Spare Parts and Car Decoration Materials

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሲዳማ ሪጅን ስር ለሚያገለግሉ ተሽከርካሪዎች የጎማ ግዥ ለመፈፀም በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር ኢ/ኤ/አ/ሲ/ሪ/ግ/ጨ/002/2019

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሲዳማ ሪጅን ስር ለሚያገለግሉ ተሽከርካሪዎች የጎማ ግዥ ለመፈፀም በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ዝርዝሩም እንደሚከተለው ነው፡-

/

የጎማው አይነት

መለኪያ

ብዛት

አስተያየት

1

12/20 ባለ ሽቦ ፍላፕ ከነ ከመነዳሪው

በቁጥር

46

ቀጭን ጥርስ 8 የፊት ወፍራም ጥርስ 38 የኃላ

2

7.50*16 ባለ 16 PR ፍላፕ ከነ ከመነዳሪው

በቁጥር

70

 

3

7.50*16 ባለ 14 PR ፍላፕ ከነ ከመነዳሪው

በቁጥር

65

 

4

225/70 R17 ፍላፕ ከነ ከመነዳሪው

በቁጥር

5

 

5

265/65 R17 ፍላፕ ከነ ከመነዳሪው

በቁጥር

5

 

6

185/70 R14 ፍላፕ ከነ ከመነዳሪው

በቁጥር

10

 

7

195/65 R15 ፍላፕ ከነ ከመነዳሪው

በቁጥር

5

 

8

9.00 R20 ባለ ሽቦ ፍላፕ ከነ ከመነዳሪው

በቁጥር

7

ቀጭን ጥርስ 2 የፊት ወፍራም ጥርስ 5 የኃላ

9

3.00-17 የኃላ ጎማ100/90/-17 የፊት ጎማ ከነከመነዳሪው (ለሞተር ሳይክል)

በቁጥር

48

3.00-17 የኃላ 24 100/90/-17 የፊት 24

1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርቡና በመስኩ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ምዝገባ (VAT) ምዝግባ ሰርተፊኬት የታክስ ክሊራንስ እና በግዥ እና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ (PPA) አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።

2. ተጫራቾች መረጃ እና ማብራሪያ ሐዋሳ ከተማ አሮጌ አውቶቢስ ተራ አጠገብ ከሚገኘው የሲዳማ ሪጅን ሰፕላይ ቼይን ንብረት እና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ቁጥር 205 ማግኘት ይችላሉ።

3. የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 800 (ስምንት መቶ) ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000182117742 ሲዳማ ሪጅን በመከፈል የጨረታ ሰነዱን ከሪጅኑ ፋይናንስ እና ኮንትሮል ቢሮ ቁጥር 405 መግዛት ይችላሉ።

4. ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻው በተገኙበት/ባይገኙም በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በሲዳማ ሪጅን የሰፕላይ ቼይን ንብረት እና ጠቅላላ አገልግሎት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 205 ይከፈታል።

5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 150,000 (አንድ መቶ ሀምሳ ሺህ) በባንክ ዋስታና (Bid bond Guarantee) ወይም ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ አለባቸው።

6. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ25/12/2018 ዓም በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ25/12/2018 በ8፡30 ይከፈታል

7. ጨረታው ለ 60 ቀናት ጸንቶ ይቆያል።

8. የቴክኒክ እና የፋይናንስ ሰነዶች በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕች ተለይተው መቅረብ አለባቸው።

9. ከኢትዮያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እና ከሌሎች ከድርጅቱ የሪጅን ዘርፎች ወይም ከማንኛውም ሌላ ስልጣን ካለው ዘርፍ ጋር የውል መቋረጥ ታሪክ ያለው እና ባለፈው የውል ዘመኑ ጥሩ ያልሆነ አፈጻጸም እንደነበረው የተረጋገጠ ማንኛውም ተጫራች በቴከኒክ ግምገማ ወቅት የመሰረዝ መብት አለው።

10. ማንኛውም የማጭበርበሪያ (ሐሰተኛ) ሰነዶችን ለማቅረብ መሞከር ከጨረታው ውድቅ እንዲሆን ያደርጋል።

11. መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሲዳማ ሪጅን


Tender details

  • Deadline: 2026-08-31
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-08-31 14:30
  • Region: Sidama
  • Publishing entity: Ethiopian Electric Utility
  • Bid bond: 150,000.00 ብር
  • Bid document price: 800.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 13, 2026)
  • Posted at: 2026-08-13T08:59:53.000Z
← Back to all tenders