Printing and Publishing

የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሃብት ልማት ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን ላይ ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር 001/2019

የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሃብት ልማት ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት የተለያዩ ሎቶች ላይ ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት፤

  • ሎት 1፡-የህትመት ስራዎች
  • ሎት 2፡-የዲኮር እና መድረክ ዝግጅት
  • ሎት 3፡-የመኪና ኪራይ
  • ሎት 4፡-የጉልበት ስራዎች
  • ሎት 5፡-የከባድ መኪና ጥገና
  • ሎት 6 -የከባድ መኪና ጎማ ጥገና (ጎሚስታ)
  • ሎት 7፡-የከባድ መኪና እጥበት
  • ሎት 8፡-ኤሌክትሮኒክስ ጥገና
  • ሎት 9፡-የከባድ መኪና መለዋወጫ እቃዎች
  • ሎት 10-መኪና ጥገና /የቢሮ/
  • ሎት 11፡-የምድረ ግቢ የጽዳት አገልግሎት ግዥ
  • ሎት 12፡- የካሜራ ባትሪዎች እና ተዛማጅ እቃዎች

በጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርት አሟልተው በጨረታው መወዳደር ይችላል።

1. የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት እንዲሁም አቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. በግብር አመቱ ተገቢውን የታክስና የግብር ግዴታ የተወጡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የገቢዎች ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤

4. የብቃት ማረጋገጫ ለሚያስፈልጋቸው ሎቶች የብቃት ማረጋገጫ ሰነዶችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. ከወጣው ጨረታ ውስጥ ብር 100,000.00 / አንድ መቶ ሺህ ብር) በላይ ዋጋ በማቅረብ በጨረታው የሚሳተፍ ማንኛውም የአገር ውስጥ ተጫራች የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ወረቀት ኮፒ ማያያዝ ይኖርባቸዋል ።

6. ጨረታው በአንድ ኤንቨሎፕ የሚቀርብ ሆኖ ኦርጅናል ዶክመንት እና ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ ፖስታ በማጠቃለል ኮ/ቀ/ክ/ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 705 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርበታል።

7. ጨረታ ሰነዱን በስራ ሰዓት ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሃብት ልማት ፑል የአስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 705 ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 500.00 / አምስት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።

8. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሰንጠረዥ ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሰረት በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ብቻ በኮ/ቀ/ክ/ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት በሚል በማዘጋጀት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

ሎት

የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ገንዘብ መጠን

1. የህትመት ስራዎች

20,000

2. የዲኮር እና መድረክ ዝግጅት

20,000

3. የመኪና ኪራይ

20,000

4. የጉልበት ስራዎች

20,000

5. የከባድ መኪና ጥገና

30,000

6. የከባድ መኪና ጎማ ጥገና (ጎሚስታ)

10,000

7. የከባድ መኪና እጥበት

10,000

8. ኤሌክትሮኒክስ ጥገና

10,000

9 የከባድ መኪና መለዋወጫ እቃዎች

50,000

10. መኪና ጥገና የቢሮ

25,000

11.የምድረ ግቢ የጽዳት አገልግሎት ግዥ

20,000

12 የካሜራ ባትሪዎች እና ተዛማጅ እቃዎች

20,000

ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚያው ቀን ጥዋት 4፡30 የሚከፈት ሲሆን ነገር ግን 11ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።

9. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

10. ተጫራቾች ሎት 1 የህትመት ስራዎች ላይ ለሚወዳደሩ ተጫራቾች የዕቃ ናሙና/sample የጨረታ ጊዜው ሳያልቅ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።

11. ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርበው ጨረታ ሰነድ ስርዝ ድልዝ ኖሮት ካልተፈረመ፣ ፍሉድ ተጠቅሞ በጉልህ የማይነበብ ከሆነ ከውድድር ወጪ ይሆናሉ።

12. መ/ቤቱ ከአሸናፊው ተጫራች ውል ከመፈረሙ በፊት በአሸናፊ ተጫራች አቅርቦት መጠን ላይ የተገኘው ዋጋ ሳይቀየር እስከ 20% መጨመር ወይም የመቀነስ የሚችል ይሆናል።

13. የጨረታውን አካሄድ ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጪ ፤ለወደፊትም በመንግስት ግዥ እንዳይሳተፉ እና ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና እንደሚወረስ ማውቅ አለባቸው።

አድራሻችን፡- ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ህንጻ 7ኛ ፎቅ ቢ/ቁ 705 የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን

አድራሻ፡- ቤቴል አደባባይ ወረድ ብሎ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አጠገብ

ስልክ ቁጥር፡- 0118 340 591

የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-27
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-27 12:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Kolfe Keranio Sub City Public Service and Human Resource Development
  • Buyer address: ቤቴል አደባባይ ወረድ ብሎ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አጠገብ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Published on: Addis Zemen (Aug 15, 2026)
  • Posted at: 2026-08-15T09:15:57.000Z
← Back to all tenders