Materials

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 አዲስ ተስፋ ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በ2019 በጀት አመት በመደበኛና በውስጥ ገቢ በጀት የተለያዩ እቃዎች ግዥና የጥገና ስራዎች በሎት ከፋፍሎ በአንደኛ ዙር ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በግዥ እና በአገልግሎት መፈፀም ይፈልጋል

Description

የ1ኛ ዙር ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 አዲስ ተስፋ ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በ2019 በጀት አመት በመደበኛና በውስጥ ገቢ በጀት የተለያዩ እቃዎች ግዥና የጥገና ስራዎች በሎት ከፋፍሎ በአንደኛ ዙር ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በግዥ እና በአገልግሎት መፈፀም ይፈልጋል፣

ስለሆነም፡-

  • ሎት 1 አላቂ የቢሮ እቃ (ኢስቴሽነሪ)
  •  ሎት 2 የትምህርት ዕቃ፣
  • ሎት 3 ደንብ ልብስ፣
  • ሎት 4 የጽዳት እቃ
  • ሎት 5 ህትመት፣
  • ሎት 6 ትራንስፖርት ጭነት አገልግሎት፣
  • ሎት 7 የሻይና ቡና መስተንግዶ
  • ሎት 8 ጥገና እና እድሳት የውሃ መስመር ጥገና
  • ሎት 9 የመምህራን ሎከር ጥገና እና እድሳት
  • ሎት 10 የቋሚ ዕቃ
  • ሎት 11 የማሽነሪ ጥገና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በግዥ እና በአገልግሎት መፈፀም ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።

1. የሚወዳደሩበት የንግድ ዘርፍ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ በመንግስት ዕቃ ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገበበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችልና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ።

2. የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ሽሮሜዳ በሚገኘው አዲስ ተስፋ የመጀ/ደረጃ ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 05 በመምጣት ወይም ወኪሎቻችሁን በመላክ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።

3. የእቃዎች ዋጋ 15 ፐርሰንት ቫት ተጨምሮ ይቅረብ ባይቀርብ። እንደተጨመረ ሆኖ የሚሰራ ይሆናል።

4. ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው ዋጋ ማቅረቢያ ቦታ በግልፅ መሙላት አለባችሁ።

5. የምታስገቧቸው ሰነድ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ሊኖረው አይገባም ስርዝ ድልዝ ያለው ሰነድ ውድቅ ይሆናል።

6. ከባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፤ ጥቃቀንና አነስተኛ ዕቃ አቅራቢዎች ከሚመለከተው አካል በትምህርት ቤቱ ስም በተፃፈው ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

7. ተጫራቾች ለሚወዳደረበት እቃዎች ናሙና ጨረታ ስመከፈቱ በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ናሙና ያላቀረበ ተጫራቾች መወዳደር አይችሉም።

8. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከጠዋት 2፡30 እስከ 11:00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው ሳጥን በቢሮ ቁጥር 5 ማስገባት ይችላሉ።

9. ጨረታው የሚከፈተው የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣ በ10ኛው ቀን ተዘግቶ በ11ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት ህጋዊ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በተገኘው ሰው ቢሮ ቁጥር-2 ይከፈታል፣ የመክፈቻው ቀን በዓል ወይም እረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።

  • የጨረታ ሎት 1 አላቂ የቢሮ እቃ (እስቴሽነሪ) 5,000 ብር
  • ሎት 2 የትምህርት እቃ 4,000 ብር
  • ሎት 3 ደንብ ልብስ 5,000 ብር
  • ሎት 4 የጽዳት እቃ 4,000 ብር
  • ሎት 5 ህትመት ፤ 3,000 ብር
  • ሎት 6 ትራንስፖርት ጭነት አገልግሎት 2.000 ብር
  • ሎት 7 የሻይና ቡና መስተንግዶ 4,000 ብር
  • ሎት 8 ጥገና እና ስድሳት የውሃ መሰመር ጥገና 3000 ብር
  • ሎት 9, የመምህራን ሎከር ጥገና እና ስድሳት 3,000 ብር
  • ሎት 10 የቋሚ እቃ 6,000 ብር
  • ሎት 11 የማሽነሪ ጥገና ብር 3.000 ብር

10. የጨረታው የፋይናንሻል ኦርጅናል ዶክመንቶች እንዲሁም የጨረታ ማስከበረያውን ለየብቻ አስተማማኝ በሆነ ማጣበቂያ በታሽገ ፖስታ ላይ የተጫራች ሙሉ ስምና አድራሻ በመፃፍ ማህተም በማድረግ በተጠቃለለ አንድ ፖስታ በማሸግ መቅረብ ይኖርባቸዋል።

11. አሸናፊ ሆኖው የተመረጡ ድርጅቶች በራሳቸው ትራንስፖርት ውጪ ት/ቤት ግምጃ ቤት ድረስ በማምጣት ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል።

12. እንደ አስፈላጊነቱ ት/ቤቱ 20% የመጨመር 20% የመቀነስም መብቱ የተጠበቀ ነው።

13. ት/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ሽሮ ሜዳ 31 ቁጥር አውቶቢስ ማዞሪያ ወደ ኪዳነምረት መሄጃ መንገድ አዲስ ተስፋ የወ/ደ/ት/ቤት ኪዳነምት ታክሲ መያዥው 50 ሜትር ገባ ብሎ

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 011 154-5513/ 011 154-3466

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 አዲስ ተስፋ ቅድመ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-25
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከጠዋት 2፡30 እስከ 11:00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-26 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ተዘግቶ በ11ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Tesfa Kindergarten & Elementary School
  • Buyer address: በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 07 ከቤተል ሆስፒታል ወደ ውስጥ ገባ ብሎ ፖሊስ ጣቢያው ጀርባ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 14, 2026)
  • Posted at: 2026-08-14T08:34:35.000Z
← Back to all tenders