House and Building Foreclosure
ፀደይ ባንክ አ.ማ. ስፋቱ 240 ካ.ሜ. የሆነ የመኖሪያ ቤትና ቦታ በግልጽ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
ፀደይ ባንክ አማ ደ/ማርቆስ ዲስትሪክት
የሀራጅ ጨረቃ ማስታወቂያ
ጸደይ ባንክ አ.ማ. ለአቶ ማረልኝ ባለው የሰጠው ብድር ባለመመለሱ ባንኩ በዋስትና /በመያዣ/ የያዘው በሞጣ ከተማ ቀበሌ 05 በካርታ ቁጥር 3374/2012 ተመዝግቦ የሚገኝ ስፋቱ 240 ካ/ሜ የሆነ የመኖሪያ ቤትና ቦታ በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልጽ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች በጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የቤቱን የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/4ኛ በጥሬ ገንዘብ ወይም ሲፒኦ በጸደይ ባንክ ስም ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
- የቤቱ ጨረታ መነሻ ዋጋው ብር 400,723.88 / አራት መቶ ሺ ሰባት መቶ ሃያ ሶስት ብር ከሰማኒያ ስምንት ሳንቲም / ነው
- በጨረታ የሚሳተፈው በህግ ሰውነት ያገኘ ድርጅት ከሆነ የድርጅቱን የጸደቀ የመመስረቻ ጽሁፍ እና መተዳደሪያ ደንብ ህጋዊ ሰውነት ያገኘበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሁም ህጋዊ ውክልና ማቅረብ አለበት።
- የጨረታ አሸናፊው አሸናፊነቱ የሚረጋገጠው የጨረታው ውጤት በሚመለከተው አካል ጸድቆ በባንኩ ደብዳቤ ሲሰጠው ይሆናል።
- የጨረታ አሸናፊው ያሸነፈበትን ቀሪውን ገንዘብ በ15 ቀን ውስጥ ለባንኩ በመክፈል ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል። በዚህ ቀን ውስጥ ካልከፈለ ግን ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ¼ ኛ ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል።
- በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ ፒ ኦ ይመለስላቸዋል።
- የጨረታ አሸናፊው ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያየዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፣ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውም ወጭዎችን ይከፍላሉ። ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ለቀሪው የሊዝ ክፍያ ገዥው ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ይዋዋላል።
- ተጫራቾች ቤቱን በባንኩ አማካኝነት መጎብኘት ወይም ማየት ይችላሉ።
- ጨረታው የሚካሄደው በሞጣ ከተማ ቀበሌ 05 ለጨረታ በወጣው ንብረት ግቢ ውስጥ ነው።
- ጨረታው የሚካሄደው መስከረም 10 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ይሆናል።
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 21 66 71 15/ 09 12 43 68 68 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።
ስልክ 058 771 2034
ፖ.ስ.ታ 341
ፋክስ 058 771 6667
ቁጠባችን ለነገ ዋስትናችን
Tender details
- Deadline: 2026-09-20
- Bid closing time: 12:00
- Bid opening: 2026-09-20 12:00
- Region: Amhara
- Publishing entity: Tsedey Bank S.C.
- Buyer address: Legahar Orda Building, 8th Floor room No-804
- Bid bond: 25%
- Published on: Reporter (Aug 12, 2026)
- Posted at: 2026-08-12T14:21:42.000Z