House Furniture

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት የተለያዩ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 04/2019

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

  • ምድብ-1፡ Office Furniture
  • ምድብ-2፡ Hot and Cold Water Dispenser, Fully Automated Ultrasonic BMI Machine, Electric Motorcycle

ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች ማሟላት የሚችሉ ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ፡፡

1. በጨረታው ለመካፈል ተጫራቾች አግባብነት ያለው የዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት (VAT)፤ የግብር ክፍያ መለያ የምስክር ወረቀት (TIN)፣ የገንዘብ ሚኒስቴር ባወጣው የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀትና ጨረታ ላይ እንዲሳተፉ ከግብርና ታክስ ሰብሳቢ መ/ቤቶች የሚሰጣቸውን የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

2. ተጫራቾች ለምድብ-1፡ብር 28,000.00 እና ለምድብ-2፡ብር 11,000.00 የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በCPO ወይም በባንክ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች የቴከኒከ እና የፋይናንስ የመወዳደሪያ የመጫረቻ ሰነዶች በታሸገ ኤንቨሎፖች በአንድ ኦሪጂናልና በአንድ ኮፒ እስከ 6/1/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ቢሮ ቁጥር 602 ለዚህ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

 4. ጨረታው በዚሁ 6/1/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት 4፡05 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በቢሮ ቁጥር 602 ይከፈታል።

5. ተጫራቾች የእያንዳንዱ ምድብ የጨረታው ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር ) በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ ከድርጅቱ ግዥና ትራንስፖርት ክፍል ቢሮ ቁጥር 011 መውሰድ ይችላሉ፡፡

6. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ :- ሜክሲኮ አደባባይ ወደ ሳርቤት በሚወስደው መንገድ
300 ሜትር ዝቅ ብሎ
ስልክ ቁጥር 011-551-32 88
ፖ.ሣ.ቁ 3375 አአ
የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-16
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-09-16 10:05
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Petroleum Supply Enterprise
  • Buyer address: ሜክሲኮ አደባባይ ወደ ሳርቤት በሚወስደው መንገድ 300 ሜትር ዝቅ ብሎ ስልክ ቁጥር 011-551-3288 ፖ.ሣ.ቁ 3375 አአ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: የእያንዳንዱ ምድብ 300 (ሶስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 17, 2026)
  • Posted at: 2026-08-18T07:44:47.000Z
← Back to all tenders