Spare Parts and Car Decoration Materials
በአብክመ በምስ/ጎ/ዞን/አዋበል/ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በተለያዩ ሴ/መ/ቤቶች በ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል ከመደበኛ በጀት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ በምስ/ጎ/ዞን/አዋበል/ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በተለያዩ ሴ/መ/ቤቶች በ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል ከመደበኛ በጀት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፣
- ሎት 1. የመኪና መለዋወጫ ዕቃ፣
- ሎት 2. የመኪና ጎማ ከነመሰል ካላማዳሪው፣
- ሎት 3. የመኪና ጥገና፣
- ሎት 4. የእንስሳት መድሃኒት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟላ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው
3. ከሎት 4. የእንስሳት መድሃኒት በስተቀር የጨረታ ተሳታፊዎች የሚሞሉት ዋጋ ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የቫትNATI ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ/ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
5. የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ/እስፔስፍኬሽን ከእያንዳንዱ ሎት/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የመሸጫ ዋጋ የማይመለስ ብር 100/ አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 03 መግዛት ይቻላል፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሎት 1 እና ሎት 2 ብር 15,000/አስራ አምስት ሺ ብር/ አንዲሁም ሎት 3 እና ሎት 4 ብር 5,000/ አምስት ሺ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ/ሲ.ፒ.ኦ/ በመሂ አንድ እና በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ድረስ በጽ/ቤቱ በግዥ ቡድን ወይም ቢሮ ቁጥር 05 በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 3፡30 ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
9. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 05 በ16ኛው ቀን እስከ 3፡30 ማስገባት የሚቻል ሲሆን በ4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
11.በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 05 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 772 0630 / 0004 በመደወል ማግኘት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው ሲከፈትም ሆነ ከተከፈተ በኋላ የሚገኝ ከጥቃቅን ስህተቶች በስተቀር ከባድ ስህተቶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
12. መ/ቤቱ ጨረታውን 20% የመቀነስ ወይም የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
13. የእቃውን ዋጋ የሚሞላው ከጨረታው ጋር በምናቀርበው ስፔስፊኬሽን መሰረት ሆኖ እስፔስፊኬሽን ቀጥሮ መሙላት የተከለከለ ነው፡፡
14. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
15. አሸናፊው ያሸነፋቸውን እቃዎችን አዋ/ወ/ገ/ጽ/ቤት ድረስ ያለማንጠባጠብ አጠቃሎ ማቅረብ ይጠበቅበታል።
16. አሸናፊው በሎት ይለያል በሎቱ ውስጥ የተጠቀሱት ዝርዝሮች በሙሉ ዋጋቸው መሞላት ይኖርባቸዋል፡፡
17. ማንኛውም የሚቀርበው እቃ ኦርጅናል መሆን አለበት፡፡
18. የመኪና ጥገና አገልግሎት የመኪና መለዋወጫ እቃ አሸናፊ የሆነ አካል ወይም ድርጅት አገልግሎቱን ወይም ግዥውን በውሉ መሰረት እስከ ሰኔ 30/2019 ዓ/ም ድረስ ማቅረብ ወይም መፈፀም አለበት፡፡
በአብክመ በምስ/ጎ/ዞን የአዋበል ወረዳ ገ/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-31
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በ3፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-31 12:00
- Bid opening (note): ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: East Gojam Administration Zone Awabel Woreda FEDB
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 15, 2026)
- Posted at: 2026-08-15T09:44:20.000Z