Textile, Garments and Uniforms

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአ/ከ/ክ/ከተማ ወረዳ 12 የኮልፌ ጤና ጣቢያ ለ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ እቃዎችና አገልግሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የአንደኛ ዙር ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ የመለያ ቁጥር ኮ/ጤ/ጣ 001/3686/18

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአ/ከ/ክ/ከተማ ወረዳ 12 የኮልፌ ጤና ጣቢያ ለ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ እቃዎችና አገልግሎቶች

  • በሎት1፡- ደንብ ልብስ ፣
  • በሎት 2፡ አላቂ የፅዳት እቃዎች፣
  • በሎት 3፡-አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ፣
  • በሎት 4 ፡- ቋሚ የእንጨት እና የብረት ውጤቶች ፣
  • በሎት 5 ፡- ቋሚ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
  • በሎት 6፡- የተለያዩ የህትመት ሥራዎች ፣
  • በሎት 7 :- የህንፃ የግንባታ ዕቃዎች፣መለዋዋጫ፤ልዩ ልዩ መሳሪያዎች፣
  • ሎት8: የሰራተኞ ካፌ አገልግሎትለመስጠት የወጣጨረታ ፣
  • ሎት 9፡- የሮቶ እጥበት አገልግሎት የሚሰጥ፣
  • ሎትıo፡- የመድሀኒት እና የላብራቶሪ ሪኤጀንት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት፡-

  1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣የንግድ ምዝገባ ፈቃድ፣ የግብር ክሊራንስ፣በአቅራቢነት ሊስት መመዝገባቸውን የሚያሳይ የምስክር ወረቀት ፣ የቫት ተመዝጋቢነት መረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. ለጨረታ ማስከበሪያ CPO-በ0.5 ፕርሰንት ተሰልቶ በሎት 1፡10,000ብር በሎት2፡9,000ብር በሎት 3፡-15,000ብር በሎት 4፡-9,000 በሎት 5፡14,000 በሎት 6፡4,000 ብር ሎት 7፡9,000 ሎት 8፡-5,000ብር ሎት9፡-2000ብር ሎት 10፡-20,000 ብር በባንክ በተረጋጠ CPO በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በወረዳ 12 ኮልፌ ጤና ጣቢያ ስም ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
  3. የጨረታ ሰነድ መግዣ ዋጋ ብር 300 (ሦስት መቶብር) በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ጀምሮ 2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት በኮልፌ ጤና ጣቢያ ግዥ ቡድን ቢሮ አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 80 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  4. የጨረታ አሸናፊ የውል ማስከበሪያ ባሸነፉበት ዋጋ ብር 10% በባንክ በተረጋገጠ CPO በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በወረዳ 12 ኮልፌ ጤና ጣቢያ ስም የሚያሰሩ ይሆናል።
  5. የሚጫረቱባቸውን ዕቃዎችን በጥራት ለመለየት እንዲያስችለን ናሙና የሚያስፈልጋቸውን ግብዓቶች እንዲሁም ናሙናውን ለማምጣት የማይችሉ ዕቃዎች ከሆኑ የፎቶ ሳንፕል። የእቃውን ዝርዝር በማያያዝ እስከጨረታ መክፈቻ ቀን ድረስ ብቻ ማቅረብ አለባችሁ።
  6. የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ማስታወቂያው ከወጣት ዕለት ጀምሮ እስከ 10ኛው የሥራ ቀን እስከ ቀኑ 11፡ዐዐ ድረስ በኮልፌ ጤና ጣቢያ ግዥ ቡድን ቢሮ አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 80 መግዛት ይችላሉ።
  7. የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣ በ11ኛው የስራ ቀን 2፡30 አስከ 4፡00 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ታሸጎ በዛው ዕለት 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ኮልፌ ጤና ጣቢያ አራተኛ ፎቅ አዳራሽ ይከፈታል። 11ኛው ቀን የእረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
  8. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ዋናውን እና ኮፒውን /ቴክኒካል ኦርጅናል እና ኮፒ፣ ፋይናሻል ኦርጅናል ና ኮፒ በተለያያ ፖስታ በማሸግ አራቱን ሰነድ የያዘውን ፖስታ በአንድ ፖስታ በማሸግ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባች። ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ወይም ፍሉድ መኖር ከውድድሩ ያሰርዛል፤ በተጨማሪም ማንኛውም ተጫራች የገዛውን መደበኛ የጨረታ ሰነድ በተጫራች መሞላት ያለበትን ክፍሎች በሙሉ የመሙላት እና ሙሉውን ሰነድ ማስገባት ይኖርበታል፤ ይህን ያላደረገ ተጫራች በቅድመ ጨረታ ልየታ ውድቅ እንደሚሆን ከወዲሁ እናሳውቃለን።
  9. ተጫራቾች የጨረታውን አሸናፊነት ከተገለፀ ከ7 የቅሬታ ቀናት በኋላ ቀርበው ውል ካልፈፀሙ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
  10. የጥቃቅንና አነስተኛ ለሆኑ ተጫራቾች አምራች ስለመሆናቸው እንዲሁም ጨረታ የወጣበትን ቀን እና ቁጥር የሚያመርቱትን ሎት በመግለፅ ከሚመለከተው አካል ደብዳቤ ማምጣት አለባችሁ።
  11. በሎት፡-8 ላይ የምትጫረቱ ተጫራቾች ዋጋ ማቅረቢያውን ከመሙላታችሁ በፊት ተቋሙ ለሰራተኞቹ የመስተንግዶ ዋጋ ተመጣጣኝ እንዲሆን ሲባል የውሃ ፣ የመብራት፣ የቤት ኪራይ ፣የተለያዩ የካፍቴሪያ ዕቃዎች ሌሎችም ድጎማዎች ስላሉት ማየት ይኖርባቸዋል። ለሎት 10 ፡- መድሀኒት እና የላብራቶሪ ሪኤጀንት የምትጫረቱ ተጫራቾች የአገልግሎት ዘመኑ ቢያንስ ከ2 ዓመት በላይ መሆን አለበት ።
  12. መስሪያ ቤቱ የሚገዙ ዕቃዎችና ተያያዥ አገልግሎቶች መጠን ሊጨመር ወይም ሊቀንስ የሚችልበት መቶኛ 20%.
  13. ጨረታው ከተዘጋ በኃላ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 12 የኮልፌ ጤና ጣቢያ ኮልፌ አጠና ተራ ከፖሊስ ጣቢያው ከፍ ብሎ

ስልክ ቁጥር፤-011 -273-8855  011-280-1021 በመደወልመጠየቅ ይቻላል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአ/ከ/ክ/ከተማ ወረዳ 12 የኮልፌ ጤና ጣቢያ


Tender details

  • Deadline: 2026-08-27
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን 2፡30 አስከ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-27 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Kolfe Health Post
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 15, 2026)
  • Posted at: 2026-08-15T09:50:49.000Z
← Back to all tenders