Textile, Garment and Leather

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮ በኮ/ቀ/ክ/ከተማ በወረዳ 10 መሠረተ ዕድገት ቅ/አ/አ/መ/ደረጃ ት/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ለመሥሪያ ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የግዢው መለያ ቁጥር NCB/00IU/2019/26

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮ በኮ/ቀ/ክ/ከተማ በወረዳ 10 መሠረተ ዕድገት ቅ/አ/አ/መ/ደረጃ ት/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ለመሥሪያ ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንድትሳተፉ ጥሪ እናቀርባለን።

የሎት ቁጥር

የአገልግሎት ዓይነት

የጨረታ ማስከበሪያ

ሎት 1

/6211/ ደንብ ልብስ

20000

ሎት 2

/6212/ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች

20000

ሎት 3

/6215/ አላቂ የትምህርት ዕቃዎች

20000

ሎት 4

/6213/ የሕትመት ሥራዎች

5000

ሎት 5

/6214/ አላቂ የሕክምና ዕቃዎች

5000

ሎት 6

/6218/ የአላቂ የፅዳት ሥራዎች

15000

ሎት 7

/6244) የጥገና የቧንቧና ኤሌትሪክ ዕቃዎች

15000

ሎት 8

/6313/ የኤሌክትሮኒክስ ቋሚ ዕቃዎች

20000

ሎት 9

/6314/ ሌሎች ቋሚ ዕቃዎች

20000

ሎት 10

/6219/ መጽሐፍት

6000

ሎት 11

/6223/ የላብራቶሪ እቃዎች

5000

ሎት 12

/6243 የኮምፒዩተር፣ ፕሪንተር፣ ማባዣ ማሽን፣ የኮፒ ማሽን የጥገና ሥራ

10000

በዚህም መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

1. ተጫራቾች የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባወጣው የእቃ አቅራቢዎች ዝርዝር የተካተቱና ማስረጃ የሚያቀርቡ፣ እንዲሁም በገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ ለዚህም በመስኩ/በዘረፉ የተሰማሩ መሆኑን የሚገልጽ የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና ቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡ እንዲሁም ተጫራቾች ያልተቀጡ (እንዲወዳደሩ ያልታገዱ) መሆን አለባቸው፡፡

2 . ተጫራቾች የተደራጁ ጥቃቅን እና አነስተኛ ከሆኑ ካደራጃቸው አካል ወቅታዊ የሆነ የድጋፍ ደብዳቤ በት/ቤቱ ስም በቅድሚያ ማፃፍ አለባቸው፤ እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ የዋስትና ደብዳቤ በት/ቤቱ ስም በትክክለኛ አድራሻ ከሚመለከታቸው አካል ማፃፍ አለባቸው፡፡

3. ተጫራቾች የቲን መለያ ቁጥር ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡

4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት በኮ/ቀ/ክ/ከወ/10 መሰረተ ዕድገት ቅ/አ/አ/መ/ደ/ት/ቤት በአካል በመገኘት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 250.00 /ሁለት መቶ ሃምሳ ብር/ በመክፈል ከት/ቤቱ ግዥ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡

5. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ሲየስገቡ በሚወዳደሩበት ዘርፍ ከላይ በሰንጠረዥ የተገለፀውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ በት/ቤቱ ስም በማሰራት ማሳያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡

6. ማንኛውም ተጫራች የሚያስገባው የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ በፍሉድ የጠፋ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

7. ማንኛውም ተጫራች በሰነዱ ላይ ናሙና እንዲቀርብባቸው ለሚጠየቁ ዕቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ማቅረብ አለበት፡፡

8. ተጫራቾች በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡

9. አሸናፊው እንደታወቀ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

10. ተጫራቾች እያንዳንዱን የሚጫረቱበትን ዋጋ ቫትን ጨምሮ በመግለፅ ሥልጣን ባለው አካል ፊርማ፣ ማህተም ያረፈበትና ሙሉ አድራሻቸውን በመጥቀስ በታሸገ ፖስታ (ዋናውንና ኮፒውን 2 ፖስታ በማድረግ) የጨረታ ሰነዱን ከነመመሪያ በመሰረተ ዕድገት ቅ/አ/አ/መ/ደ/ት/ቤት የግዥ ቢሮ በመገኘት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡

11. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ማስታወቂያ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሉበት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ በአል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሰዓቱ ካልተገኙ የመሥሪያ ቤቱ ጨረታውን የመከፈት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

12. በዚህ ጨረታ ላይ የሚቀርቡ ማንኛውም የመወዳደሪያ ዋጋ ቢያንስ ለ6 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል፡፡

13. በአነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት በአዋጅ መሰረት የተቋቋሙ አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት ከአገር ውስጥ አቅራቢዎች ጋር በሚያደረጉት ውድድር በግዥ በመመሪያው መሰረት ልዩ አስተያየት ይደረግላቸዋል፡፡

14. የጨረታ መዝጊያ ዕለትና ሰዓት ካለፈ በኋላ የሚቀርብ ማንኛውም ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡

15. ት/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- ከጦርኃይሱች ወደ ኮልፌ በሚወስደው መንገድ ከሆላንድ ኤምባሲ ከፍ ብሎ

ስልክ፡- 0913346653/0921313443

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ መሰረተ ዕድገት ቅድመ አንደኛ፤ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት  


Tender details

  • Deadline: 2026-08-28
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ማስታወቂያ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-28 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ማስታወቂያ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Meserte Edget Kindergarten & Elementary School
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 250.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published on: Addis Zemen (Aug 16, 2026)
  • Posted at: 2026-08-17T07:52:25.000Z
← Back to all tenders