሙ /ማቅረብ የሚችሉ
4. የሚሞሉት ዋጋ ከ200,000 ሺህ ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
5. ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ማንኛውንም ዕቃ በኦርጅናል መሙላትና ያሽነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ወጭ የማጓጓዣ የማስጫኛ እና ማውረጃ እንዲሁም ወደ እስቶር የማስገባት ወጭዎችን በራሳቸው በመሸፈን በሰሜን ወሎ ዞን ግዥ ንብ/አስተዳደር ቡድን ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የፎቶ ኮፒና የፋከስ ቀለሞች ኦሪጂናል ስለመሆናቸው በሚወስደው ፕሪንተር - ማስሞከር፣ እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን በባለሙያ ማስፈተሽ ይኖርባቸዋል፡፡
6. ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለጸላቸው ከ5 ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት መጥተው ውል መውሰድ እና በውሉ ላይ በተቀመጠው ቀን ገደብ ውስጥ ሁሉንም ያሸነፉትን እቃ ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
7. ተጫራቾች ከሚያቀርቧቸው ሰነዶች ላይ የድርጅታቸውን ማህተም፡ ስምና ፊርማ በሚነበብ መልኩ መፃፍና በየገፁ ማህተም ማድረግና መፈረም ይጠበቅባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ ማንኛውንም የመንግስት ግብር እና ታክስን ያካተተ ዋጋ መሆን አለበት፡፡
8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦሪጅናል እና ኮፒ በማድረግ በየሎቱ በፖስታ አሽገው ማቅረብ እና በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
9 ውድድሩ በድምር ዋጋ /በሎት/ መሆኑ ታውቆ በየሎቱ የተዘረዘሩትን እቃዎች ዋጋ ሁሉንም መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡
10. ከ1 እስከ 11 ላሉት ሎቶች ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ገዝተው መውሰድ ይችላሉ፡፡
11. ሎት 3 /የተሸከርካሪ መለዋወጫ እቃዎች በመምሪያው የተሽከርካሪ እንክብካቤ ባለሙያዎች እና በጋራዥ ባለሙያዎች በጥምር የጥራት አረጋጋጭ ተፈትሾ የሚገባ ስለሆነ በየተሽከርካሪ ሞዴሎቹ ትኩረት ተሰጥቶ ኦርጂናል እቃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
12. ከሎት 9 -11 የህትመት ስራ፣ የኤሌክትሮኒክስ ጥገና እና የፈርኒቸር ጥገና ስራ ተጫራቾች የስራ ድርጅታችሁ በወልድያ ከተማ የተከፈተ ወይም ቅርንጫፍ ያላችሁ መሆን ይጠበቅበታል፡፡
13. ተጫራቾች ከሎት 1- 11 ያሉትን የጨረታ ሰነድ መጫረቻ ሰነድ/ ከ 05/12/2018 እስከ 19/12/2018 ዓ.ም ድረስ በመምጣት ገዝተው መውሰድ ይችላሉ፡፡
14. የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋው በ20/12/18 ዓ.ም ከሎት 1 እስከ ሎት 6 ከጧቱ በ4፡00 ታሽጉ በዚሁ ቀን 4፡30 የሚከፈት ሲሆን ከሎት 7 እስከ ሎት 11 ያሉት ሎቶች ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡30 ላይ ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ በጨረታው ያልተገኙ ተጫራቾች ፖስታቸው በሌሉበት የሚከፈት ሆኖ በግዥ መመሪያው ቁጥር 1/2003 መሰረት ተገዥ የመሆን /የመቀበል/ ግዴታ አለባቸው፡፡
15. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የማብራሪያ ጥያቄ ካላቸው ከጨረታው መክፈቻ ጊዜ ከ5 ቀን በፊት ለመምሪያው ማሳወቅ አለባቸው::
16. የጨረታ ማስከበሪያ ከሎት 1 እስከ ሎት 4 ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ ከሎት 5 እስከ ሎት 8 ብር 30,000.00 /ሰላሳ ሺህ ብር/ ከ ሎት 9 እስከ ሎት 11 ብር 15,000.00 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1/ በመ/ቤቱ የገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ በማስቆረጥ /ኦርጅናሉን/ በጨረታ ፖስታው ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
17. ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃ ሙሉ በሙሉ ሳያስረክቡ ክፍያ ቢጠይቁ መ/ቤቱ አያስተናግድም ሙሉ በሙሉ እንዳስረከቡ ክፍያው ወዲያውኑ ይፈጸማል፡፡
18. የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ ማስረጃና የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም የተሳሳተ ስርዝ ድልዝ/ የጨረታ ሰነድ ማቅረብ ከጨረታ ውጭ ያደርጋል በህግም ያስጠይቃል፡፡
19. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ ፡-
- ተጫራቾች ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 033 331 1597 / 2680 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ::
- ከሎቱ አንድም ሆነ ከአንድ እቃ በላይ ዋጋ ያልሰጠ ተጫራች ካለ ከጨረታ ውድድር ውጭ ያስደርጋል፡፡
- ሳምፕል /ናሙና ታይቶ ዋጋ የሚሞላባቸውን እቃዎች ዝርዝር በዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዡ ላይ በተገለፀው መሰረት የመ/ቤቱን ሳምፕል በማየት ዋጋ ሊሞላ ይገባል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ግልጽ ያልሆነለትን ነገር ደውሎ ግልጽ ካልሆነለት በስተቀር ያለ አግባቡ ዋጋ መሙላት የለበትም፡፡
- በኋላ ለሚያቀርበው ጥያቄ ተቋሙ የማይቀበልና የተቋሙ ሃሳብ ተቀባይነት ያለው መሆኑን እናሳስባለን::
የሰሜን ወሎ ዞን ገንዘብ መምሪያ
Tender details
- Deadline: 2026-08-26
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-08-26 14:30
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ሰዓት በየሎቱ የተለያየ ነው
- Region: Amhara
- Publishing entity: North Wollo Zone Finance Department
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 11, 2026)
- Posted at: 2026-08-11T10:44:17.000Z