Others
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 አስተዳደር ጽ/ቤት በ2019 በጀት አመት ለወረዳው የሚያስፈልገውን የተለያዩ ዕቃዎች ኪራይ በግልፅ ጨረታ አወዳደድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
1ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 አስተዳደር ጽ/ቤት በ2019 በጀት አመት ለወረዳው የሚያስፈልገውን የተለያዩ ግብዓት በሎት አከፋፍለው
1. የተለያዩ እቃዎች ኪራይ በጨረታ ቁጥር፡-01/2019 የ2019 በጀት ዓመት በስሩ ለሚገኙት የተለያዩ ጽ/ቤቶች መገልገያ የሚሆኑ የተለያዩ ዕቃዎች ኪራይ በግልፅ ጨረታ አወዳደድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በዚህ ስራ ላይ የተሰማራችሁ አቅራቢዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ቀርባችሁ መወዳደር እንደምትችሉ እናሳውቃለን።
የጨረታው መስፈርት
1. በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው፧
2. የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈለና ክሊራንስ ያለው እና የዘመኑ ንግድ ፍቃዱን ያሳደሰ፤
3. VAT ተመዝጋቢ የሆነ እና ህጋዊ ደረሰኝ ያለው
4. በመንግስት ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገበበትን መረጃ ማቅረብ የሚችል ፧
5. በስራ ክህሎት የተደራጁ ኢንተርፕራይዞች በሀገር ውስጥ ምርቶች ላይ ብቻ ልዩ ድጋፍ የሚደረግላቸው ሲሆን ይህም የሚደረገው ከአደራጃቸው ጽ/ቤት ኃላፊ በተፈረመ የድጋፍ ደብዳቤ ይሆናል። ከስራ ዘርፉ እና ከሀገር ውስጥ ምርቶች ውጭ ለሆኑት እንደማንኛውም ነጋዴ የሚስተናገዱ ይሆናል።
6. የጨረታውን ሰነድ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ቆርቆሮ ፋብሪካ አካባቢ ወረዳ 2 አስተዳደር ህንጻ ፋይናንስ ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 203 በመገኘት ከጠዋቱ 2፡30 እሰከ ከሰአት 11፡30 በብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በካሽ በመግዛት መጫረት ይችላሉ።
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ/CPO/ 15000 (አስራ አምስት ሺህ ብር) በኢትዮጵያ ብር ማስያዝ ይኖርባቸዋል የጨረታው ማስከበሪያ በየሎቱ በተጠየቀው መሰረት በሲፒኦ (CPO) ዋስትና በወረዳ 02 አስተዳደር ጽ/ቤት በሚል በማሰራት በዋናው ሰነድ ውስጥ ማቅረብ አለባቸው።
8. የጨረታ ማስከበሪያ ያላስያዘ በጨረታው ሰነድ በቅድመ ምርመራ ውድቅ ይሆናል።
9. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ በግልፅ የሚታይ እና የሚነበብ የዕቃውን ዓይነት ስም ፤የተመረተበት ሀገር የሞዴሉን ቁጥር፤ የተመረተበትን ጊዜ ያካተተ መሆን ይገባዋል።
10. ግዥ ፈጻሚው አካል አሸናፊ ተጫራቾች በሚያቀርቡት እቃ ወይም አገልግሎት ላይ እንዳስፈላጊነቱ 20% መቀነስ ወይም መጨመር ይቻላል።
11. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዕቃ እስከ መ/ቤቱ ግምጃ ቤት/ ንብረት ክፍል/ድረስ የመጓጓዣ አካትተው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
12. የጨረታው ሰነድ በሁለት ፖስታ የሚቀርብ ሆኖ ዋና እና ፎቶ ኮፒ የጨረታው ሰነድ መቅረብ አለባቸው እነዚህም ሰነዶች በጨረታው ሲቀርቡ ድርጅቶቹ ወይም ህጋዊ ውክልና ባለው አካል መፈረም አለባቸው በሰነዶቹ እና ፓስታዎቹ ላይ የድርጅቱ /አቅራቢው/ ማህተም ሊኖር ይገባል ፤ ሰነዱ በሚሞላበት ወቅት ስርዝ ድልዝ (ለማንበብ አስቸጋሪ) ከሆነ ከውድድር ውጭ ያስደርጋል።
