Spare Parts and Car Decoration Materials
የኦሮሚያ መሬት ቢሮ የመኪና ጎማዎች ከህጋዊ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የኦሮሚያ መሬት ቢሮ ቁጥር NCB/2/2019 ለመስሪያ ቤቱ የመኪና ጎማዎች ከህጋዊ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መሥፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
- ድርጅቶች የዘመኑን ግብር የከፈሉና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና ከመጋዝን (stoke) ውስጥ ጎማውን ማቅረብ የሚችል መሆን ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር / TIN NO/ ያላቸው መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ/ በመክፈል በኦሮሚያ መሬት ቢሮ 3ኛ ፎቅ ፋይናንስ ክፍል መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ በCPO ብቻ ለመወዳደር 300,000 (ሶስት በመቶ ብር ብቻ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የእቃዎቹን የዋጋ ዝርዝር በጨረታ ማወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ስማቸውን፤ ፊርማቸውንና አድራሻቸውን በማስፈርና ማህተም በማድረግ የጨረታ ዶክመንቶችን የራሳቸውን የፋይናንሻል ኦርጅናልና ኮፒውን እና የጎማዉ የቴክኒካል ኦርጅናልና ኮፒውን ዶክመንቱን በተለያየ ከCPO ጋር በአምስት (5) በታሸገ ኤንቨሎፕ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል።
- የጨረታ ሣጥኑ ከታሸገ ወይም ከተከፈተ በኋላ የሚቀርብ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
- የጨረታው አሸናፊ አካል በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ ዕቃውን ጨርሶ ማስረከብ የሚችል። መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ በዚህ ስልክ ቁጥር መጠቀም ይችላሉ /09 49 44 57 29/ 09 10 62 27 00/ 09 19 51 99 51/ 09 46 65 33 04
አድራሻ ፡- ሳርቤት አደባባይን ዞሮ ወደ ቄራ መሄጃ ዋናው አስፋልት 200 ሜትር ላይ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስሪያ ቤቶች ቅጥር ግቢ ውስጥ
የኦሮሚያ መሬት ቢሮ
Tender details
- Deadline: 2026-08-26
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-08-26 14:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Oromia Land Bureau
- Buyer address: ሳርቤት አደባባይን ዞሮ ወደ ቄራ መሄጃ ከዋናው አስፋልት 200 ሜትር የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስሪያ ቤቶች ቅጥር ግቢ ውስጥ
- Bid bond: 300,000 (ሶስት በመቶ ብር ብቻ)
- Bid document price: 100 (አንድ መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Aug 11, 2026)
- Posted at: 2026-08-11T12:45:11.000Z