Food and Beverage

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ሥልጠና ማዕከል ለ2019 ዓ.ም. አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በዘርፉ ከተሰማሩ ሕጋዊ ድርጅቶች ግዥ መግዛት ይፈልጋል

Description

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር እ.አ.ስ.ስ.አ.ኮ.ስ.ማ 001/2019

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ሥልጠና ማዕከል ለ2019 ዓ.ም አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በዘርፉ ከተሰማሩ ሕጋዊ ድርጅቶች ግዥ መግዛት ይፈልጋል ፡፡

  • ሎት 1፡- የምግብ ዝግጅት ግብዓቶች ምርት ግዥ
  • ሎት 2፡- አላቂ የጽዳትና የጽሕፈት መሳሪያ እቃዎች ግዥ
  • ሎት 3፡- የሕንጻ ፊኒሽንግ ሥራ
  • ሎት 4፡- የሠልጣኞች የስፖርት መገልገያ አልባሳት ግዥ
  • ሎት 5፡- የህትመት አገልግሎት ግዥ

በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች -

1. በዘርፉ ሕጋዊና የታደሰ ንግድ ፍቃድ የንግድ ምዘገባ ምስክር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምስክር ወረቀት የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin) ምስክር ወረቀት ግብር ከፋይነትን የሚያረጋግጥ ከሀገር ውስጥ ገቢ ሰርተፍኬት (ታክስ ክሊራንስ) እና በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

2. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 500/ አምስት መቶ ብር /በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከሰኞ እሰከ ዓርብ ከጠዋቱ 2፡30-11፡30 ድረስ ብቻ አዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የእሳትና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ሥልጠና ማዕከል አስተዳደርና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 1 ክፍያ በመፈጸም የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላል::

3.ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 11 ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ስልጠና ማዕከለ ግዥ ክፍል ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ የጨረታ ሰነዳችሁን ማስገባት ይኖርባችዋል፡፡

4.ጨረታው በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ተጫራቶች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 ሥልጠና ማዕከሉ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ዕለቱ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡

5.ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ሥልጠና ማዕከል ስም የተዘጋጀ የገንዘብ መጠን ለእያንዳንዱ ሎት ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰርተ የባንክ ዋሰትና ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

6. ተጫራቾች የቴክኒክና ፋይናንሽያል ሰነዶች ተለይተዉ በተለያዬ - ፖስታ ፋይናንሽያል ኦርጅናል እና ኮፒ እንዲሁም ቴክኒካል ኦርጅናል እና ኮፒ ተብሎ በአራት ፖስታ በማድረግ ኮፒ እና ኦርጅናሉ በጉልህ ተጽፎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡የጨረታ ማስከበሪያው በቴክኒካል ኦርጅናል ስነድ ጋር በአንድ ላይ ታሽጎ መቅረብ አለበት::

7. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

አድራሻ አዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ሰታዲየም ጎን ነው::

ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፤ 0114 397 220 / 0114 622 379 ደውለው ማነጋገር ይችላሉ::

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር የእሳትና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ሥልጠና ማዕከል


Tender details

  • Deadline: 2026-08-26
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-26 10:30
  • Bid opening (note): ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ababa City Administration Fire and Disaster Management Commission
  • Buyer address: ቅ/ጊ/ዮርጊስ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ወይም ሚኒሊክ ሀውልት ፊት ለፊት ያለው እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ህንፃ
  • Bid bond: 50,000.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Bid document price: 500.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Published on: Addis Zemen (Aug 14, 2026)
  • Posted at: 2026-08-14T08:07:43.000Z
← Back to all tenders