13. ጨረታውን ለመገምገም በሥራ ላይ የሚውሉትን ዘዴዎች ለዚሁ ግምገማ የሚያገለግሉትን መስፈርቶች እና እያንዳንዱ መስፈርት የሚኖረውን ድርሻ እንዲሁም ሁለት እና ከሁለት በላይ የሆኑ ዕጩ ተወዳዳሪዎች በግምገማ እኩል በሆኑ ጊዜ አሸናፊን ለመለየት በግዥ መመሪያው መሰረት የሚለይ ይሆናል።
14. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል የተከለከለ ነው።
15. የጨረታውን አካሄድ ለማዛባት የሚሞክር ማንኛውም ተጫራች ከጨረታው ውጪ እንደሚሆን፣ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ /ሲፒኦ/ እንደሚወረስ እና ለወደፊቱም በመንግስት ግዥ ጨረታ እንደማይሳተፉ ለሚመለከተው አካል ሪፖርት እንደሚደረግ ማወቅ ይኖርበታል፤
16. የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ግዥውን 10% በብር/ሕጋዊ CPO/በወረዳ 02 አስተዳደር ጽ/ቤት / woreda 02 administration office/በሚል በማሰራት ማስያዝ የሚችል።
17. ጨረታው በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ተጫራቹ /ህጋዊ ወኪል/ በተገኘበት ተዘግቶ በ4፡30 በአቃ/ቃ/ክ/ከ/ወ 02 ህዳሴ አዳራሽ የሚከፈት ሲሆን ተጫራቹ /ህጋዊ ወኪሉ/ ያለመገኘት የጨረታ አከፋፈት ላይ ተፅኖ አያመጣም። ሆኖም ግን 11ኛው ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል
18. ውድድሩን ያሸነፈ ተወዳዳሪ ውድድሩን ማሸነፉ ከታወቀ ቀን እና የቅሬታ እና አቤቱታ 7 ቀን ካለቀ በኋላ በ15 (አስራ አምስት) ቀን ውስጥ በአካል ቀርቦ የውል ስምምነት መፈረም አለበት ።
19. ተጫራቾች በጨረታው ሰነድ ላይ የማብራሪያ ወይም የማሻሻያ ጥያቄ ካላቸው የጨረታ ሰነዱ የመክፈቻ ቀን ከሶስት የስራ ቀናት በፊት በጽሁፍ ማቅረብ ይችላሉ።
20. ተጫራቾች በጨረታው አፈፃፀም ሂደት ላይ ቅሬታ ካላቸው ለጽ/ቤት ኃላፊ በጽሁፍ ማቅረብ ይችላሉ።
21. ክፍያን በተመለከተ አቅራቢው ዕቃውን ሙሉ በሙሉ በጥራት እና በናሙና መሰረት ማቅረቡ በቴክኒክ ኮሚቴ ተረጋግጦ ወደ ንብረት ክፍል ገቢ ሲሆን የሚከፈል ይሆናል፤
22. መደበኛ የጨረታ ሰነዱ በራሱ አንድ የጨረታ መመሪያና ውል መሆኑን ተጫራቾች መረዳት ይገባቸዋል፤
23. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ውድድሩን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ይሆናል።
24. አድራሻ - አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ቆርቆሮ ፋብሪካ ሳይደርሱ ወረዳ 2 አስተዳደር ህንጻ ፋይናንስ ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 203 ይገኛል፤
25. ለተጨማሪ መረጃ የስልክ ቁጥር፤- 011 462 2360 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 አስተዳደር ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-28
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-28 10:30
- Bid opening (note): ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Akaki Kality Sub City Woreda 2 Administration Office
- Bid bond: 15,000.00 ብር
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 16, 2026)
- Posted at: 2026-08-17T11:16:18.000Z