House Furniture

በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ጤና ጣቢያ በ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል

Description

በግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ጤና ጣቢያ በ2019 በጀት ዓመት 1ኛ ዙር ጨረታ ለጤና ጣቢያችን አገልግሎት የሚውሉ ግብዓቶችን ማለትም ሎት 1 - ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ፣ ሎት 2 ፡- የፈርኒቸር ዕቃዎች ፤ ሎት 3 - የህንፃ መሳሪያዎች ሎት ፤ 4 ፦ የደንብ ልብሶች ፣ ሎት 5 - የደንብ ልበስ ስፌቶች ፤ ሎት 6 - የፅዳት ዕቃዎች ሎት 7 – የፅህፈት መሳሪያዎች ፤ ሎት 8 - የህትመት ስራዎች ፤ ሎት 9 ፡- የጥገናና ፓርቲሽን ስራዎች ፤ ሎት 10 ፡- የፎቶ ዕጥበት ስራዎች ፣ ሎት 11 - የትራንስፓርትና ጭነት አገልግሎት ስራዎች ፤ ሎት 12 - የእሳት ማጥፊያ ሙሌት ስራዎች ፤ ሎት 13 ፡- የፍጆታ ምርቶች ፤ ሎት 14 ፡- የሽንት ቤትና የውሀ ቱቦዎች ጥገና ስራ ፣ ሎት 15 ፡- የላብራቶሪ ሪኤጀንቶች ፤ መድሀኒቶችና የህክምና ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል ፡፡

በመሆኑም በጨረታው ለመወዳደር

1. የንግድ ምዝገባና የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ማስረጃ ፣

2. የግብር ከፋይነት ቲን ነምበር ማስረጃ ፤

3. የቫት ተመዝጋቢነት /የተጨማሪ እሴት ታክስ ማስረጃ ፣

4. ያቅራቢነት የተመዘገቡበት ማስረጃ ኮፒ ፤

5. የዘመኑን ግብር ስለመከፈሉ የሚያረጋግጥ የግብር ከፋይነት ማስረጃ / ከሊራንስ / ማቅረብ የሚችሉ ፤

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ላይ የድርጅቱ ስም ፤ ፊርማና ህጋዊ ማህተም ማድረግ አለባቸው፤

7. ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም ፤

8. ተጫራቾች የዋጋ ዝርዝራቸውን በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ ሞልተው ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን የሚሞላው ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት ነገር ግን ቫትን ሳያካትት የሚቀርብ ዋጋ ቫትን እንዳካተተ ተደርጎ ይወሰዳል ፤

9. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የሚጫረቱበትን ለአንድ ሎት የማይመለስ ብር 200.00 / ሁለት መቶ ብር / በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚችሉ ፡፡

10. ከካሽ ሬጅስተር ውጭ የእጅ በእጅ ደረሰኝ የምትጠቀሙ ተጫራጮች ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ኪውአር ኮድ ያለው ደረሰኝ ካልሆነ በስተቀር የማናስተናግድ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን ፤

11. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚጫረቱበት ለእያንዳንዱ በሎት ቢል ቦንድ በሲፒኦ /CPO / የተዘጋጀ ብር 10000.00 / አስር ሺህ ብር / ሲሆን የጨረታ ሰነዱን ሲያስገቡ ማስያዝ ይኖርባቸዋል ፤

12.ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ስርዝ ድልዝ የሌለበትና ሰነዳቸው ላይ ለየትኛው እቃ /ሎት እንደሚወዳደሩ ለይተው መፃፍ አለባቸው ፤

13.ተጫራቾች በገዙት ሰነድ መሰረት የሚጫረቱበትን ዋጋ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ በእያንዳንዱ ሎት ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻ ታሽጎ ዘወትር በስራ ሰዓት እንግሊዝ ኢምባሲ ፊት ለፊት በሚገኘው ወረዳ 07 ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ በመቅረብ ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችኋል ፤ በአንድ ላይ ታሽጎ የሚቀርብ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም ፤

14.ተጫራቾች የምትጫረቱባቸውን ዕቃዎች ሳምፕል / ናሙና / ጥራታቸውን በጠበቀ መልኩ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ አለባቸው ፤ ሆኖም ናሙናውን እንዳለ ማቅረብ የማይቻል ከሆነ በግልፅ በሚታይ ሁኔታ የተነሳ ፎቶ ግራፍ አልያም የዕቃውን ዝርዝር መግለጫ በፅሁፍ ማቅረብ ወይም ማኑዋል ማቅረብ ይኖርባቸዋል

15.የቀረቡት ናሙናዎች የጨረታ አሸናፊው ከተገለፀበት ቀን አንስቶ ተሸናፊ ተጫራቾች ያቀረቧቸውን ናሙናዎች በ3 ወራት ውስጥ መውሰድ አለባቸው ፤ ካልተወሰደ ሳምፕለ ውስጥ ለመንግስት ውርስ በማድረግ ገቢ ይደረጋል ፤

16.ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ/ ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም እንዲሁም ራሳቸውን ማግለል አይችሉም ሆኖም የጨረታውን ሂደት ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ ይሆኑና ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ውርስ ተደርጎ በመንግስት ግዥ ላይ እንዳይሳተፉ ይደረጋል ፡፡

17.ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ ያሸነፉበትን 10 % የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል ፤

18 የጨረታው ጊዜ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ከዋለ በኋላ በ11ኛው ቀን 4፡30 ሠዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ 5፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ፤ የመከፈቻው ቀን በዓላትና የዕረፍት ቀናት ላይ ከዋለ በሚቀጥሉት የስራ ቀናት በተመሳሳይ ሰዓት በግልፅ ይከፈታል።

19.መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::

ለበለጠ መረጃ በስልከ ቁጥር 0118-93-20-89 መረጃ ማግኘት ይችላሉ

የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ጤና ጣቢያ


Tender details

  • Deadline: 2026-08-29
  • Bid closing time: 10:30
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ከዋለ በኋላ በ11ኛው ቀን 4፡30 ሠዓት
  • Bid opening: 2026-08-29 11:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ከዋለ በኋላ በ11ኛው ቀን 5፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Yeka Sub City Woreda 07 Health Post
  • Bid bond: 10,000.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Published on: Addis Zemen (Aug 18, 2026)
  • Posted at: 2026-08-18T09:44:20.000Z
← Back to all tenders