Textile, Garment and Leather

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በምዕራብ አርሲ ዞን የኮኮሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በሥሩ ለሚኘት ባለበጀት መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዓይነት ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድረው ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር፦ B_6/941/2018

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በምዕራብ አርሲ ዞን የኮኮሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በሥሩ ለሚኘት ባለበጀት መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዓይነት ያላቸውን ዕቃዎች በ2019 የበጀት ዓመት ውስጥ በዘርፉ ከተሰማሩትና ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ካላቸው አቅራቢ ድርጅቶች ላይ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድረው ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሠረት

  • የሰራተኞች የደንብ ልብስና ጫማዎችን
  • የተለያዩ የግንባታ ዕቃዎችን
  • የጽህፈት መሳሪያዎችንና ሌሎች አላቂ የቢሮ ዕቃዎችን
  • የጽዳት ዕቃዎችን
  • የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን
  • የውጭ ሀገር ፈርኒቸሮችን
  • የመኪናና የሞተር ሳይክሎችን ጎማ ከነከማዳርያቸው 
  • ሞተር ሳይክሎችን እና
  • የተለያዩ የቴክኒክና ሙያ ት/ት ሥልጠና መመሪያዎችን - በዘርፉ የተሰማሩትና ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ካላቸው አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተለውን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉና በሥራ ዘርፍ የተሰማሩ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።

1. ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የ 2019 ዓ.ም የመንግሥት ግብር የከፈሉ

2. የአቅራቢነት ምዝገባ የምሥስክር ወረቀት ያላቸው።

3. የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት (ቲን ነምበር) ያላቸው

4 የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው።

5. ያሸነፉባትን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት በምዕራብ አርሲ ዞን ኮኮሳ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ የሚችሉ።

6. ጥራታቸው የተጠበቀ ዕቃዎችን ማቅረብ የሚችሉና ጥራት የሌላቸውን ዕቃዎች ለመቀየር ፈቃደኛ የምትሆኑ

7. መ/ቤታችን ለአሸናፊዎችና አቅራቢ ድርጅቶች ከሚከፍላቸው ክፍያ 15% ቫት ላይ 7.5% እና ዊዝ ሆልዲንግ 3% አጠቃላይ 10.5 % ቀንሶ የሚያስቀር መሆኑን የሚረዱ

8. የማስጫኛና ማውረጃ ወጪ ራሳቸው የሚችሉ።

9. ለጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ጨረታ ሰነድ በባንክ በተመሰከረለት በሲፒኦ 30,000.00 /ሰላሳ ሺህ ብር/ ማስያዝ የሚችሉ

10 ተጫራቾች ለእያንዳንዳቸው የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር / በኮኮሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሂሳብ ቁጥር 1000095337701 ገቢ በማድረግ የጨረታውን ሰነድ በ07/12/2018 ዓ.ም እስከ 28/12/2018 ዓ.ም እስከ 11፡30 ሰዓት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከኮኮሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥ ንብረት አስተዳደር ማስወገድና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ቁጥር 07 የከፈሉበትን ደረሰኝ ይዘው በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

11. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ላይ የእያንዳንዱን እቃ ዋጋ በድርጅታቸሁ ዋጋ ማቅረቢያ ላይ በመሙላት በሰም በታሸጉ ኤንቨሎፕ በማድረግ እስከ 28/12/2018 ዓ.ም 11፡30 ሰዓት ድረስ በምዕራብ አርሲ ዞን ኮኮሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

12. ጨረታው 29/12/2018 ዓ.ም በ3፡00 ሰዓት ተዘግተው በዚሁ እለት 03፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በምዕራብ አርሲ ዞን ኮኮሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 07 ውስጥ ይከፈታል። እለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ጨረታው የሚከፈት ይሆናል።

13. ለተጨማሪ መረጃ በሞባይል ቁጥሮች፡- 09 11 31 85 42/ 09 10 17 27 95/ 09 10 28 09 19 በመደወል መጠየቅና መረዳት ይችላሉ።

14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የኮኮሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

ኮኮሳ


Tender details

  • Deadline: 2026-09-04
  • Bid closing time: 09:00
  • Bid opening: 2026-09-04 09:30
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Kokosa Woreda F/E/D/Bureau
  • Bid bond: 30,000.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ
  • Published on: Addis Zemen (Aug 13, 2026)
  • Posted at: 2026-08-13T07:51:04.000Z
← Back to all tenders