Textile, Garments and Uniforms

በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 12 የካራ ጋቢሳ ቅድመ መደበኛ የመጀመረያ ደረጃ ት/ቤት ዕቃዎችና አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ የግልፅ ጨረታ ቁጥር 01/2019

በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 12 የካራ ጋቢሳ ቀድመ መደበኛ የመጀመረያ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 ዓ/ም በጀት አመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎችና አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፣

ስለሆነም ህጋዊ ድርጅቶች ከዚህ በታች በተዘረዘረው መስፈርት መሰረት መሳተፍ የምትቸሉ መሆኑን እንገልፃለን፣

በየሎቱ የተጠየቀው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በኢትዮ ብር

  • ሎት፣1 የደንብ ልብስ 6000ብር
  • ሎት2. አላቂ የቢሮ ዕቃዎች 3000ብር
  • ሎት3 የህትመት 2000ብር
  • ሎት4. አላቂ የሕክምና ዕቃዎች 2000ብር
  • ሎት5. አላቂ የት/ት እቃዎች 4000ብር
  • ሎት6. ሌሎች አላቂ ዕቃዎች 3000ብር
  • ሎት7. ሌሎች አላቂ መሣሪዎችና መፅሀፍት 2000ብር
  • ሎት8. ቋሚ የቢሮ እቃዎች 10,000ብር

በጨረታ መሳተፍ ለምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች ማሟላት ያለባችሁ:

1. በዘርፋ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና ከሀገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን የዘመኑን የመንግሰት ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃቸውንና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የምስክር ወረቀትና ቲን ነበር ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው

2. ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ አና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ በተጨማሪም ካሽሬጅስተር ማሽን ደረሰኝ ያላቸው

3. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስከ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰአት የካራ ጋቢሳ ቅድመ መደበኛና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 01 መግዛት ዶችላሉ ስለዚህ በተሰጠው ቀንና ሰዓት ሁሉም ተጫራቾች ሰነዳቸውን አስገብተው ማጠናቀቅ አለባቸው።

4. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከላይ በየሎቱ በተጠቀሰው የዋስትና ማስያዣ ብር መሰረት በባንክ የተመሰከረለት የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/CPO/ ማስያዝ አለባቸው። የመወዳደሪያ እቃ ዋጋ ከቫት ጋር ደምረው ህጋዊ ማህተምና ፊርማ አድርገውበት ይላኩልን።

5. ተጫራቾች በእያንዳንዱ እቃ የሚጫረቱበትን ዋጋ ዝርዝር በመግለጽ በሰም በታሸገ ኢንቨሎኘ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።

6. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት እቃዎች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ሲያቀርቡ ኦሪጂናልና ኮፒ አድርገው ማስገባት አለባቸው።

7. ተጫራቾቸ ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ የእቃ ዝርዝር ደረጃውን የጠበቀ ናሙና ለት/ቤቱ ማቅረብ አለባቸው።

8. ተጫራቾች ያሸነፏቸውን እቃዎች ተወዳድረው ካሽነፈበት ናሙና ምንም ለውጥ ሳያደርጉ በራሳቸው ወጪ ነው የማቀረብና ደረጃውን ያልጠበቀ እቃ ከሆነ መልሰው ትክክለኛውን እቃ የማምጣት ግዳታ አለባቸው።

9. ጨረታው የሚታሸገው በ10ኛው ቀን ከሰዓት በኋላ 10፡00 ሰዓት ሲሆን በዚሁ እለት 10፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል።

10. የጨረታው አሸናፊ የጨረታው ውጤት ሲታወቅ የውል ማስከበሪያ ካሸነፈበት ጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 10% በጥሬ ገንዘብ/C.PO/ በቅድሚያ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ቦታ ካራ ጋቢሳ የመጀደ ት/ቤት ከካራ ወደ ጣፎ ሲሄዱ በገደራ
ሳራ አምፑል በግራ በኩል ገባብሎ የካ አባዶ ኮንዶሚኒየም
ሳይት G7 መጨረሻ በስተግራ ታጥፎ 4.5 ኪሜ ገባ ብሎ
አዲስ አበባ ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 011-868-0487/ 09 33-73-85-04
በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 12 የካራ ጋቢሳ ቅድመ መደበኛ የመጀመረያ ደረጃ ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-25
  • Bid closing time: 16:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከሰዓት በኋላ 10፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-25 16:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከሰዓት በኋላ 10፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Kara Gabissa Kindergarten and Primary School
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 14, 2026)
  • Posted at: 2026-08-14T08:10:36.000Z
← Back to all tenders