Chemicals and Reagents

የሻሸመኔ ከተማ ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የዉሃ ማጣርያ ኬሚካል፣ የዉሃ ቆጣሪ፣ የሰራተኛ የደንብ ልብሶች፣ አላቂ የጽህፈት መሣሪያዎች፣ የቢሮ የጽዳት ዕቃዎች እና የመኪና ጎማ እና የባጃጅ ጎማዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በሻሻመኔ ከተማ መስተዳደር የሻሻመኔ ከተማ ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት

  1. የዉሃ ማጣርያ ኬሚካል
  2. የዉሃ ቆጣሪ
  3. የሰራተኛ የደንብ ልብሶች
  4. አላቂ የጽህፈት መሣሪያዎች
  5.  የቢሮ የጽዳት ዕቃዎች
  6. የመኪና ጎማ እና የባጃጅ ጎማዎች

በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ የሚከተለውን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋበዛሉ፡፡

  1. ዕቃዎቹን በጥራት ለማቅረብ የሚያስችል ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉና የንግድ ፍቃዳቸውን ያደሱ መሆን አለባቸው፡፡
  2. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ ማስከበሪያ 1% ሲፒኦ ወይም ቢድቦንድ ከሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ጋር ማስያዝ አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ከሻሻመኔ ከተማ ዉሃ አገልግሎት ድርጅት ቢሮ አስተዳደርና ሎጀስቲክ ክፍል በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውን እና ኮፒውን (ቴክኒክና ፋይናንሽል ለየብቻ) በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ (ፖስታ) ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 6፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከቀኑ 8፡00 ስዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ጨረታው ይከፈታል፡፡
  6. ተጫራቾች የሚያቀርቡበት ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ጋር መሆኑን ወይም አለመሆኑን መግለጽ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ተመላሽ የሚሆነው አሽናፊው ድርጅት በጽሑፍ ከተገለፀ በኋላ ይሆናል፡፡
  8. የጨረታው አሸናፊ በተጫራቾች መመሪያ በተሰጠው መሰረት የጨረታ አሸናፊነቱ በጽሁፍ እንደተገለጸ አስፈላጊውን የጨረታ ውል ማስከበሪያ ገንዘብ በማስያዝ በሻሻመኔ ከተማ ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ውል መፈራረም አለበት። ይህ ባይፈፀም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡
  9. የእቃዎች ርክክብ የሚካሄደው በሻሻመኔ ከተማ ዉሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ግምጃ ቤት ይሆናል፡፡
  10. የእቃው ብዛት (Quanity) የሚወሰነው በመስሪያ ቤቱ (በድርጅቱ) የበጀት ሁኔታ ላይ ተመርኩዞ ነው፡፡
  11.  መ/ቤቱ የተሻለ አማራጮች ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ሆኖ ከበጀታችን በላይ የሚሆነውን መቀነስ ወይም መጨመር የምንችል መሆኑን እንገልጻለን።

አድራሻ፡- የሻሻመኔ ከተማ ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት

ስልክ  0916871624/0916581638/0916002432/

የሻሸመኔ ከተማ ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት 


Tender details

  • Deadline: 2026-09-03
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 6፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-03 14:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ስዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Shashemene City Water Supply and Sewerage Service
  • Bid bond: 1%
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 17, 2026)
  • Posted at: 2026-08-18T09:47:16.000Z
← Back to all tenders