Textile, Garments and Uniforms
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በጅማ ዞን የሠቃ ጨቆርሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የሰራተኞች የደንብ ልብስ፣ የጽ/ቤት አላቂ ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የተሽከርካሪ ጎማዎችን እና የሁለት እግር የሞተር ሳይክሎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Textile, Garments and UniformsTextile, Garment and LeatherShoes and Other Leather Products
Oromia
More tags
StationeryOffice Supplies and ServicesEquipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsComputer and AccessoriesIT and TelecomOffice Machines and AccessoriesSpare Parts and Car Decoration MaterialsTri Wheeler, Motorcycles and Bicycles PurchaseCleaning and Janitorial Equipment and ServiceAmharic2merkatoJimma Zone Seka Chekorsa Woreda Finance and Economic Development Bureau
Description
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በጅማ ዞን የሠቃ ጨቆርሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 ዓ.ም በወረዳው ውስጥ ላሉ ባለበጀት መስሪያ ቤቶች የሚያገለግሉ የጥራት ደረጃቸው በኢትዮጵያ ደረጃ መዳቢዎች የተረጋገጠ የምስክር ወረቀት ያላቸው በቅርብ አመታት ውስጥ የተመረቱ
- ዕቃዎችን የሰራተኞች የደንብ ልብስ፤
- የጽ/ቤት አላቂ ዕቃዎች ፣
- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ፤
- የተሽከርካሪ ጎማዎችን እና
- የሁለት እግር የሞተር ሳይክሎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት ማናቸውም በንግድ ስራ ዘርፍ የተሰማሩ ህጋዊ የስራ ፍቃድ ያላቸው ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የሚያሟሉ እንዲወዳደሩ እንጋብዛለን።
- ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የንግድ ፍቃዳቸውን ያሳደሱ የዘመኑን ግብር የከፈሉና ዋናና ቅጂ በንግድ ፍቃዳቸውን ያሳደሱ የዘመኑን ግብር የከፈሉና ዋናና ቅጂ መረጃ አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ።
- ተወዳዳሪዎች በአቅራቢዎች ዝርዝር ላይ የተመዘገቡበትን መረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተወዳዳሪዎች ተጨማሪ እሴት ታክስ ( ቫት) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰረተ ቼክ CPO 50,000 (ሀምሳ ሺህ ብር ) በታሸገ ፓስታ ማቅረብ የሚችሉ።
- ጠቅላላ ተወዳዳሪዎች በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትና የፌደራል መንግስት የተደነገገውን የግዥ ሕግ የሚያከብሩ መሆን አለባቸው።
- በኢትዮጵያ ደረጃ መዳቢዎች የተረጋገጠ ዕቃ ስለመሆኑ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነድ ከተከፈተ በኋላ በሰነዱ ላይ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ መለወጥ ማሻሻያ ማድረግ ወይም ከጨረታ መወጣት አይችሉም።
- ተወዳዳሪዎች በጨረታው ላይ መግለጫ ወይም የማሻሻያ ጥያቄ ካላቸው በተመዘገቡ በአምስት ቀን (5) ውስጥ ማቅረብ ይችላሉ።
- ተወዳዳሪዎች ባቀረቡት መወዳደሪያ ሰነድ ላይ ስም ፤ ፊርማ የድርጅቱ ማህተም እና አድራሻ መጥቀስ አለባቸው።
- የጨረታውን ሰነድ በሠቃ ጨቆርሳ ወረዳ ገንዘብና ጽ/ቤት ቁጥር 7 የማይመለስ 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይቻላል።
- ተወዳዳሪዎች ጨረታውን ለማሰናከል ከሞከሩ ከጨረታ ውጭ ይሆናሉ ለወደፊትም በሠቃ ጨቆርሳ ወረዳ በሚካሄደው በመንግስት የግዥ ጨረታ አይሳተፉም:: ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብም አይመለስም።
- ይህ ጨረታ ለ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የመንግስት የስራ ቀን በአየር ላይ የሚውል ይሆናል በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ።
- የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈን ዕቃ በራሱ ትራንስፓርት አጓጉዞ እስከ ጽ/ቤቱ ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
- መስሪያ ቤቱ እንደአስፈላጊነቱ 20% ጨምሮ ወይም ቀንሶ መግዛት ይችላል፣
- የተሰረዘ የተደለዘ የተፋፋቀ ወይም በግልፅ የማይነበብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረም።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ዋጋ መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ በመሙላት ማቅረብ ይኖርበታል።
- የጨረታው ሰነድ አቅራቢ ድርጅቶች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛ የመንግስት የስራ ቀን 4:00 ሰዓት ታሽጎ በቀኑ 8:00 ሰዓት ላይ ይከፈታል።
- በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ መስፈርቶች በዋና የጨረታ ሰነድ ላይ ያሉ መሆናቸውን እንገልፃለን።
- የቴክኒክ እና ፋይናንሻል ሰነዶች ኦርጅናል እና ኮፒ በተለያየ ፓስታዎች በማሸግ በአንድ ጥቅል እሽግ መቅረብ ይኖርበታል።
- ግዥ የሚፈጽመው አካል የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በጥቅል የመሰረዝ መብት አለው።
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በጅማዞን የሠቃ
ጨቆርሳ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-28
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛ የመንግስት የስራ ቀን 4:00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-28 14:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛ የመንግስት የስራ ቀን 8:00 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: Jimma Zone Seka Chekorsa Woreda Finance and Economic Development Bureau
- Bid bond: 50,000 ብር
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 11, 2026)
- Posted at: 2026-08-11T11:06:02.000Z