Textile, Garments and Uniforms
የልደታ ልማት አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የተለያዩ እቃዎችን ግዥ መፈጸም ይፈልጋል
More tags
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥው መለያ ቁጥር 01/2019ዓ.ም
በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 9 አስተዳደር ስር ያለው ልደታ ልማት የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የ2019ዓ.ም በጀት ዓመት የሚያስፈልገውን
- ሎት 1. የደንብ ልብስ የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 36,000.00
- ሎት2. አላቂ የቢሮና የትምህርት ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 20,500.00
- ሎት3. የጽዳት እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 10,200.00
- ሎት4. የቋሚ እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 52,940.00
- ሎት5. ለሕትመት የጨረታ ማስከበርያ በብር መጠን 1,500.00
- ሎ6. የደንብ ልብስ ስፌት የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 1500.00
- ሎት7. የከተማ ግብርና ግብዓቶች የዓሣ እና የዶሮ መኖ የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 3,000.00
- ሎት8. ለፕላንት፤ ለማሽነሪ እና ለመሣሪያ ዕድሳት እና ጥገና ጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 3,800.00
- ሎት9. አላቂ የሕክምና ቁሳቁስ የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 500.00
ብቃት ያላቸውና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾች አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት።
1. በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ በመንግሥት ግ/ን/አስ/ኤጀንሲ ድህረ-ገጽ ላይ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር የተመዘገቡ የቲንና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
2. ተጫራቾች ጨረታውን በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
3. ተጫራቾች ጨረታቸውን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ በተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ የማይመስስ ብር አንድ ሎት 200 (ሁለት መቶ) በመክፈል በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ልደታ ልማት የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ10ኛው (አስረኛው) ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በማግስቱ 3፡00 በልደታ ልማት የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ይከፈታል።
6. የመክፈቻው ቀን ቅዳሜ፤ እሁድ ወይም በበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ የሥራ ቀን ታሽጎ ይከፈታል።
ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ሎት 1 ሎት 2 ሎት 3 ሎት 4 ሎት 5 ሎት እና 9 ብቻ ናሙና ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን በቀረበው የፍላጎት መግስጫ መሠረት የተሟላ የፍላጎት መግለጫ ማዘጋጀትና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
7. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸው እቃዎች የሞሉት ዋጋ ከቫት ጋር መሆኑን መለየት አለባቸው።
8. የዘገየ ጨረታና ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
9. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸው እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ገዥ ፈጻሚው መሥሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
10. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ስሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ (ጥያቄ)
አድራሻ ልደታ ክ/ከተማ በወረዳ 09 ስር የሚገኘው ልደታ ልማት የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ስልክ ቁጥር፡- 011 557 7520/011 557 8474
የልደታ ልማት አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-27
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ በ10ኛው (አስረኛው) ቀን በ8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-28 12:00
- Bid opening (note): በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ በ10ኛው (አስረኛው) ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በማግስቱ 3፡00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Lideta Limat Elementary School
- Buyer address: ልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 09 ስር የሚገኘው ልደታ ልማት የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: በየሎቱ 200 (ሁለት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Aug 17, 2026)
- Posted at: 2026-08-18T08:07:49.000Z