Spare Parts and Car Decoration Materials
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የከለላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ፋስት ሙቪንግ የመኪና ስፔር ፓርት፣ ዓመታዊ የመኪና ስፔር ፓርት እና የቀላል መኪና ጎማ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የከለላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥ ቡድን በመደበኛ በጀት በ2019 በጀት ዓመት ለከላላ ወረዳ ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል
- ሎት1 ፋስት ሙቪንግ የመኪና ስፔር ፓርት
- ሎት 2 ዓመታዊ የመኪና ስፔር ፓርት እና
- ሎት 3 የቀላል መኪና ጎማ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው
- የግዥ መጠን ብር ከ200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ሎት ለየብቻ ለአመታዊ ስፔር ፓርት እና ፋስት ሙቪንግ ለእያንዳንዳቸው ብር 150,000 / አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ/ ብር ብሎም ለመኪና ጎማ 50,000 /ሃምሳ ሺህ/ ብር በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 (ደረሰኝ) ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊነታቸው ከታወቀ የውል ማስከበሪያ 10% በማስያዝ በከለላ ወረዳ ዓቃቤ ሕግ ጽ/ቤት ውል በመግባት በተቀመጠው ዝርዝር መግለጫ መሰረት ኦርጅናል እቃ ማቅረብ አለባቸው።
- አሸናፊው ድርጅት በውላቸው መሰረት የመኪና ስፔር ፓርቱን እስከ ሰኔ 30/2019 ዓ.ም እንደ አስፈላጊነታቸዉ የሚቀርብ ሲሆን የመኪና ጎማውን ግን ከለላ ወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች ድረስ ማስጫኛና ማውረጃን ጨምሮ በራሳቸው ወጭ በማጓጓዝ ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታ ሰነዱን ከከለላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 02 የማይመለስ 500/ አምስት መቶ/ የኢትዮጵያ ብር በመክፈል መውሰድ ይችላል።
- የውድድሩ ሁኔታ በጠቅላላ ድምር በሎት ነዉ።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከለላ ወረዳ ገንዘብ ጽቤት ቢሮ ቁጥር 04 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 14 61 22 51/ 033 451 0464 በመደወል ማግኘት ይቻላል።
- ማንኛውም ተጫራች በመጫረቻ ሰነዱ ላይ የአንድ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ በመሙላት ጠቅላላ ድምር በማስቀመጥ የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ከለላ ወረዳ ገንዘብ ጽቤት ቢሮ ቁጥር 04 በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ከቆየ በኋላ በ16ኛው ቀን 3፡00 ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በከለላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 04 በ3፡30 ይከፈታል። ሆኖም ግን ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ባይገኙም የጨረታውን መከፈት የማያስተጓጉል ከመሆኑም በተጨማሪ በጨረታ ሂደቱ ለሚተላለፍ ውሳኔዎች ተገዢ ይሆናሉ።
- የጨረታው መክፈቻ ጊዜ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
- መ/ቤቱ የእቃውን 20% የመጨመርም ሆነ የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የከለላ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-29
- Bid closing time: 09:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 3፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-29 09:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 3፡30 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: ANRS Kelela Woreda Finance and Economic Development Bureau
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 14, 2026)
- Posted at: 2026-08-14T07:49:38.000Z