House and Building Sale
የክርስቲያን ሚሽነሪ ፌሎውሺፕ ኢንተርናሽናል (CMFI) ሲጠቀምባቸው የነበሩትን ሕንፃዎች ቪላ ቤቶች፣ አፓርትመቶች እና ተያያዥ ንብረቶችን በጥቅል ባሉበት ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት (CSO) ብቻ በጨረታ አወዳድሮ ለማስተላለፍ (ለመሸጥ) ይፈልጋል
Description
የንብረቶች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የክርስቲያን ሚሽነሪ ፌሎውሺፕ ኢንተርናሽናል (CMFI) ሲጠቀምባቸው የነበሩትን ሕንፃዎች ቪላ ቤቶች፣ አፓርትመቶች እና ተያያዥ ንብረቶችን በጥቅል ባሉበት ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት (CSO) ብቻ በጨረታ አወዳድሮ ለማስተላለፍ (ለመሸጥ ) ይፈልጋል።
1.1 ንብረቶቹ የሚገኙበት አድራሻ፡- በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሸገር ከተማ አስተዳደር መልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ ኖኖ ወረዳ የቤት ቁጥር አዲስ ወይም በተለምዶ አጠራር ታጠቅ ደስታ መንደር ወደ ፌስቱላ ሆስፒታል ሕሙማን ማገገሚያ ማዕከል በሚወስደው ዋና መንገድ ላይ ይገኛል።
1.2 ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈለግ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት መወዳደር ይችላል።
1.3 ተጫራቶች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመንና ሪፖርተር ጋዜጦች ላይ ከወጣበት ከነሐሴ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለአስራ አምስት የሥራ ቀናት በሥራ ሰዓት ኦርጅናል ማህተም እና ፊርማ ያለበትን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል የድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤት በሚገኝበት በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 የቤት ቁጥር 280 በተለምዶ ዘነበ ወርቅ አካባቢ ታቦት ማደሪያ ፊት ለፊት ከሚገኘው ቢሮው በአካል መጥተው መግዛት ይቻላል።
1.4 የጨረታው ሰነዱ (የጨረታ ቁጥር 04/2018) ብዙ ዝርዝር ገዳዮችን የያዘ መሠረታዊ ሰነድ በመሆኑ መግዛት እጅግ አስፈላጊ ነው።
1.5 ተጫራቶች ለጨረታ የሚያቀርቡት ዋጋ ከጨረታው ሰነድ ጋር በተያያዘው የዋጋ ማቅረቢያ ላይ ከሞሉ በኋላ ባቀረቡት ዋጋ ላይ በመንተራስ 20%(ሀያ በመቶ) የማያንስ የጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ኤም.ኤፍ.አይ (CMF) ስም በባንኩ በተረጋገጠ ክፍያ መዘዣ (CPO) በታሸገ ኤንቨሎፕ ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር አያይዘው እስከ ጳጉሜ 3 ቀን 2018 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። CPO (ሲ.ፒ.ኦ) ከ 20%(ሀያ በመቶ) ካነሰ የጨረታ ሰነዱ ውድቅ ይደረጋል።
1.6 የጨረታው ሳጥን የሚቀመጠው በተ.ቁ 1.1 ተቀምጦ ባለው አድራሻ ንብረቶች በሚገኙበት ታጠቅ ደስታ መንደር የቤት ቁጥር አዲስ ኖኖ ወረዳ መልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ ሸገር ከተማ አስተዳደር በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ነው።
1.7 የጨረታው ሳጥን ጳጉሜ 03 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ የዕለቱ ዕለት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከረፋዱ 4፡15 ሰዓት ይከፈታል።
1.8 አሸናፊው ወዲያውኑ እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ታሳቢ ቀሪውን በ15 ቀናት ውስጥ ከፍለው ንብረቱን መረከብ አለባቸው።
1.9 በተራ ቁጥር 1.7 መሰረት ጨረታውን አሸንፈው በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ውስጥ ከፍለው የማይረከቡ ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ያስያዙት (CPO) ቢድ ቦንድ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል።
1.10 የጨረታው አሸናፊ ከስም ዝውውር ጋር የተያያዘው ግብር እና ማንኛውም በመንግሥት የሚጠየቁትን ክፍያዎች ይሸፍናሉ፡፡ ውዝፍ ዕዳ ካለ ግን አጫራች (ሻጭ) ይከፍላል።
1.11 የጨረታው ለማያሸንፉ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲ.ፒ.ኦ (CPO) የጨረታ ግምገማ ውጤት ከተገለፀ በኋላ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
1.12 የጨረታ ሰነድ ሽያጭ ማስታወቂያው በጋዜጦች ከወጣበት ከነሐሴ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት (አስራ አምስት ቀናት) እስከ ጳጉሜ 02 ቀን 2018 ዓ.ም 10፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ የሚቆይ ይሆናል።
1.13 በተጨማሪም በጨረታው ሰነድ ውስጥ የተጠቀሱት የተጫራቾች መመሪያን ትኩረት ሰጥቶ ተግባራዊ ማድረግ ከተጫራቾች ይጠበቃል።
1.14 የክርስቲያን ሚሽነሪ ፌሎሽን ኢንተርናሽናል (CMF) የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ፖ.ሳ.ቁ.2920
አዲስ አበባ
ስ.ቁ. 09 11 20 64 04 ወይም 09 44 35 45 19
የክርስቲያን ሚሽነሪ ፌሎውሺፕ ኢንተርናሽናል (CMFI)
Tender details
- Deadline: 2026-09-08
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-09-08 10:15
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Christian Missionary Fellowship International (CMFI)
- Bid bond: 20%
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 16, 2026)
- Posted at: 2026-08-17T11:31:33.000Z