Cleaning and Janitorial Equipment and Service
በሲዳማ ብ/ክ/ መንግስት በሀዋሳ ከተማ የአዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል ለ2019 በጀት ዓመት የሚሆን የተለያዩ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በሲዳማ ብ/ከ/ መንግስት በሀዋሳ ከተማ የአዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል ለ2019 በጀት ዓመት የሚሆን ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1 የህዝብ መድኃኒት ቤት መድኃኒት ግዥ
- ሎት 2 አዳሬ ግቢ መድኃኒት ግዥ
- ሎት 3 ፅህፈት መሳርያ ግዥ
- ሎት 4 ፅዳት ዕቃዎች ግዥ
- ሎት 5 ላቦራቶሪ ሪኤጀንት ግዥ
- ሎት 6 ደንብ ልብስ ግዥ
- ሎት 7 ህንፃ መሳርያ ግዥ
- ሎት 8 ዘይትና ቅባት ግዥ
ተጫራቾች
ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለው፤
የዘመኑን የ2018 ዓ/ም ግብር የከፈሉ፤
እንደ አስፈላጊነቱ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣
በመስኩ የንግድ ሥራ የተሰማሩ፤
የጨረታ ማስከበሪያ በሆስፒታሉ ስም የተሠራ CPO 10,000 (አስር ሺህ ብር) ማስያዝ የሚችሉ፣ የጨረታ ሰነዱ አዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል ግዥ ክፍል በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) የጨረታ ሰነድ አንድ ኦርጅናል ሁለት ኮፒ ለየብቻ ፋይናንሻል እና ቴክንካል በሰም በታሸገ ኤንቭሎፕ በድምሩ 6 ፖስታ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ እንዲያስገቡ ሆኖ በ10ኛው ቀን ከረፋዱ 6፡30 ሰዓት ላይ የጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ይታሸግና ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ይህ ቀን ቅዳሜ ወይም እሁድ እንዲሁም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው በሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ
ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙ ጨረታው ተከፍቶ ውሳኔ ይሰጣል።
መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው።
ፋይናንሻል ሰነድ ከሆስፒታሉ የተዘጋጀው ሰነድ ላይ ብቻ ዋጋ መሙላት ይገባል።
በፋይናንሻል ሰነድ ላይ የዋጋ መሙያን መቀየርም ሆነ ከተጠየቀው ይዘት ውጪ መለኪያ በመቀየር ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ አይቻልም።
ለተጨማሪ መረጃ የስልክ ቁጥር 0462122370
በሲዳማ ብ/ክ/ መንግስት በሀዋሳ ከተማ የአዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል
Tender details
- Deadline: 2026-08-25
- Bid closing time: 12:30
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከረፋዱ 6፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-25 14:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከረፋዱ 8፡30 ሰዓት
- Region: Sidama
- Publishing entity: Adare General Hospital
- Bid bond: 10,000.00 (አስር ሺ ብር)
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 16, 2026)
- Posted at: 2026-08-17T09:31:09.000Z