Materials

የናታኒም በጎ አድራጎት ድርጅት በ“CADiR” (Collective Action for Disability Rights) ፕሮጀክት አማካኝነት ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎችና ወጣቶች አገልግሎት የሚውሉ ድጋፍ ሰጪ መሣሪያዎችን፣ የትምህርትና የልዩ ፍላጎት ቁሳቁሶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡ NCO/0299/26

ናታኒም የበጎ አድራጎት ድርጅት (Natanim Charitable Organization)

  • ድጋፍ ሰጪ መሣሪያዎችና የልዩ ፍላጎት ትምህርት ቁሳቁሶች ግዢ ጨረታ

የናታኒም በጎ አድራጎት ድርጅት በ“CADiR” (Collective Action for Disability Rights) ፕሮጀክት አማካኝነት ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎችና ወጣቶች አገልግሎት የሚውሉ ድጋፍ ሰጪ መሣሪያዎችን፣ የትምህርትና የልዩ ፍላጎት ቁሳቁሶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

1. ስለ ናታኒም በጎ አድራጎት ድርጅት (Natanim Charitable Organization - NCO)

ናታኒም በጎ አድራጎት ድርጅት (NCO) በሚያዚያ 5 ቀን 2015 ዓ.ም. (License No. 6792) የተመዘገበ ኢትዮጵያዊ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ሲሆን፣ በአእምሮ ጤና፣ በማህበራዊ ድጋፍ (psychosocial support) እና አካል ጉዳተኞችን በማካተት ላይ ትኩረት አድርጎ ይሰራል። NCO ከመንግስት ተቋማት፣ ከትምህርትና ጤና ዘርፎች፣ ከሌሎች በጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ከአካል ጉዳተኞች ማህበራት (OPDs) ጋር በትብብር ይሰራል።

  • ራዕይ (Vision): ሁሉም ማህበረሰብ እና ግለሰብ ከማህበራዊ ቀውስ እና ከአእምሮ ጤና ችግሮች የተጠበቀ እና የዳነ ሆኖ ማየት።
  • ተልዕኮ (Mission): ተጋላጭ ማህበረሰቦችን በማህበራዊ ድጋፍ፣ በትብብር እና በመሟገት ማገልገል።
  • እሴቶች (Values): ገለልተኝነት፣ የአእምሮ ደህንነት፣ መሟገት፣ ትብብር፣ ቁርጠኝነት፣ ፈጠራ እና ርህራሄ።

I. የሚፈለጉ የመሣሪያዎች እና ቁሳቁሶች ምድብ (Procurement Categories / Lots)

  • Lot 1: Mobility & Orthotic Assistive Devices (የመንቀሳቀስ ችግር መርጃ መሣሪያዎች)
  • Lot 2: Hearing, Visual & Educational Technology Devices (የመስማት፣ የእይታና የቴክኖሎጂ መርጃ መሣሪያዎች)
  • Lot 3: Sensory, Therapy & Adaptive Learning Materials (የስሜት ህዋሳት፣ የተራፒና የልዩ ፍላጎት መማሪያ ቁሳቁሶች)
  • Lot 4: Books, Learning Supplies & General Office Materials (የማጣቀሻ መጻሕፍት፣ የመማሪያና የጽሕፈት ቁሳቁሶች)
  • Lot 5: Hygiene, First Aid & Sanitation (የንጽህና፣ የሕክምናና የመጀመሪያ እርዳታ ቁሳቁሶች)

II. የጨረታው ተሳታፊዎች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች

  • የንግድ ፈቃድ: በዘርፉ የተሰማሩበት የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው።
  • ግብር ከፋይነት: የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና የቫት (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑበት ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
  • የአቅርቦት ልምድ: ተመሳሳይ ድጋፍ ሰጪ መሣሪያዎችንና የትምህርት ቁሳቁሶችን በማቅረብ ልምድ ያላቸው መሆኑን ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል።
  • የቴክኒክ ዝርዝር: ለሚቀርቡት እቃዎች ሁሉ ዝርዝር የቴክኒክ መግለጫ (Specification) እና የመነሻ ሀገር (Country of Origin) ማቅረብ አለባቸው።
  • የዋጋ ተመን: ዋጋውን በኢትዮጵያ ብር (ETB) በVAT ያካተተ ወይም ያልያዘ መሆኑን በግልጽ መጥቀስ አለባቸው።

III. የጨረታ ማስገቢያና መክፈቻ ጊዜ ሰሌዳ

  • የጨረታው ማስታወቂያ የሚወጣበት ቀን: አርብ፣ ነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ.ም. / August 14, 2026
  • የጨረታ ማስገቢያ የመጨረሻ ቀን፡ ሰኞ፣ ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ.ም. / Monday, August 24, 2026 ከቀኑ 11:00 ሰዓት በፊት።
  • የጨረታ መክፈቻ ቀን፡ ማክሰኞ፣ ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ.ም. / Tuesday, August 25, 2026 ከቀኑ 5:30 ሰዓት ላይ።

አቅራቢዎች የጨረታ ሰነዱን (ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ፕሮፖዛልን) በሁለት የተለያዩ ኢንቭሎፖች ታሽገው በተፈረሙ ፖስታዎች በማድረግ፣ በአጠቃላይ በሶስተኛ ጥቅል ፖስታ ውስጥ በማሸግ በናታኒም በጎ አድራጎት ድርጅት ዋና ጽ/ቤት አዲስ አበባ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 02 በአድራሻችን በአካል በመገኘት፣ እንዲሁም ከታች በተዘረዘሩት ስልክ ቁጥሮች አድራሻውን በመጠየቅ ማስገባት ይችላሉ።

ማሳሰቢያ: ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መመሪያ (Terms of Reference - TOR) ሰነድ ከዚሁ የጨረታ ማስታወቂያ ጋር ማግኘት ይችላሉ።

ለበለጠ መረጃ፡

  • ናታኒም የበጎ አድራጎት ድርጅት
  • ስልክ፡ 0933839191 (Betelihem Kefyalew) / 0993252797 (Tsedeniya Getinet) / 0945462424 (Fikirte Tarekegn)
  • ኢሜይል: [email protected][email protected][email protected] 
  • አድራሻ፡ አዲስ አበባ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 02

Tender details

  • Deadline: 2026-08-24
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid opening: 2026-08-25 11:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Natanim Charitable Organization (NCO)
  • Buyer TIN: 0084298990
  • Published on: 2merkato.com (Aug 15, 2026)
  • Posted at: 2026-08-15T06:51:04.000Z
  • Buyer website: https://natanimethiopia.org/
← Back to all tenders