Building and Finishing Materials

የሆለታ ኤጄሬ ንፁህ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ለ2019 በጀት ዓመት የሚውል፤ የተለያዩ የቧንቧ እቃዎችን፣ የጽሕፈት መሣሪያዎችን፣ የቢሮ እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የሠራተኞች የደንብ ልብስ፣ የሠራተኞች የደንብ ልብስ የስፌት ዋጋ፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮ መካኒካል፣ የመኪና ጎማ፣ የመኪና ጥገና፣ ሞተር ሳይክል የተለያዩ የግንባታ ዕቃዎችና የውሃ ጥራት ዕቃዎች የሚውሉ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የሆለታ ኤጄሬ ንፁህ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ለ2019 በጀት ዓመት የሚውል፤ የተለያዩ የቧንቧ እቃዎችን፤ የጽሕፈት መሣሪያዎችን፤ የቢሮ እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፤ የሠራተኞች የደንብ ልብስ፤ የሠራተኞች የደንብ ልብስ የስፌት ዋጋ፣ የፅዳት ዕቃዎች፤ ኤሌክትሮ መካኒካል የመኪና ጎማ ፤ (የመኪና ጥገና፤ ሞተር ሳይክል የተለያዩ የግንባታ ዕቃዎችና የውሃ ጥራት ዕቃዎች የሚውሉ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

 ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ነጋዴዎች መወዳደር ትችላላችሁ።

1. በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ኖሮት የታደሰ የንግድ ፈቃድ የያዘና የዘመኑን ግብር የከፈለ፤

2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገበና ሰርተፍኬት ያለው፤

3. ተጫራቾች ካወጣችሁት ንግድ ሥራ ዘርፍ ውጪ የተወዳደረ ተጫራች ከጨረታው ይሰረዛል።

4. ለጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ 100,000 /አንድ መቶ ሺህ / ብር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስንቄ ባንክ እና ኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ብቻ በሲፒኦ ማስያዝ የሚችሉት ጨረታውን ካሸነፈ ለውል ማስከበሪያ ያሸነፈበት ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ 10 /100 በባንክ ማስያዝ የሚችል፤

5. ተጫራቹ ጨረታውን ካሸነፈ በኋላ ዕቃዎቹን በራሱ ወጪ እስከ የሆለታ ኤጄሬ ከተማ ንፁህ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ድረስ ማቅረብ የሚችል፤

6. ድርጅቱ ለሚጠረጥራቸውና ማጣራት ለሚፈልገው ዕቃ ናሙና ማስቀረብ ይችላል።

7. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናቶች በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ 16ኛው ቀን በ8፡30 ሰዓት ላይ የሚጠናቀቅ ሲሆን በዚሁ ቀን በ9፡00 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ተወካዮቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል።

8. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በማይመለስ 1000(አንድ ሺህ) ብር በቢሮ ቁጥር 3 በመክፈል /ቢሮ ቁጥር 2 መግዛት ትችላላችሁ።

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር
0112370059 0112610442፤ መጠየቅ ትችላላችሁ።
የሆለታ ኤጄሬ ንፁህ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-02
  • Bid closing time: 14:30
  • Bid closing (note): ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናቶች በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ 16ኛው ቀን በ8፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-02 15:00
  • Bid opening (note): ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናቶች በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ 16ኛው ቀን በ9፡00 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Holeta Ejiere City Water Supply and Sewerage Enterprise
  • Bid bond: 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር)
  • Bid document price: 1000 (አንድ ሺህ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 15, 2026)
  • Posted at: 2026-08-15T07:59:33.000Z
← Back to all tenders