Textile, Garment and Leather

በኢሉአባቦር ዞን ሐሉ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በስሩ ላሉት መ/ቤቶች ለ2019 ዓ.ም. የበጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል መሳሪያዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በኢሉባቦር ዞን ሐሉ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት 2019 የጨረታ መመሪያ

በኢሉአባቦር ዞን ሐሉ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በስሩ ላሉት መ/ቤቶች ለ2019 ዓ.ም የበጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል መሳሪያዎች ፈርኒቸር፣ ጎማና ካለመዳሪያ፣ ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች፣ ደንብ ልብስ፣ ደንብ ልብስ ስፌት፣ የጽህፈት መሳሪያዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ እንዲሁም ለመንገድ ጥገና ስራ የተለያዩ ማሽኖችን ስሪታቸው እ.አ.አ 2014 ወድህ ሲኖትራክ፣ ፒካፕ ትዮታ ደብል ጋቢና ለሳይት ስራ አገልግሎት የሚውል፣ሩሎ ባለቫይብሬተር፣ ግሬደር፣ እስካቫተር፣ ሻወርትራክ፣ ዶዘር እና ሎደር አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ::

1. በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው የዘመኑን ግብር የከፈለና ማስረጃ አያይዞ ማቅረብ የሚችል እና የቫት /VAT/ ተመዝጋቢ መሆን አለበት፡፡

2. በንግድ ሚኒስቴር በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገበ፡፡

3. ለጨረታ ማስከበሪያ 70,000.00 /ሰባ ሺህ ብር/ በሲፒኦ / cpo/ ብቻ ለእያንዳንዱ ዶክመንት ማስያዝ የሚችልና ጨረታውን ካሸነፈ በኋላ ለውል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ/cpo/ማስያዝ አለበት፡፡

4. ተጫራቹ ጨረታውን ካሸነፈ ቀርቦ ውል ለመፈረም ፈቃደኛ የሆነና ዕቃዎቹን በራሱ ሙሉ ወጪ በታዘዘ በ15 ቀን ውስጥ እስከ ጽ/ቤቱ ለማቅረብና ቆጥሮ ማስረከብ አለበት፡፡

5. ተጫራቹ የዕቃውን ሞዴል ባልተገለጸበት ቦታ በጨረታው ዝርዝር ላይ አብራርቶ መግለጽ አለበት፡፡

6. ተጫራቹ የተፈለገውን ዕቃ ጥራትና ብዛት አሟልተው የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡

7. በፈርኒቸር ዕቃዎች ላይ የምትወዳደሩ ድርጅቶች የፈርኒቸሮችን ዲዛይንና በምስል ከዋጋው ጋር አሽጎ ማቅረብ እና ካሸነፈ ገጣጥሞ ማስረከብ የሚችል መሆን ይኖርበታል።

8. ተጫራቹ ለሚያቀርባቸው የደንብ ልብሶች እና ለመ/ቤቱ አስፈላጊ ለሆኑ ቢሮ ዕቃዎች ከጨረታው ሰነድ ጋር በምስልና ናሙና ሳምፕል ማቅረብ አለበት።

9. ተጫራቹ የሚያቀርበው ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት።

10. ጨረታውን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጀምሮ ለ15 የስራ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጠናቆ በዚሁ ቀን በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሐሉ ወረዳ ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡

11. ተጫራቾች እያንዳንዱን የጨረታውን ሰነድ በማይመለስ 1200.00 /አንድ ሺህ ሁለት መቶ/ ብር ከሐሉ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ግዢ ክፍል በመግዛት የሚጫረቱበትን መወዳደሪያ የአንዱን ዋጋ በመሙላት ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡

12. በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ከልክል ነው፡፡

13. የሚወዳደሩበትን ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌላው እና የሚነበብ መሆን አለበት።

14. ተወዳዳሪዎች ዋጋን የሚገልጽ ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻ ፍቃድና የተለያዩ ተፈላጊ ሰነዶችን የሚገልጽ ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻ እንዲሁም ሲፒኦ/ cpo/ ለየብቻ 5/አምስት ፖስታዎችን በማሸግ አለባቸው፡፡

15. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታው ሣጥን በግዥ ክፍል ውስጥ ከፍት መሆኑን አውቃችሁ እስከ 15ኛው ቀን ፖስታዎችን የስራ ቀናት በፈለጋችሁት ቀን ማስገባት ትችላላችሁ፡፡

16. አሸናፊ ተጫራቾች ማሽኑን ማምጫ እና መመለሻ እስከ ሀለ ወረዳ መንገድ እና ሎጅስትከስ ጽ/ቤት እና ስራ ቦታ (ሳይት) ማስገባት እና ከአንድ ቦታ (ሳይት) ወደ ሌላ ቦታ (ሳይት) ስራ የምሰራበት ሳይት ማቅረብ ማንቀሳቀስ በራሱ ወጪ የሚችል፡፡

17. የማሸኑ የማስመጫ እና ማውረጃ እና ነዳጅ በአሸናፊ የሚሸፈን ይሆናል፡፡

18. አሸናፊ ተጫራች ማሸኑን በፈጸሙት ስምምነት መሰረት ካላቀረቡ ለስራቸው አፈጻጸም ያስያዙት 10 ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡

19. ማሽኑ ቢበላሽ በ 5 ቀን መካከል ቀይሮም ይሁን አሰርቶ የባለንብረቱ ይሆናል፡፡

20. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር፡- 0911 013 596 / 0917 216 107 / 0922 003 180

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር በኢሉባቦር ዞን የሐሉ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-01
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጀምሮ ለ15 የስራ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-01 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጀምሮ ለ15 የስራ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Illubabor Zone Halu woreda Finance and Economic Development Bureau
  • Bid bond: 70,000.00 ብር ለእያንዳንዱ ዶክመንት
  • Bid document price: 1,200.00 ብር ለእያንዳንዱ ሰነድ
  • Published on: Addis Zemen (Aug 14, 2026)
  • Posted at: 2026-08-14T08:29:49.000Z
← Back to all tenders