Textile, Garments and Uniforms

የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ለ8ኛው ዙር የቡና ቤተሰብ ዓመታዊ ሩጫ የመሮጫ ቲሸርትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ለ8ኛው ዙር የቡና ቤተሰብ ዓመታዊ ሩጫ የመሮጫ ቲሸርትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘረውን የምታሟሉ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

1. የሩጫ ማሊያው ክለቡ በሚያቀርበው ዲዛይንና ቀለም ሆኖ ደረጃውን በጠበቀ ፓሊስተር መሰራት አለበት።

2. የሩጫው ማሊያ የክለቡ እና የስፖንሰሮች ሎጎ ያረፈበት መሆን ይኖርበታል።

3. ተጫራቹ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

4. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ የብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርበታል።

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 5,000 (አምስት ሺህ ብር) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ሜክሲኮ በሚገኘው የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ህንጻ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 114 መግዛት ይችላሉ። ስለማሊያው ክብደትና ስለሚሰራበት ግብዓት እንዲሁም ዲዛይን በተመለከተ ዝርዝር መረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር የሚሰጥ መሆኑን እናስታውቃለን።

6. ተጫራቹ ቲሸርት ሊሰሩ የሚችሉበትን ዋጋ በስም በታሸገ ኢንቨሎፕ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት ከማይመለስ ናሙና ጋር እስከ ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

7. ጨረታው ነሀሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በክለቡ ፅ/ቤት ይከፈታል።

8. ክለቡ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 11 48 10 72 በስራ ሰዓት ደወስሙ መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
ኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ


Tender details

  • Deadline: 2026-08-25
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-08-26 14:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Coffee Sport Club
  • Buyer address: A A. Mexico Square, Ethiopian Commodity Development Authority Building,Room No. G 05
  • Bid bond: 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር)
  • Bid document price: 5,000 (አምስት ሺህ ብር)
  • Published on: Reporter (Aug 16, 2026)
  • Posted at: 2026-08-17T12:37:18.000Z
← Back to all tenders