Spare Parts and Car Decoration Materials

በአብክመ የከሚሴ ከተማ እና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በጽ/ቤቱ ሥር ለሚገኙት ለሁሉም ማሽነሪዎች የሚውል የጎማ እና መለዋወጫ እቃዎች ግዥ ለመፈፀም በዘርፉ የንግድ ፈቃድ ያላቸውን ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የማሽነሪ ጎማ እና መስዋወጫ ግዥ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በአብክመ የከሚሴ ከተማ እና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በጽ/ቤቱ ሥር ለሚገኙት ለሁሉም ማሽነሪዎች የሚውል የጎማ እና መለዋወጫ እቃዎች ግዥ ለመፈፀም በዘርፉ የንግድ ፈቃድ ያላቸውን ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት 1 የማሽነሪ መለዋወጫ ዕቃዎች ግዥ
  • ሎት 2 የማሽነሪ ጎማ ግዥ

ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ ፈቃደኛ የሆኑ፡-

1. ለሥራው ሕጋዊ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉና ያሳደሱ፤ ለሥራው የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፤ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው ግዥው ከ200,000 ሺህ ብር በላይ የሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆነ መሆን አለበት።

2. የጨረታው ሰነድ ከከሚሴ ከተማ እና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 33 በግዢ/ፋይ/ንብ/አስ/ዋና የሥራ ሂደት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 /ለአስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ከላይ የተዘረዘሩትን መረጃዎች ዋናና ኮፒ በመያዝ ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመከፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋና እና ኮፒ በማድረግ በታሸገ ኤንቨሎፕ በአብክመ የከሚሴ ከተማ እና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በግዢ/ፋይ/ንብ/አስ/ዋና የሥራ ሂደት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ ስድስተኛው /16/ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጎማ እና መለዋወጫ እቃዎች ግዥ ጨረታ ሰነድ ባለው ጊዜ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

4. ጨረታው 22/12/2018.ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 የማሽነሪ ጎማ እና መለዋወጫ እቃዎች ግዥ ላይ በግዢ/ፋይ/ንብ/አስ/ዋና የሥራ ሂደት ቢሮ ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

5. ተጫራቾች ተመላሽ የሚደረግ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ገንዘብ

  • ሎት 1 – 30,000 /ሰላሳ ሺህ ብር
  • ሎት 2፡- 30,000/ሰላሳ ሺህ ብር በጥሬ ገንዘብ ወይንም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ /CPO/ ማስያዝ አለባቸው።

6. ለማሺነሪ ጎማ እና መለዋወጫ እቃዎች ግዥ የጨረታ አሸናፊ የሆነው ድርጅት ውል በሚዋዋልበት ጊዜ የውለታ ማስከበሪያ ከአጠቃላይ ድምር ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርበታል።

7. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

8. ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ፤ በኬሚሴ ከተማ እና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በግንባር በመቅረብ ወይንም በስልክ ቁጥር 033 554 0255 ደውለው መረዳት ይችላሉ።

በአብክመ የከሚሴ ከተማ አስተዳደር ከተማ እና መሠረተ ልማት ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-28
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-08-28 10:30
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Kemise City Administration Urban and Infrastructure Development Office
  • Bid bond: 30,000.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Bid document price: 300.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published on: Addis Zemen (Aug 13, 2026)
  • Posted at: 2026-08-13T09:00:18.000Z
← Back to all tenders