Stationery
በአብክመ ሰሜን ሸዋ ዞን የደብረሲና ከተማ አስተዳደር ገንዘብ/ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎች ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል
Description
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ግዥ/ንብ/አስ/001/2019
በአብክመ ሰሜን ሸዋ ዞን የደብረሲና ከተማ አስተዳደር ገንዘብ/ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት በከተማዉ ዉስጥ ላሉ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች በየሎቱ የተጠቀሱትን እቃዎች ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል።
- ሎት1. የተለያዩ አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች እና አነስተኛ የቢሮ እቃዎች ግዥ ሎት2
- ሎት3. የተለያዩ የጽዳት እቃዎች ግዥ
- ሎት4. የተለያዩ ኮምፒውተርና ተዛማጅ እቃዎች
- ሎት5. የተለያዩ የቢሮ ፈርኒቸር
ስለዚህ፡-
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዝርዝር ጉዳይ የያዘ የእያንዳዱን የጨረታ ሰነድ ከሎት 1 እስከ ሎት 5 የማይመለስ በብር 500.00 ብር ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ብቻ ዘወትር በስራ ሰዓት ደ/ሲና ከተማ አስተዳደር ገንዘብ/ፅ/ቤት ቀርበው በመግዛት መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች ከሎት1 እስከ ሎት5 ያሉትን ሰነዶች በእያንዳንዱ የዋጋ ዝርዝር ማቅረቢያ ሰንጠረዥ ውስጥነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋውን ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በጥንቃቄ በመሙላት የድርጅቱን ማህተም፤ ስም፤ ፊርማ እና አድራሻ ስልክ ቁጥር በማስፈር ኦርጅናል የመጫረቻ ሰነድ በፖስታ አሽገው ደ/ሲና ከተማ አስተዳደር/ገንዘብ/ፅ/ቤት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባትይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ከሎት 1 እስከ ሎት 5 ያሉትን ሰነዶች በእያንዳንዱ የዋጋ ዝርዝር ማቅረቢያ ሰንጠረዥ ውስጥ ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋውን ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በጥንቃቄ በመሙላት የድርጅቱን ማህተም፤ ስም፤ ፊርማ እና አድራሻ ስልክ ቁጥር በማስፈር ኦርጅናል የመጫረቻ ሰነድ በፖስታ አሽገው የጨረታ ሳጥኑ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት በ16ተኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ይታሸጋል፡፡ በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮች በተገኙበት ወይም ባልተገኙበት ከጠዋቱ 4:45 ሰዓት ጀምሮ ደብረሲና ከተማ አስተዳደር/ገንዘብ/ፅ/ቤት ይከፈታል፡፡ቀኖቹ ቅዳሜና እሁድ ወይም በዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ይታሸግና 4፡45 ይከፈታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው ከታወቁ ባንኮች የሚሰጥ እንደ ተጫራቾች ምርጫ ሲ.ፒ.ኦ/CPO/ ወይንም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ለመስሪያ ቤቱ ዋና ገንዘብ ያዥ በመሂı በጥሬ ገንዘብ በምትወዳደሩበት ዘርፍ(ሎት)2% ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማሽግ ማስያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡
- ተ.ቁ 4 ላይ የተገለፀውን የጨረታ ማስከበሪያ ያላሟላ ተጫራች ከውድድር ውጪ ይሆናል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ ማብራሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ከተያዘው የተጫራቾች መመሪያ በማንበብ መረዳት ይችላሉ።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር0116801206 ደውለው ይጠይቁ።
በአብክመ ሰሜን ሸዋ ዞን የደብረሲና ከተማ
አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-26
- Bid closing time: 10:30
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ተኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-26 10:45
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ተኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡45 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: Debre Sina City Administration Finance & Economic Cooperative Bureau
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 500.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Published on: Addis Zemen (Aug 11, 2026)
- Posted at: 2026-08-11T12:22:28.000Z