Laboratory Equipment and Chemicals

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ሥር የሚገኘው የወረዳ 9 ኳስ ሜዳ ጤና ጣቢያ የህክምና መድሀኒቶችና የላብራቶሪ ሪኤጀንት፣ አላቂ የፅህፈት መሣሪያ፣ ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣ የደንብ ልብስ ጨርቆች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ ቋሚ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች፣ ህትመት፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ጥገናና ሰርቪስ፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ የተለያዩ ክፍሎች የጥገናና እድሳት ስራ በ2019 ዓ.ም. የበጀት ዓመት ግዥ

Description

ግልፅ የጨረታ  ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር 001/2019 ዓ.ም.

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ሥር የሚገኘው የወረዳ 9 ኳስ ሜዳ ጤና ጣቢያ በ2019ዓ/ም የበጀት ዓመት የሚያስፈልጉትን እቃዎችና አቅርቦቶች ማለትም

  • የህክምና መድሀኒቶችና የላብራቶሪ ሪኤጀንት፣
  • አላቂ የፅህፈት መሣሪያ፣
  • ቋሚ የቢሮ እቃዎች የደንብ ልብስ ጨርቆች ፣
  • የፅዳት ዕቃዎች ቋሚ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች፤
  • ህትመት፣
  • የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ 
  • ጥገናና ሰርቪስ፣
  • አላቂ የቢሮ እቃዎች፣
  • የተለያዩ ክፍሎች የጥገናና እድሳት ስራ በ2019 ዓ.ም የበጀት ዓመት ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል።

 ስለሆነም ይህንን የጨረታ ማስታወቂያ አጥቷል።

በመሆኑም በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ ላይ መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች አሟልቶ በጨረታው መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

  1. በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን የሀገር ውስጥ ገቢ ግብር አጠናቀው የከፈሉ።
  2. የንግድ ምዝገባ ፈቃድ ወይም ሰርተፍኬት ያላቸው።
  3. ንግድ ፈቃዳቸው በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በእቅራቢነት የተመዘገበና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም በዌብሳይት የሚረጋገጥ።
  4. የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸዉ።
  5. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት ተመዝጋቢ) መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት (ሰርተፍኬት) ማቅረብ የሚችሉና የሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ ከቫት ጋር የተሰላ /ተጨማሪ አሴት ታክስን ያካተተ መሆን አለበት።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያውን በባንክ በተረጋገጠ (በተመሰከረለት) ሲፒኦ (CPO) ከጨረታው ፖስታ ጋር በየግዥ መደቡ (በየሎቱ )ለየብቻ በማሽን አብረው ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  • ማንኛውም ተጫራች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200.00 / ሁለት መቶ/ ብር ብቻ በመክፈል በወረዳ 9 ኳስ ሜዳ ጤና ጣቢያ በግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ በኩል በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  • ተጫራቾች ሰነዱን ከገዙ በኋላ የሚወዳደሩበትን ዋጋ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማህተምና ፊርማ በማድረግ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ሰነዶችን ለየብቻ በማድረግ ማስታወቂያው ለመጀመሪያ ጊዜ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከላይ በተጠቀሰው ቢሮ በመገኘት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  • ለተጫራቾች ጨረታው እንደተጠናቀቀ ተመላሽ የሚደረግ የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ።

ሎት 1. መድሀኒቶችና የላብራቶሪ ሪኤጀንቶች

22, 500(0.5) (ሃያ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር)

ሎት 2. አላቂ የዕህፈት መሳሪያዎች

10,000(0.5) (አስር ሺህ ብር)

ሎት 3. ቋሚ  የቢሮ እቃዎች

15,000(0.5) (አስራ አምስት ሺህ ብር)

ሎት 4. የደንብ ልብስ

15,000(0.5) (አስራ አምስት ሺህ ብር)

ሎት 5. አላቂ የፅዳት ዕቃዎች

12.500(0.5) (አስራ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር)

ሎት 6. ቋሚና አላቂ የህክምና መገልገያመሳሪያዎች

10,500(0. 7) (አስር ሺህ አምስት መቶ ብር)

ሎት 7. ህትመቶች

6,000(0.8) (ስድስት ሺህ ብር)

ሎት 8. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገናና ስርቪስ

2,100(0.7) (ሁለት ሺህ አንድ መቶ ብር)

ሎት 9. አላቂ የቢሮ ዕቃዎች

13,500(0.9) (አስራ ሶስት ሺህ አምስት መቶ ብር)

ሎት 10. የተለያዩ ክፍሎች የጥገናና እድሳት ስራ

6,000(0.5) (ስድስት ሺህ ብር ብቻ)

7. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ 11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ታዛቢዎችና ወኪሎች ባሉበት የጨረታ መቀበያ ጊዜ ያበቃ መሆኑን የሚገልፅ ቃለ-ጉባኤ በመያዝ ታሽጎ በዛው ዕለትና ሰዓት 4:30 ላይ የመክፈቻ ቃለ-ጉባኤ ተይዞ ሲታሸግ የነበሩ ታዛቢዎችና ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል። በዚህ ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲገኙ ይጋበዛሉ፤ ባይገኙ ግን የጨረታ መዝጊያም ሆነ የመክፈቻ ቀኑም ሆነ ሰዓቱ የማይራዘም መሆኑን እናሳስባለን።

8. አሸናፊ ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ የውሉን ዋጋ 10% (አሥር በመቶ) በውል ማስከበሪያነት ለመንግስት መስሪያ ቤቱ ማስያዝ አለባቸው።

9. ተጫራቾች ለሚያቀርቧቸው ዕቃዎች በጥራት ደረጃ አስተማማኝነቱን የጠበቀ ናሙና ከጨረታው በፊት ማቅረብ አለባቸው።

10. ማንኛውም የጥቃቅን ተጫራች ካደራጃቸው አካል አምራች መሆናቸውን የሚገልፅ ህጋዊ ደብዳቤ ወይም ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ ሙቡቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥራችን 1-011-275-0975 ሊያገኙን ይችላሉ።

አድራሻ፡-በአዲስ ከተማ ክፍስ ከተማ አስተዳደር መማሰሚያ ወዴ ኮልፌ አጠና ተራ

በሚወስደው መንገድ ከበለስ ሆቴል ፊት ለፊት ወይም ከባስሶር ህንፃ በስተጀርባ በኩል

የወረዳ 9 ኳስ ሜዳ ጤና ጣቢያ

አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-24
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ 11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-24 10:30
  • Bid opening (note): ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ 11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ababa Sub City Health Office Woreda 9 kuas Meda Health Center
  • Buyer address: አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ መሳለሚያ ወደአጠና ተራ በሚወስደው መንገድ በለስ ሆቴል ፊት ለፊት ወይም ባለሶራው ሕንፃ በስተጀርባ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 12, 2026)
  • Posted at: 2026-08-12T10:19:32.000Z
← Back to all tenders