Spare Parts and Car Decoration Materials
የኮ/ቀ/ክ/ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን የተለያዩ ግዥዎችን በፑሉ ተጠቃሚ ለሆኑ መ/ቤቶች የእቃና አገልግሎት ግዥዎችን በምድብ ከፍሎ በግልፅ ጨረታ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2019
የኮ/ቀ/ክ/ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን የተለያዩ ግዥዎችን በፑሉ ተጠቃሚ ለሆኑ መ/ቤቶች የእቃና አገልግሎት ግዥዎችን በምድብ ከፍሎ በግልፅ ጨረታ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት
- ሎት 1. የከባድ እና መካከለኛ ተሸከርካሪ ጎማ
- ሎት 2. ጎማየጎሚስታ እና ላቪያጆ አገልግሎት
- ሎት 3. የህትመት አገልግሎት
- ሎት 4. መስተንግዶ ውሃና ቆሎ የመሳሰሉት
- ሎት 5. የአዳራሽ ዲኮርና ስቴጅ ኪራይ
- ሎት 6. የድንኳንና ሌሎች አገልግሎቶች ኪራይ
- ሎት 7. የመኪና ኪራይ አገልግሎት
- ሎት 8. ቀላልና መካከለኛ የመኪና ጥገና /ጋራዥ/
- ሎት 9. የከባድ ተሽከርካሪ ጥገና (የጋራዥ አገልግሎት)
- ሎት 10. የኤሌክትሮኒክስ ጥገና
- ሎት 11. የጉልበት ስራ አገልግሎት
- ሎት 12. የኩፖን ሲስተም ሴፍትዌር አግልግሎት ግዥ
1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበትንና አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ፣ ቲን ሰርተፍኬት፣ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም ከፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በእቃ አቅራቢነት የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት እና የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ከላይ የተጠቀሱትን መረጃዎች ዋናውንና ኮፒውን በማቅረብ ዘወትር በስራ ሰዓት መውሰድ ይችላሉ።
3. የጨረታ ሰነዱ በኢንቨሎፕ ታሽጎ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰናድ ዋናውንና ኮፒውን ለየብቻው በፖስታ ታሽጎ የኮ/ቀ/ክ/ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት የመንግሰት ግዥ ቡድን 3ኛ ፎቅ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
4. ጨረታው እስከ 11ኛው ቀን 4፡00 ሠዓት ድረስ ሰነዱ ተመላሽ ተደርጎ በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
5. ተጫራቾች በጋዜጣው ላይ በተገለጹት የጨረታ ዓይነቶች በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይችላሉ።
6. ተጫራቾች በግዙት ጨረታ ሰነድ ላይ ፊርማቸውን፣ የድርጅቱን ማህተም በእያንዳንዱ ገጽ ላይ በመፈረም ማቅረብና ማረጋገጥ አለባቸው::
7. የጨረታ ማስከበሪያ በሎት1 ለተጠቀሰው 30,000 (ሠላሣ ሺህ ብር)-ከሎት2 እስከ ሎት12 10,000 (አስር ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ከሆኑ ከአዳራጃቸው አካል የድጋፍ ደብዳቤ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት ፑል የመንግስት ግዥ ቡድን ስም ተሰርቶ መቅረብ ይኖርበታል።
8. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ጨረታ የጨረታ ዓይነቶች ውስጥ የተዘረዘሩትን ያንዱ ዋጋ እና የጠቅላላውን ዋጋ በግልጽ ከጽ/ቤት ገዝተው በወሰዱት ሰነድ ላይ ማስፈር ይኖርባቸዋል።
9. ተጫራቾሎት 1,3 በተገለፁት ጨረታ ዓይነቶች በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን እስከ ቀኑ 4 ሰአት ድረስ ብቻ ናሙና ማቅረብ /ግዴታ ወደ ፅ/ቤታችን ሳንፕል ክፍል ማስገባት ይኖርባቸዋል። በሎት 12 የኩፖን ሲስተም ሴፍትዌር አገልግሎት ግዥ ጨረታ በተዘጋጀው ሰፔክ መሰረት መሙላት የሚኖርባቸው ሲሆን ጨረታው እንደተከፈተ ስፔኩ ታይቶ ሲረጋጥ አሸናፊው የሚለይ ይሆናል፡፡ ሌሎቹ በጨረታ ሰነዱ በተገፀው ስፔስፊኬሽን መሰረት ዋጋ መሙላት ይኖርባቸዋል።
10. በሎት 11 ለተጠቀሰው የጉልበት ስራ አግልግሎት የቫት ሰርፊስትና የአቅራቢነት ሰነድ ግዴታ አይደለም
11. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆኖ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ኮ/ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 06 የሚገኘው የክፍለከተማው ህንፃ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 301
ስልክ ቁጥር 0118 350 897
የኮ/ቀ/ክ/ከተማ የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን
Tender details
- Deadline: 2026-08-29
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን 4፡00 ሠዓት
- Bid opening: 2026-08-29 12:00
- Bid opening (note): በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Kolfe Keranio Sub City Administration Design & Construction Works Pool Administration Finance Office
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 18, 2026)
- Posted at: 2026-08-18T09:55:06.000Z