Construction Machinery and Equipment

የትመን ጅፕሰምና የጅፕሰም ውጤቶች ማምረቻና መሸጫ ኃላ.የተ.የግ.ማህበር የኤክስካቫተር ማሽን ኪራይ በጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል

Description

የኤክስካቫተር ማሽን ኪራይ ግዥ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

ድርጅታችን የትመን ጅፕሰምና የጅፕሰም ውጤቶች ማምረቻና መሸጫ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን በደጀን ከተማ የሚገኝ ጅፕሰምና የጅፕሰም ውጤቶችን ማምረቻ ፋብሪካ ሲሆን ፋብሪካው ለጅፕሰም ውጤቶች ሚሆን የጅፕሰም ድንጋይ ጥሬ እቃ ኩራር ቀበሌ ተብሎ ከሚጠራው የኩባንያው ኳሪ ሳይት ለማምረት፤ የኤክስካቫተር ማሽን በጃክ ሃመር እና በአካፋ በሰዓት ለማሰራት በጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት፡-

1.በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ድርጅት በጨረታው የመሳተፍ መብቱ የተጠበቀ ነው።

2. ጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ኩባንያው ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ጥያቄ ማመልከቻ ፎርም መሰረት ፈርሞ መጠየቅ አለበት።

3. በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ሰነድ ይሸጥልኝ ጥያቄ ፎርም ላይ ሞልቶ ያመለከተው ተጫራች ከመንግስት የንግድ ስራ ፈቀድ አውጥቶ በማንኛውም አይነት የንግድ ስራ መስክ የተሰማራ ድርጅት፣ ማህበራትና ሌሎች ተቋማት ከሆነ የዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ ቲን ናምበር፣ ቫት ተመዝጋቢ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት ከማመልከቻው ጋር አያይዞ ማቅረብ አለበት።

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና/ ቢድ ቦንድ/ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 10% /አንድ በመቶ/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ለድርጅቱ ገቢ ማድረግ አለባቸው።

5. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የኤክስካቫተር ማሽነሪ ከነቫቱ በሰዓት በአካፋ እና በጃክ ሀመር በምን ያህል ዋጋ እንደሚያከራዩ በግልፅ መሙላት አለባቸው።

6. ተጫራቾች ለመጫራት የሚያቀርቡት ማሽን የስሪት ዘመን የ2024 እ.አ.አ እና በኋላ የተመረተ የተሰራ/ ከዚህም በተጨማሪ ዝቅተኛ የፈረስ ጉልበቱ 360HP መሆን አለበት

7. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ማሽነሪ ዓይነት፣ የስሪት ዘመን፣ ማሽነሪው ከዚህ በፊት የሰራውን የሰዓት መጠን እና ሞዴል ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፍኬሽን/ በዋጋ መሙያው ላይ ማስፈር አለባቸው።

8. ተጫራቾች የሞሉትን የጨረታ ሠነድ በጥንቃቄ በማሸግ የግዥ ፈፃሚ ድርጅቱ፣ የተጫራቹን ስም፣ አድራሻ በመፃፍ በማህተምና ፊርማ አስደግፎ ለግዥ ፈፃሚው ድርጅት ሰነዱን መመለስ ይኖርባቸዋል።

9. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን አዘጋጅተው ሲያቀርቡ አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ በተለያየ ፖስታ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ በአስተሻሸግ ችግር ምክንያት ለሚከሰት ማንኛውም አይነት የሰነድ መጥፋት ተከራይ ተጠያቂ አይሆንም።

10. ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነዱን የትመንጅፕሰም ቁጥር 02 ፋብሪካ ከጨረታ ኮሚቴው ቢሮ ቁጥር 04 የማይመለስ ብር በ200.00 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በአካል ወይም በድርጅቱ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 100357178658 በመክፈልና የተከፈለበትን የባንክ ማስረጃ በመያዝ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

11. ጨረታው አየር ላይ የሚቆየው በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ብቻ ሲሆን፤ ለስራ ቀን አቆጣጠር ሲባል ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡00 ያለው ጊዜ የተከራይ የስራ ቀን ስለሆነ እንደ አንድ ሙሉ የስራ ቀን ይቆጠራል።  በ15ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በቀጣይ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 በኩባንያው ቁጥር 02 ፋብሪካ ቢሮ ቁጥር 01 የጨረታ መከፈት ስነ- ስርዓቱን መከታተል የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፣

12.ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ወይም ዝግ ከሆነ ሰዓቱ እንደተጠበቀ ሆኖ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል።

13. አሸናፊው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከ1 የስራ ቀን በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ በማስያዝ ውል ይዞ አገልግሎቱን መስጠት መጀመር አለበት።

14. ተጫራቹ አሸናፊ ሆኖ ውል አልይዝም ካለ ያስያዘው የጠቅላላ ዋጋ 10% CPO ለኩባንያው ገቢ ይሆናል።

15. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

16. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09-11-60-15-75 / 09-12-38-72 97 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፤

የትመን ጅፕሰምና የጅፕሰም ውጤቶች ማምረቻና መሸጫ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር


Tender details

  • Deadline: 2026-08-27
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ጨረታው አየር ላይ የሚቆየው በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በ15ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-28 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው አየር ላይ የሚቆየው በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ብቻ ሲሆን በቀጣይ ቀን ከጠዋቱ 4፡00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Yetmen Gypsum and Gypsum Products Production Plc
  • Bid bond: 10% /አንድ በመቶ/
  • Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 11, 2026)
  • Posted at: 2026-08-11T11:08:27.000Z
← Back to all tenders