Textile, Garments and Uniforms
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የነቀምቴ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና ኮሌጅ የተለያዩ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Textile, Garments and UniformsTextile, Garment and LeatherShoes and Other Leather Products
Oromia
More tags
StationeryOffice Supplies and ServicesCleaning and Janitorial Equipment and ServiceEquipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsComputer and AccessoriesIT and TelecomOffice Machines and AccessoriesOffice FurnitureFurniture and FurnishingHouse FurnitureWood and Wood WorkingTri Wheeler, Motorcycles and Bicycles PurchaseAmharic2merkatoNekemte TVET College
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የነቀምቴ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና ኮሌጅ በ2019 ዓ.ም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
ስለዚህ፤-
- 1ኛ. የሠራተኞች ደንብ ልብስ።
- 2ኛ. የጽሕፈት መሣሪያዎች።
- 3ኛ. የጽዳት ዕቃዎች ።
- 4ኛ. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች::
- 5 ኛ. የቢሮ ፈርኒቸሮች እና ዕቃዎች፡
- 6ኛ. የጋርመንት ብትን ጨርቅና ።
- 7ኛ.ሌዘር ጉድስ
- 8ኛ. ብስክሌት ሞቶር
ስለዚህ፡- የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።
- በዘርፉ ላይ ሕጋዊ የስራ ፍቃድ ያለው (ያላት)
- የ2018/2019 ዓ.ም. ግብር - ከፍሎ መታደሱን ማስረጃውን ማቅረብ የሚችል።
- የቫት ተመዝጋቢ የሆነና ማስረጃውን ማቅረብ የሚችል።
- ቲን ያለውና ማስረጃውን ማቅረብ የሚችል።
- በአቅራቢነት መመዝገቡን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
- ማንኛውም ተጫራች ከመንግሥት ግዥ ያልታገደ መሆን አለበት።
- የዕቃዎቹን ናሙና ማቅረብ የሚችል።
- ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ወደ ቢሮ ስትመጡ ዶክመንታችሁን ኦሪጅናሉን ይዛችሁ መቅረብ አለባችሁ፤
- የማይመለስ ብር 1000 ( አንድ ሽህ ብር) በመክፈል ለዚሁ የተዘጋጀውን ሠነድ ለመግዛት የሚችል።
- ያሸነፈውን ዕቃ በራሱ ወጪ እስከ ነቀምቴ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና ኮሌጅ ድረስ ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዕቃ ጥራት ያለውና ደረጃውን የጠበቀ መሆን አለበት።
- ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ መተው ወይም ሌላ ሃሣብ ማቅረብ አይችሉም፡፡
- ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 10000 (አሥራ አምስት ሺህ ብር) ለውል ማስከበሪያ የግዥ ጠቅላላ ዋጋ 5 በባንክ በተረጋገጠ ማስያዝ አለበት።
- ጨረታውን ለማደናቀፍ የሞከረ ማንኛውም ተጫራች መንግሥት ከሚያወጣውጨረታ ውጪ ይሆናል።
- አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ማንኛውም ተጫራች አሸናፊ መሆኑ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ 10 ቀን ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ቀርቦ ውል መቀበል አለበት።
- ተጫራቾች የገዙትን ሠነድ ዋጋውን ከሞሉ በኃላ የድርጅቱ ማህተምና ፊርማተደርጎበት በዋና ና ኮፒ በሁለት ኤንቬሎፕ በሰም ታሽጎ ተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 11፡30 ሰዓት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ16 ኛው ቀን እስከ 4፡00 ሠዓት የጨረታውን ሰነድ ማስገባት የምትችሉ ሲሆን ከ 4:00 ሰዓት በኋላ የጨረታው ሣጥን ስለሚዘጋ በ ሰዓቱ ያልተገኘውን ተጫራች የምና ወዳድር መሆኑን እየገለጽ፡ በዚው ዕለት ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ በ4፡05 ይከፈታል። ነገር ግን ቀኑ ዓመት በዓል ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር /0917038042 /0920274774/ 0920417393
የነቀምቴ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና ኮሌጅ
Tender details
- Deadline: 2026-08-31
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16 ኛው ቀን እስከ 4፡00 ሠዓት
- Bid opening: 2026-08-31 10:05
- Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16 ኛው ቀን እስከ 4፡05 ሠዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: Nekemte TVET College
- Bid bond: ብር 10000 (አሥራ አምስት ሺህ ብር)
- Bid document price: 1000.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 15, 2026)
- Posted at: 2026-08-15T08:13:07.000Z