Generators

የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ሲገለገልባቸው የነበሩ እቃዎች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር -- 01/22/27

የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ሲገለገልባቸው የነበሩ

  • ያገለገሉ የተለያዩ አቅም ያላቸው ጀነሬተሮች፣ 
  • ኮምፒውተሮች፣
  • ፕሪንተሮች፣ ዩፒኤሶች ፣
  • የብር መቁጠሪያ ማሽኖች፤
  • የተለያዩ የቢሮ ወንበሮች፣ ጠረጴዛዎች፣
  • ማስታወቂያ ታፔላዎች፣
  • የኤቲኤም ሴንተር መጠለያዎች፣
  • ያገለገሉ የመኪና ባትሪዎች፣
  • ያገለገሉ የመኪና ጎማዎች፣
  • የተቃጠለ የመኪና ዘይት አሉሚኒየም ፓርትሽኖች፣
  • ካውንተር እና ኬጂ፣
  • የቅርንጫፍ ከነ በርሜሎቹ ጋር፣
  • አሮጌ ጋዜጣዎች፣
  • ባዶ የቶነር እቃዎች፣ ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለዚህ ለመግዛት ለሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መመሪያዎች መከተል ይኖርባቸዋል -

  1. የዕቃዎቹ ዓይነትና ዝርዝር በጨረታው ሰነድ ላይ የሚገኝ በመሆኑ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ከነሐሴ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ነሐሴ 25 ቀን 2018 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት ወይም የግብር መለያ ካርድ ያላችሁ ተጫራቾች ቦሌ መንገድ የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ኢጆ ቅርንጫፍ ወይም በአቅራቢያዎ በሚገኝ የባንኩ ቅርንጫፍ በመሄድ ላገለገሉ ዕቃዎች ጨረታ ሰነድ መግዣ ብር 300.00 (ሦስት መቶ) በሂሳብ ቁጥር ETB1446500010001 በማስገባት ደረሰኙን በመያዝ የጨረታ ሰነዱን ቦሌ መንገድ ከአፍሪካ ኢንሹራንስ ፊትለፊት፣ ከባንኩ ህንጻ አጠገብ ራንግ ህንጻ 7ኛ ፎቅ ከባንኩ ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል መውሰድ ይችላሉ።
  2. የዕቃዎቹን ዓይነትና ዝርዝር ሁኔታ በአካል ማየት ለሚፈልጉ ተጫራቾች የከፈሉበትን ስሊፕ እና የጨረታ ሰነዱን በመያዝ ንብረቶቹ በሚገኙበት አንድ ቃሊቲ ገብርኤል በመጀመሪያው ቅያስ ወደ ቀኝ 200 ሜትር ገባ ብሎ ሀሴት አካዳሚ አጠገብ እና ሁለት ሱሉልታ አዲስ የተሰራዉ ክ/ከተማ ከዋና መንገድ ወደ ቀኝ 100 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው ፒልከን ተብሎ በሚታወቀው የባንኩ ግምጃ ቤት ውስጥ በመገኘት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን የገዙ ተጫራቾች ብቻ በተቀመጠው ፕሮግራም መሠረት ፒልከን ለሚገኘው ንበረት ነሐሴ 19፣ 21 እና 23 ቀን 2018 ዓ.ም ከጧቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ድረስ ሲሆን ቃሊቲ ገብርኤል ለሚገኘው ንብረት ነሐሴ 20 እና 22 ቀን 2018 ዓ.ም እንዲሁም ነሐሴ 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከጧት 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ሁለቱም ቦታ መጎብኘት ይችላሉ።
  3. እንዲሁም የተቃጠለ የመኪና ዘይት ከነበርሜሉ ያለበትን ሁኔታ ለመጎብኘት ቄራ በረት ከአልማዝዬ ሜዳ ወደ ጎፋ በሚወስደው ዋናው መንገድ 100 ሜትር እንደተጓዙ በቀኝ በኩል የባንኩ ጋራጅ ቅጥር ግቢ ውስጥ በማንኛውም የሥራ ሰዓት እስከ ነሐሴ 25 ቀን 2018 ዓ.ም 6፡00 ሰዓት ድረስ መጎብኘት ይችላሉ።
  4. ገዢዎች የሚገዙበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቬሎፕ እስከ ጨረታ መዝጊያ ነሐሴ 25 ቀን 2018 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስ ቦሌ መንገድ ራንግ ህንጻ ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል በአካል ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውን በመላክ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ በማስገባት መጫረት ይችላሉ።
  5. ባንኩ የሚከተለው የማወዳደሪያ ዘዴ በሰነዱ ሰንጠረዥ ላይ ንብረቶቹ እንደተዘረዘሩት ዓይነት በተናጠል መስመር በመስመር ሲሆን ባንኩ የተሻለ ሆኖ ካገኘም በጥቅል ወይም በጅምላ ያወዳድራል።
  6. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጠቅላላ መነሻ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር 10% (አስር በመቶ)ዉን በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፤ በተጨማሪም የጨረታ መነሻ ዋጋ ለሌላቸው የሚገዙበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  7. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሳይያያዝ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  8. ተጨራች የሚገዛበት የመግዣ ዋጋ በግልጽ በዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ በተቀመጠው መሠረት ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) 15% መካተቱን ወይም አለመካተቱን ለይቶ መጻፍ ይኖርበታል፤ ነገር ግን አሻሚ ቦታ ላይ ወይም ሁለቱም ቦታ ላይ ተመሳሳይ ዋጋ ከጻፈ እና ምንም ካልተገለጸ ባንኩ የቀረበው ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተካቶ እንደቀረበ ታሳቢ ያደርጋል።
  9. አሸናፊ መሆናቸው የተገለፀላቸው ተጫራቾች ያሸነፉትን ንብረት ሙሉ ክፍያውን በአምስት ቀናት ውስጥ ከፍለው ማንሳት ይኖርባቸዋል፤ ካልሆነ ግን ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፖኦ ውርስ ይደረጋል።
  10. ጨረታው ሰኞ ነሐሴ 25 ቀን 2018 ዓ.ም በ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዛው ዕለት ሰኞ ነሐሴ 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ራንግ ህንጻ 7ኛ ፎቅ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ተጫራቾች በተገኙበት የጨረታ ሰነዱ የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን።
  11. ባንኩ የተሸለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ (አ.ማ)

ስልክ ቁጥር 011 557 6174 ፖ.ሣ.ቁ 16936

ማህበረሰቡን ማጎልበት፣ ህይወትን መለወጥ


Tender details

  • Deadline: 2026-08-31
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-08-31 14:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Cooperative Bank of Oromia S.C.
  • Buyer address: Dembel City Center
  • Bid bond: 10%
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Reporter (Aug 16, 2026)
  • Posted at: 2026-08-17T12:32:05.000Z
  • Buyer website: https://coopbankoromia.com.et/
← Back to all tenders