Building and Finishing Materials
የአብክመ ጤና ቢሮ ለደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አገልግሎት የሚውል 2019 ዓ.ም በጀት አመት ከደረጃ 4 እና በላይ የሆኑ ተቋራጭ የህንፃ ግንባታ ስራ ለማሰራት፤ ለአንድ ጊዜ የግንባታ እቃ አቅርቦት ግዥ እና ለአንድ አመት የሚቆይ የህትመት ውጤት ለማሳተም ይፈልጋል
Description
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የአብክመ ጤና ቢሮ ለደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አገልግሎት የሚውል 2019 ዓ.ም በጀት አመት ከደረጃ 4 እና በላይ የሆኑ ተቋራጭ የህንፃ ግንባታ ስራ ለማሰራት፤ለአንድ ጊዜ የግንባታ እቃ አቅርቦት ግዥ፤ለአንድ አመት የሚቆይ የህትመት ውጤት ለማሳተም፡፡ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት እና ለመግዛትይፈልጋል።
ስለሆነም አግባብነት ያላቸውን ሁሉ በጨረታው እየጋበዝን
1. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት አይነት የተዛመደ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው።
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን-ነምበር ማቅረብ የሚችሉ
4. የግዥው መጠን ከ200,000 በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆነ
5. የሕንፃ ግንባታ ሥራ ለመሳተፍ ደረጃ 4 እና በላይ የሆነ ተቋራጭ መሆን አለበት።
6. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር ከ1-5 የተገለፁትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታው ኦርጅናል ሰነዶች ጋር ማቅረብ ይጠበቃል።
7. የህንፃ ግንባታ ስራን በተመለከተ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 21 ቀናት ከሆስፒታሉ ግዥ ክፍል የማይመለስ 500 ብር /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፤ የግንባታ ዕቃ አቅርቦት እና የህትመት ውጤት በተመለከተ 15 ተከታታይ ቀናት ሆኖ የሰነድ መግዣ ብር የማይመለስ 300(ሶስት መቶ ብር ብቻ) ይሆናል።
8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከኦርጅናሉ የጨረታ ሰነድ ጋር ማያያዝ ይኖርበታል። ጨረታ በሚያስገቡበት ጊዜ ዋና የጨረታ ሰነድ እና ኮፒውን ለየብቻው በፖስታ በማሸግ እንደገና ሁለቱንም በአንድ ላይ በትልቅ ፖስታ በጥንቃቄ በሰም በማሸግ የድርጅቱ ስም፣ አድራሻውንና ማህተም በመምታት በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
9. የሕንፃ ግንባታ ሥራ ለማሠራት በተመለከተ የጨረታው ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታው ማስታወቂያ በወጣበት በመጨረሻው 22ኛው የሥራ ቀን ፤ የግንባታ እቃ አቅርቦት እና የህትመት ውጤት በመጨረሻ በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ታሽጎ 4፡30 በዕለቱ ይከፈታል።
10. ሆስፒታሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
11. ሆስፒታሉ ቫት/7.5/ እና ዊዝ ሆልድ (3%) ቆርጦ የሚያስቀር መሆኑን እንገልፃለን።
12. የግንባታ እቃው ሆስፒታሉ በሚመርጠው ባለሙያ ተረጋግጦ ገቢ ይሆናል።
13. አስፈላጊ መረጃ ከፈለጉ በሆስፒታሉ ግዥ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ስልክ ቁጥር 033 111 7670 መደወል ይችላሉ።
14. ለአንድ አመት የሚቆይ የህትመት ውጤት ውድድሩ በሎት የሚካሄድ መሆኑን እናሳውቃለን።
15. የሕንፃ ግንባታ ሥራ በተመለከተ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ እና የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት።
የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
Tender details
- Deadline: 2026-09-05
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-09-05 12:00
- Bid opening (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
- Region: Amhara
- Publishing entity: Dessie General Specialized Hospital
- Bid bond: 2%
- Bid document price: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Published on: Addis Zemen (Aug 15, 2026)
- Posted at: 2026-08-15T09:01:37.000Z