Textile, Garments and Uniforms

የበቾ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የተለያዩ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የግዢ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር በ/ወ/ገ/ጽ/01/2019

የበቾ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 ዓ/ም ለወረዳው መንግሥት መ/ቤቶች ከዚህ በታች በሰንጠረዥ በሎት የተከፋፈሉትን ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ሎት 1

 

ሎት 2

 

ሎት 3

 

ሎት 4

 

ሎት 5

 

ሎት 6

 

የደንብ ልብስ፣ ፍራሽና አልጋ

 

የጽህፈት መሳሪያና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች

 

የጽዳት ዕቃዎች፣ አነስተኛ ዕቃዎችና መሳሪያዎች

 

የመኪና ጎማ፣ የተሽርካሪዎች መለዋወጫ፣ የመብራት ዕቃዎች የበር ቁልፎች

ኤሌክትሮኒክስ፣ ቋሚ፣ የቢሮ ዕቃዎች፣ ምንጣፎች፣ መጋረጃዎች

 

ሞተር ብስክሌት

 

ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የሚያሟሉ አቅራቢዎች የጨረታ ሰነዱን ገዝተው እንዲወዳደሩ እናስታውቃለን።

1. የታደሠ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

2. በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና ለዚህም የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የቲን(T) እና የቫት (VAT) ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሁሉም ሎት አንድ ላይ ብር 60,000 (ስልሳ ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሠነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

4. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የዕቃ ዋጋ ላይ የመንግሥትን ታክስ አካተው (ደምረውበት) ማቅረብ አለባቸው። በጨረታ ሰነድ ላይ የመንግሥት ታክስ መካተቱ (መደመሩ) ካልተገለጸ የቀረበው የጨረታ ሰነድ የመንግሥትን ታክስ እንደተካተተበት ተሰልቶ ይሰራል።

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ዋጋ ከሎት 1 እስከ ሎት 6 የሰውን እያንዳንዳቸው በብር 100(መቶ) በመስላት በበቾ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000036818909 በተከፈው ሂሳብ ገቢ በማድረግና ገቢ የተደረገበትን ደረሰኝ በማቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፣

6. የጨረታ ሠነድ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የሥራ ቀናትና በሥራ ሰዓት በቱሉ ቦሎ ከተማ በበቾ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የቢሮ ቁጥር 3 እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ።

7. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒውን ሠነድ ለየብቻቸው በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ከላይ በተራ ቁጥር 6 በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ጨረታው ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው የሥራ ቀን 6፡00 ሠዓት ድረስ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።

8. ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ16ኛው የሥራ ቀን፣ ከቀኑ በ8፡00 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በበቾ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 ይከፈታል። ዕለቱ የበዓል ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ላይ ይከፈታል።

9. ከተገለጸው ሰዓት ውጪ የቀረበው የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።

10. ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ያሸነፈበትን ዕቃ በራሱ ማጓጓዣ (ወጪ) በቾ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ _ ቤት ዕቃ ግምጃ ቤት አምጥቶ ማስረከብ ይኖርበታል።

11. በጨረታ ማስታወቂያና በግዢ ጨረታ መመሪያ ላይ የተፃፉ መስፈርቶች የሚለያዩ ከሆነ በግዢ ጨረታ መመሪያ ላይ የተፃፉ መስፈርቶች ተቀባይነት ይኖራቸዋል።

12. የጥቃቅንና አነስተኛ ማይክሮ ኢንተርፕራይዝ ለውድድር የሚቀርቡት የዘመኑን ሒሣብ (የ2018 ዓ.ም)ኦዲት አስደርገው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና ከዚህ በፊት ለሰሩት ስራ መልካም ስምና ተግባር ስለመኖራቸው ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

13. ተወዳዳሪው በራሱ ስም የተከፈተውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና የሲንቄ ባንክ ሂሳብ ቁጥር ለብቻ ጽፈው ከግዢ ሰነድ (ከመወዳደሪያ ሀሳብ) ጋር ማስገባት ይኖርበታል።

14. መ/ቤቱ ከዚህ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

15. ማሳሰቢያ፡-ውድድሩ የሚካሄደው በሎት ሳይሆን ለእያንዳንዱ ዕቃ ነጠላ ዋጋ በተሞለው ዋጋ  መሠረት ነው።

አድራሻ፡- በጅማ መሥመር ከአ.አ 80 ኪ.ሜ. ላይ ቱሉቦሎ ከተማ መናኸሪያ አከባቢ እንገኛለን።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011 342 1080/ 09 23 71 18 97/ 09 13 30 75 62/ ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የበቾ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
ቱሉቦሎ


Tender details

  • Deadline: 2026-08-28
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው የሥራ ቀን 6፡00 ሠዓት
  • Bid opening: 2026-08-28 14:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው የሥራ ቀን 8፡00 ሠዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Becho Woreda Finance and Economic Development Bureau
  • Bid bond: ለሁሉም ሎት አንድ ላይ ብር 60,000 (ስልሳ ሺህ)
  • Bid document price: ለእያንዳንዱ 100 (አንድ መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 11, 2026)
  • Posted at: 2026-08-11T12:57:26.000Z
← Back to all tenders